ተቋሙ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለማዕከሉ እገዛ ማድረግ እንዳለበት ያምናል
……………////……………
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ ከመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ ጋር ተወያዩ፡፡
የማዕከሉ ሥራ አሰስኪያጅ አቶ ቢኒያም በለጠ ማዕከሉ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን ከጎዳና ላይ በማንሳት እየሰጠ ስላለው አገልግሎት ለዋና ስራ አስፈፃሚው ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የሆነ ወጪ ማዕከሉ ያስጀመረውን ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ ህንፃ ስለደረሰበት ደረጃም ገልፀውላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋም ለህንፃው ግንባታ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ አቶ ቢኒያም ጠይቀዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ በበኩላቸው ማዕከሉ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን ከጎዳና በማንሳት እያከናወነ ያለው ተግባር ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለማዕከሉ እንቅስቃሴ ፈተና ቢሆንም ያለምንም የውጭ እርዳታ አገልግሎቱ ሳይስተጓጎል መቀጠሉ የሚበረታታ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ተቋሙም ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለማዕከሉ እገዛ ማድረግ እንዳለበት ያምናል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ማዕከሉ በምን ዓይነት መንገድ ቢታገዝ የተሻለ ይሆናል የሚለውን በመለየት ድጋፍ ለማድረግ ተቋሙ አማራጮችን እንደሚያጠና አቶ አሸብር ተናግረዋል፡፡
መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በአዲስ አበባ ብቻ እስከ 4000 ሰዎችን ከጎዳና አንስቶ ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ማህበር ነው፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ ነው - የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
*******************
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ(ዶ/ር፣ ኢ/ር ) ገለፁ።
2 ሺህ 160 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ በኢትዮጵያ ከሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ(ዶ/ር፣ኢ/ር ) የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ግድቡ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የጊቤ ሶስት ውሃ የሚጠቀም በመሆኑ 6 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሊትር ውሃ ብቻ እንዲይዝ ተደርጎ እንደሚገነባም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፤ይህም ግድቡን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።
ግድቡ “በገበታ ለሀገር” የኮይሻ ፕሮጀክት መካተቱን ጠቅሰው፤ የግድቡ በፍጥነት መጠናቀቅ አካባቢውን የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
የፕሮጀክቱ የኮንትራት ስራዎች ተቆጣጣሪ አቶ ኢዩኤል ሰለሞንም በእስካሁን ሂደት የውሃውን ተፈጥሯዊ አቅጣጫ ማስቀየርን ጨምሮ መሰረታዊ የቁፋሮ ስራዎች እና የማስተንፈሻ ግንባታ ቁፋሮው ከግማሽ በላይ መጠናቀቁንም ገልጸዋል።
ለአራት ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ የግንባታ ስምምነቱ የተፈረመው በመጋቢት 2008 ዓ.ም ነው።
የፕሮጀክቱ የግንባታ አፈፃፀም 39 በመቶ መድረሱን ኢዜአን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ እና ጤናማ የሂሳብ ሪፖርት ለማቅረብ እየተሰራ ነው
……………..///………….
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ እና ወቅታዊ የሂሳብ ሪፖርት ለኦዲት አገልግሎት ቦርድ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የተቋሙ የፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ፡፡
ሥራ አስፈፃሚው አቶ ደመረ አሰፋ እንደገለፁት የተቋሙን የ2012 በጀት ዓመት የሂሳብ ሪፖርትን ለኦዲት አገልግሎት ቦርድ በወቅቱ ለማቅረብ እና ሪፖርቱ ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት የሚመረመረውን የተቋሙን የ2012 በጀት ዓመት ሂሳብ ሪፖርት ለኦዲት አገልግሎቱ በወቅቱ ለማቅረብ የሂሳብ መዝጋት ስራ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ የኦዲት ሪፖርት ከ2009 በጀት ዓመት ጀምሮ ቀደም ሲል ከነበረበት የትችት አስተያየት (disclaimer) ነፃ መሆኑን ሥራ አስፈፃሚው አስታውሰዋል፡፡
የ2012 በጀት ዓመት ሂሳብን ለኦዲት አገልግሎት በወቅቱ በማቅረብ በ2009 የተሰጠውን የኦዲት አስተያየት ለማስቀጠልና የኦዲት ሪፖርቱ ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡
የተቋሙን ሂሳብ እንደ ሀገር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በዓለም አቀፋዊ የፋይናንስ ሪፖርት ስርዓት (IFRS) እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ደመረ በአሁኑ ወቅትም የተቋሙ ቋሚ ንብረት ቆጠራና የዋጋ ክለሳ ስራ በረቂቅ ደረጃ ተጠናቋል ብለዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ተከስቷል
……………/////………………
ከጣና በለስ ወደ ባህርዳር በሚሄደው የ400 ኪሎ ቮልት የኃይል መስመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ዛሬ በኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጣል፡፡
በመስመሩ ላይ የተከሰተው የቮልቴጅ መዋዠቅ በአጠቃላይ የአገሪቱ የኃይል አቅርቦት ላይ ችግር እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
በዚህም ምክንያት በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5 ሰአት ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ተከስቷል።
ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ በተሰሩ ስራዎች ከጊቤ 3 ኃይል ማመንጫ በስተቀር አብዛኛዎቹን የኃይል መመንጫዎች ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ማገናኘት ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ አብዛኛው አካባቢ እንዲሁም ባህርዳርና አካባቢዋ ኃይል ማግኘት የጀመሩ ሲሆን ሁሉንም የሀገሪቱን አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
ጥቅምት 13 ቀን 2013

በመላው ሀገሪቱ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሷል
******************
በመላው ሀገሪቱ ከረፋዱ 5 ሰአት ጀምሮ ለተወሰኑ ሰዓታት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ አገልግሎት ተመልሷል።
የኃይል ማመንጫዎችን ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር መልሶ የማገናኘት ሥራው በስኬት በመጠናቀቁ ደረጃ በደረጃ ሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ተደርጓል።
ለሰዓታት ኃይል በመቋረጡ የተቸገራችሁትን በሙሉ ላሳያችሁት ትዕግስት እያመሰገንን የገጠመንን ችግር ለመቅረፍ ሙያዊ ኃላፊነታችሁን በትጋት ለተወጣችሁ የተቋማችን ባልደረቦች በሙሉ ላሳያችሁት ርብርብ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ/ም

የሕዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ግድብ ነው። ኢትዮጵያውያን፣ አሰቡት፤ ኢትዮጵያውያን ጀመሩት፤ ኢትዮጵያውያን ገነቡት፤ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ይጨርሱታል። አይቀሬ ነው።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ !
ጥቅምት 14 2013
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ በፍጣሪዋ ታምና በሕዝቧ አንድነትና ጽናት የቆመች ሀገር ናት። ጥቂት ሰጥተው ብዙ ሊያዟት በሚሞክሩ ተማምና አታውቅም።
ሕይወታቸውን ሰጥተው ሊታዘዟት በተዘጋጁ ልጆቿ እንጂ። ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ነው። የገነቧት ደግሞ ልጆቿ ናቸው። እነዚህ ልጆቿ በከፈሉት መሥዋዕትነት ዓለምን ጉድ ያሰኙ ታሪኮችን ሠርታለች። እነዚህ አስደናቂ ታሪኮችን ስትሠራ አብረዋት ታሪክ የሠሩ ወዳጆች ነበሯት። የከዷት ወዳጆችም ነበሩ። ይህ ለኢትዮጵያ አዲስ አይደለም። ነገር ግን የዓለም ታሪክ ያረጋገጣቸው ሁለት ሐቆች አሉ።
ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም የሚለው ቀዳሚው ነው። ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለአንድ ዓላማ ከቆሙ ድል ማድረጋቸው አይቀርም የሚለው ደግሞ ሁለተኛው።

በዋና ሥራ አስፈፃሚው የተመራ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ አመራር ቡድን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎበኘ
................./////...............
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ የተመራ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ አመራር ቡድን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጎብኝቷል።
የግድቡ ግንባታ አሁን የደረሰበትን ደረጃ፣ ቀሪ ግንባታውን ለማፋጠንና ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተሰሩ ያሉት ወሳኝ ስራዎችን በተመለከተ በግድቡ ግንባታ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢ/ ር ኤፍሬም ገ/ኪዳን ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
የዋናውን ግድብ ፣ የኮርቻ ቅርፅ ግድቡን የኃይልማመንጫ ቤቱንና ውሃው በግድቡ ላይ የሚፈስበትን ስፍራ ቡድኑ ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
የስራ አመራር ቡድኑ ጉብኝት ዋና ዓላማ በመጀመሪያ ዙር የውሃ መሊት የተመዘገበውን ስኬት በስፍራው በመገኘት ለመመልከትና የፕሮጀክት አስተዳደሩን ለማገዝ ነው።
ይህን መሰል ጉብኝት መዘጋጀቱ የሥራ አመራሩ ፕሮጀክቶችን በቅርበት በመመልከት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ለመስጠት እንደሚያግዘው ታምኖበታል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስራ አመራር ቡድን የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን በጋራ ሲጎበኝ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው።
የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 76 ነጥብ 3 በመቶ ደርሷል።
በተያያዘ ዜና የስራ አመራር ቡድኑ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የተካተተውንና በኮይሻ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትንም ጎብኝቷል።
ጥቅምት 15 ቀን 2013 ዓ/ም

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
………….///……….
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ሴቶችን ተሳትፎና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የተቋሙ የሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኤዲኤ ገለፁ፡፡
በተቋሙ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች፣ በኦፕሬሽንና በሁሉም የስራ መስኮች ከጥናት ጀምሮ እስከ ትግበራ ድረስ ባለው ሰንሰለት ሴቶችን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎች በስፋት መከናወን እንዳለባቸው በስርዓተ ፆታና ስርፀት ላይ ትኩረት ባደረገው የአምስት ቀናት ስልጠና መዝጊያ ላይ ገልፀዋል፡፡
ወ/ሮ ሌንሴ እንዳሉት ከህብረተሠቡ 50 በመቶ የሚሆኑትን ሴቶች ያገለለ ልማት ትርጉም ሊኖረው አይችልም፡፡
በመሆኑም ውጤታማ ስራ ለማከናወን ከተፈለገ ሴቶችን በየደረጃው ተሳታፊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ለአምስት ቀናት በቆየው ስልጠና የስርዓተ ፆታ ምንነትና የተዛቡ አመለካከቶች፣ የስርዓተ ፆታ ትንተና፣ የስርዓተ ፆታ ዓለማቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊ እንዲሁም የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቲጂካዊ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጧል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ 25 ባለሙያዎች ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ካሉት አጠቃላይ ሠራተኞች ብዛት 15 በመቶዎች ሴቶች መሆናቸውን የተቋሙ የሰው ሀብት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው
………………….////………………..
የሠመራ አፍዴራ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ፕሮጀክትን የሲቪል እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ የሙከራና ፍተሻ ሥራ ለመስራት መታቀዱን የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስታወቀ፡፡
የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጁ አቶ ኢዮሲያስ ኃይለማርያም እንደተናገሩት በፕሮጀክቱ የማከፋፈያ ጣቢያ የትራንስፎርመር ማስቀመጫ ቤት፣ የኃይል መቆጣጠሪያ ክፍል፣ የመኖሪያ እና የቢሮ ግንባታዎች በመከናወን ላይ ነው፡፡
የግንባታ ስራው ህዳር 2011 ፕሮጀክቱ ለአፍዴራ እና አካባቢው ነዋሪዎች ብሎም ለጨው ማምረቻና የአዮዲን ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ አልሞ የተገነባ ነው፡፡
በአፍዴራ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ፕሮጀክት 40 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለው አንድ የኃይል ትራንስፎርመር እንደሚገጠምለት ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በረሃማ በሆነ አካባቢ የሚገኝ ቢሆንም ተቋራጩ ጥልቅ ቁፋሮ በማካሔድ ለግንባታ እና ለመጠጥ የሚያገለግል ውሃ ማቅረቡንና ይህም ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር ለጣቢያው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሠመራ አፍዴራ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ፕሮጀክት አካል የሆነውና 195 ኪ.ሜ የሚረዝመው የሠመራ-አፍዴራ ባለ 230 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታም በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም.

የአዋሽ III የኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ
…………./////………..
በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በጎርፍ ተጥለቅልቆ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው የአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ላለፉት 49 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየውና 32 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የአዋሽ III የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በውሃ መጥለቅለቅ አደጋ ምክንያት ከነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነበር፡፡
በወቅቱ ከተርባይን ወለል እስከ ተርባይን ሮተር ማገናኛ ዘንግ (Turbine Rotor Coupling Shaft) ድረስ ያሉት የኤሌክትሮ-መካኒካል እቃዎች በውሃ ተውጠው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።
ለሁለት ወራት አካባቢ አገልግሎት አቋርጦ የነበረው ጣቢያ አንድ ዩኒት ወደስራ ማስገባት በመቻሉ ጣቢያው በከፊል ስራ የጀመረ ሲሆን ቀሪውን አንድ ዩኒት ስራ ለማስጀመር በሂደት ላይ ይገኛል።
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ/ም

የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) መሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅም ግንባታ ስምምነት ተፈረመ
…………….////……………….
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የተሰኘ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅም ግንባታ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ሥምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ተፈራርመዋል፡፡
ሥምምነቱ በዋናነት የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) የአሰራር ሥርዓትን ከተቋሙ የሥራ ባህሪ አንፃር የመተግበር እና የማዘመን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ሥምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢ.አር.ፒ የአሰራር ሥርዓትን ከሰባት ዓመት በላይ የተገበረውና ውጤታማ አፈፃፀም ያስመዘገበበት በመሆኑ ተቋሙ በቀላሉ ወደ ትግበራ እንዲገባ እና የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ ይረዳዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በርካታ ሥራዎችን በትብብር በመስራት መልካም ግንኙነት መመስረታቸውን ተናግረዋል፡፡
ስምምነት የተፈረመበትን የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒግ (ኢ.አር.ፒ) መሰረተ ልማት ዝርጋታና አቅም ግንባታ ስራ በተያዘለት በጀትና ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም.