EEP Communication
15.6K subscribers
10.8K photos
33 videos
32 files
2.03K links
EEP Communication
Download Telegram
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
………….///……….
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ሴቶችን ተሳትፎና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የተቋሙ የሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኤዲኤ ገለፁ፡፡
በተቋሙ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች፣ በኦፕሬሽንና በሁሉም የስራ መስኮች ከጥናት ጀምሮ እስከ ትግበራ ድረስ ባለው ሰንሰለት ሴቶችን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎች በስፋት መከናወን እንዳለባቸው በስርዓተ ፆታና ስርፀት ላይ ትኩረት ባደረገው የአምስት ቀናት ስልጠና መዝጊያ ላይ ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ ሌንሴ እንዳሉት ከህብረተሠቡ 50 በመቶ የሚሆኑትን ሴቶች ያገለለ ልማት ትርጉም ሊኖረው አይችልም፡፡
በመሆኑም ውጤታማ ስራ ለማከናወን ከተፈለገ ሴቶችን በየደረጃው ተሳታፊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ለአምስት ቀናት በቆየው ስልጠና የስርዓተ ፆታ ምንነትና የተዛቡ አመለካከቶች፣ የስርዓተ ፆታ ትንተና፣ የስርዓተ ፆታ ዓለማቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊ እንዲሁም የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቲጂካዊ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጧል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ 25 ባለሙያዎች ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ካሉት አጠቃላይ ሠራተኞች ብዛት 15 በመቶዎች ሴቶች መሆናቸውን የተቋሙ የሰው ሀብት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም
ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው
………………….////………………..
የሠመራ አፍዴራ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ፕሮጀክትን የሲቪል እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ የሙከራና ፍተሻ ሥራ ለመስራት መታቀዱን የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስታወቀ፡፡
የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጁ አቶ ኢዮሲያስ ኃይለማርያም እንደተናገሩት በፕሮጀክቱ የማከፋፈያ ጣቢያ የትራንስፎርመር ማስቀመጫ ቤት፣ የኃይል መቆጣጠሪያ ክፍል፣ የመኖሪያ እና የቢሮ ግንባታዎች በመከናወን ላይ ነው፡፡
የግንባታ ስራው ህዳር 2011 ፕሮጀክቱ ለአፍዴራ እና አካባቢው ነዋሪዎች ብሎም ለጨው ማምረቻና የአዮዲን ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ አልሞ የተገነባ ነው፡፡
በአፍዴራ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት 40 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለው አንድ የኃይል ትራንስፎርመር እንደሚገጠምለት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በረሃማ በሆነ አካባቢ የሚገኝ ቢሆንም ተቋራጩ ጥልቅ ቁፋሮ በማካሔድ ለግንባታ እና ለመጠጥ የሚያገለግል ውሃ ማቅረቡንና ይህም ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር ለጣቢያው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሠመራ አፍዴራ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ፕሮጀክት አካል የሆነውና 195 ኪ.ሜ የሚረዝመው የሠመራ-አፍዴራ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታም በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/

ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም.
የአዋሽ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ
…………./////………..
በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በጎርፍ ተጥለቅልቆ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው የአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ላለፉት 49 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ከነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነበር፡፡

በወቅቱ ከተርባይን ወለል እስከ ተርባይን ሮተር ማገናኛ ዘንግ (Turbine Rotor Coupling Shaft) ድረስ ያሉት የኤሌክትሮ-መካኒካል እቃዎች በውሃ ተውጠው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

ለሁለት ወራት አካባቢ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው ጣቢያ አንድ ዩኒት ወደስራ ማስገባት በመቻሉ ጣቢያው በከፊል ስራ የጀመረ ሲሆን ቀሪውን አንድ ዩኒት ስራ ለማስጀመር በሂደት ላይ ይገኛል።

ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ/ም
የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) መሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅም ግንባታ ስምምነት ተፈረመ
…………….////……………….
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የተሰኘ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅም ግንባታ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ሥምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ተፈራርመዋል፡፡
ሥምምነቱ በዋናነት የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የአሰራር ሥርዓትን ከተቋሙ የሥራ ባህሪ አንፃር የመተግበር እና የማዘመን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ሥምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢ.አር.ፒ የአሰራር ሥርዓትን ከሰባት ዓመት በላይ የተገበረውና ውጤታማ አፈፃፀም ያስመዘገበበት በመሆኑ ተቋሙ በቀላሉ ወደ ትግበራ እንዲገባ እና የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ ይረዳዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በርካታ ሥራዎችን በትብብር በመስራት መልካም ግንኙነት መመስረታቸውን ተናግረዋል፡፡
ስምምነት የተፈረመበትን የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) መሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅም ግንባታ ስራ በተያዘለት በጀትና ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም.
ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) ተግባራዊ ለማድረግ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ
.....///.…...
ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የአሰራር ሥርዓትን በተቋሙ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የሥራ ክፍሎች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሞደርናይዜሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ገነቱ ደሳለኝ እንደገለፁት ተቋሙ ያሉትን ሀብቶች በአንድ የመረጃ ቋት ውስጥ መዝግቦ ለማስተዳደር የኢ.አር.ፒ ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት በተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት ዝግጅት እየተደረገ በመሆኑ በየደረጃው ያሉ የሥራ ክፍሎች በባለቤትነት ስሜት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የአሰራር ሥርዓቱን ለመተግበር ከሀብት ምዝገባ ጋር የተያያዙ የመረጃ ክፍተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት ኃላፊው ችግሩን ለመቅረፍም ሁሉም የሥራ ክፍሎች በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
እንደ አቶ ገነቱ ገለፃ ኢ.አር.ፒ የአሰራር ሥርዓት ሁለንተናዊ የሆነ ተቋማዊ ለውጥ ከማምጣት ባሻገር መረጃዎችን በአግባቡ በመመዝገብ የሀብት ብክነትን ያስቀራል፡፡
ኢ.አር.ፒ የአሰራር ሥርዓት የፋይናንስና ቁጥጥር፣ የሰው ሀብትና ፔሮል፣ የመረጃ ማዕከል፣ የንብረት አስተዳደርና የዕቃ ግምጃ ቤት እንዲሁም መሰል አስተዳደራዊ ሞጁሎች ያሉት ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሳፕ ከተባለው የጀርመን ሶፍትዌር አምራች ኩባንያ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የአሰራር ሥርዓት ሶፍትዌር ፈቃድ ለመግዛት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለነቢዩ መሀመድ ልደት(መውሊድ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሠላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይመኛል፡፡
የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው
የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነው
……………..////…………..
በኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘውን የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እየተፋጠነ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ገለፁ፡፡
ምክትል ሥራ አስኪያጁ ኢንጂነር አባይነህ ጌትነት እንዳሉት ፕሮጀክቱ ከፋይናንስ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች የታሰበውን ያህል በፍጥነት ባይጓዝም ወሳኝ የሚባሉ የተለያዩ ሥራዎች ግን ተሰርተዋል፡፡
ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው ለዚህ ፕሮጀክት መንግስት ትልቅ ትኩረት በመስጠቱና የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ በመቻሉ በተያዘው መርሃ ግብር ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በአብዛኛው ከግድቡ ግንባታ ጋር የተያያዙ የወንዙን ተፈጥሯዊ አቅጣጫ የማስቀየስ፣ የዋና ግድብና የኃይል ማመንጫ ቤቶች (power houses) ግንባታ የመሰረት ቁፋሮ የተከናወነ ሲሆን የቁፋሮ ስራዎቹ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው የዋናው ግድብ የኃይል ማመንጫ ቤት መሰረት የአርማታ ኮንክሪት RCC ሙሌት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
በአሁን ሰዓት የሠራተኞች መኖሪያ ቤቶችና ቢሮዎች እንዲሁም መንገዶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡
እንደ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የብረታ ብረትና ሜካኒካል ስራዎች በጨረታ ሂደት ላይ ቢሆኑም የግድቡ ውሃ ማስተንፈሻ ቁፋሮ ግን ከሌሎች የሲቪል ስራዎች ጋር ጎን ለጎን እየተከናወነ በመሆኑ ፕሮጀክቱ በተያዘው መርሃ ግብር ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ተነስቶ ፕሮጀክቱ ድረስ የሚደርስ የ400 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ዝርጋታ እና የስዊች ያርድ ግንባታ ከ80 በመቶ በላይ ተጠናቋል፡፡
ለፕሮጀክቱ የተገነባው 80 ኪ.ሜ. የሚሸፍን መንገድ የአካባቢውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ሁለት ወረዳዎችን የሚያገናኝ 170 ሜትር ርዝመት ያለው ድልድይ እንዲሁም የትምህርት ቤቶችና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታና የማስፋፊያ ስራዎች ተከናውነው ለማህበረሰቡ መተላለፋቸውን አብራርተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ 129 ኪሜ ርዝመት ያለው ሰው ሰራሽ ሀይቅ የሚፈጥር ነው፡፡
በተጨማሪም በአካባቢው ካለው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ጋር በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ስራ ከፍተኛ የቱሪዝም ማዕከል በመሆን ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ትልቅ ድርሻ እንደሚያበረክት ይታሰባል፡፡
የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀከት የማመንጨት አቅሙ 2160 ሜጋ ዋት ሲሆን በዓመት በአማካይ 6460 ጊጋ ዋት ሰዓት እንዲያነጭ ታስቦ እየተገነባ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡
ይህም በማመንጨት አቅሙ በሀገሪቱ ካሉ የኃይል ማመንጫ ግድቦች ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ ያስችለዋል፡፡
የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታውን የሲቪል ስራ የቀድሞ ሳሊኒ የአሁኑ ዊ ቢዩልድ እያከናወነ ሲሆን ለፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጭ 2 ነጥብ 525 ቢሊየን ዩሮ ተመድቦለታል፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀም 39 በመቶ ደርሷል፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም.
የትውውቅ መድረክ ተካሄደ
………../////……………
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደተቋሙ ለተቀላቀሉ አዳዲስ የኤሌትሪክ እና የመካኒካል መሐንዲሶች የትውውቅ መድረክ አካሄደ፡፡
በትውውቅ መርሃግብሩ ላይ የተቋሙ የሰው ኃይል ስልጠናና ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድወሰን ካሣ እንደተናገሩት አዳዲሶቹ መሐንዲሶች በኃይል ማመንጫዎች፣ በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎችና የኦፕሬሽን የስራ ክፍሎች የሚመደቡ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል በነበሩት ጊዜያት ሠራተኞች ወደ ተቋሙ ሲቀጠሩ በተደራጀ መልኩ በቂ መረጃ ሳያገኙ ወደ ሥራ መግባታቸው ተቋሙ በፍጥነት ለሚጠብቀው ውጤታማነት እንቅፋት እንደሆነባቸው በመገንዘብ የትውውቅ መድረኩ መዘጋጀቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የትውውቅ መርሃግብሩ ዋና ዓላማ የተቋሙን ራዕይ፣ ተልዕኮ እንዲሁም ተቋሙ ሊያሳካ የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች፣ አደረጃጀቶች እና አሰራር ተቋሙን ለተቀላቀሉ አዳዲስ ሠራተኞች ለማሳወቅ ነው፡፡
ከሰራተኞቹ የሚጠበቀውን በመለየት በአዕምሮ ዝግጁ ሆነው ወደ ሥራ ለማስገባት እንደሆነ ዶ/ር ወንደሰን ጠቁመዋል፡፡
በጊዮን ሆቴል በተካሄደው መድረክ ላይ የተቋሙ የሰው ኃይል ሥራ አስፈፃሚ ጨምሮ ከፍተኛ የስራ መሪዎች ተገኝተዋል፡፡