EEP Communication
15.5K subscribers
10.9K photos
33 videos
32 files
2.03K links
EEP Communication
Download Telegram
የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ እና ወጪውን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው
……………….////…………

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢውን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ እና ወጪውን ለመቀነስ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከፕሮጀክቶች አዋጭነት ጥናት ጀምሮ እስከ ኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ድረስ እንዲሁም በደጋፊ የስራ ሂደቶች ወጪዎችን በመቀነስ እና አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በመለየት ተግባራዊ ለማድረግ አማካሪ ድርጅት ተቀጥሮ እየሰራ ላይ ይገኛል፡፡

በአማካሪ ድርጅቱ የተጀመረው ስራ የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ እና ወጪውን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት የሚችል ሲሆን ጥናቱን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የተቋሙን ወጪ ለመቀነስ እና ገቢውን ለማሳደግ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኛና አመራር የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ለተለያዩ ጉዳዮች የሚወጣውን ወጪ በመቀነስና ብክነትን በማዳን እንዲሁም በየክፍሉ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎችን ወደ ገቢ በመቀየር ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
መስከረም 28 / 2013 ዓ.ም.
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76.35 በመቶ ደረሰ
***********
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76 ነጥብ 35 በመቶ መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፣ በመስኖ ልማት፣ በኢነርጂ እንዲሁም በተፋሰስና የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ የ2013 የሩብ ዓመት የስራ ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በተያዘው 2013 ዓ.ም ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ ለማስቻል በሩብ ዓመቱ የግንባታውን አፈፃፀም በ1 ነጥብ 6 በመቶ ለማሳደግ ታቅዶ በ2 ነጥብ 05 በመቶ ለማሳደግ መቻሉን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል፡፡
በዚህም በሩብ ዓመቱ የግንባታውን አፈፃፀም ከታቀደው በላይ ለማከናወን መቻሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በመስኖ ግድቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመያዙ የተያዘውን ውሃ ወደ ልማት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ዶ/ር ስለሺ ገልፀዋል፡፡
በንፁህ መጠጥ ውሃ እና በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ዙሪያም በሩብ ዓመቱ አበረታች ሥራ መሰራቱን ሚንስትሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአየር ክልል ከበረራ ነፃ እንዲሆን የተደረገው ያለውን የደህንነት ስጋት ለማስቀረት ነው ብለዋል፡፡
በዕቅዱ መሰረት በተያዘው ዓመት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡
# ኢቢሲ
በተቋሙ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ተከበረ
-----------------------//////-----------------------
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓልን በዋናው መ/ቤት አክብሯል፡፡
በዓሉ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል በወጣው ፕሮቶኮል መሠረት በጥቂት ሰዎች ሰንደቅ ዓላማውን በክብረ በመስቀል እንዲከበር ተደርጓል፡፡
የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሠላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለሀገራዊ ብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ጀምሮ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
ክልሎችና ተቋማት ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በዓሉን እንዲያከብሩ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሰጠው አቅጣጫ መሠረት በተቋማችንም እንዲከበር ተደርጓል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በየዓመቱ የጥቅምት ወር መጀመሪያ ሰኞ እንዲከበር መወሰኑ ይታወሳል፡፡
ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ
…………////……..
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብን ጎበኙ፡፡
በስፍራው እየተሰራ ያለውን እና የ"ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክት አካል የሆነውን ሰው ሰራሽ ሐይቅ የግንባታ ሂደት መመልከታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ
..........................///............................
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጎብኝተዋል።

ግድቡ በአንድ ጊዜ 2,160 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን በዓመት ደግሞ በአማካይ 6 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ያመነጫል።

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አጠቃላይ አፈፃፀም በአሁኑ ወቅት 36 በመቶ የደረሰ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ ከኃይል ማመንጫነት ባሻገር ለቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

በግንባታ ላይ የሚገኘውን የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአንድ ወር በፊት መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ: ኢቢሲ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ
********
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ በጋራ እያደረጉት ባለው ሁለተኛ ቀን ጉብኝታቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለመጎብኘት ጉባ ገብተዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው የውሃ ሙሌት ባለፈው ሐምሌ ከተከናወነ በኃላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስፍራው ሲያቀኑ የአሁኑ የመጀመሪያቸው ነው ፡፡

ሁለቱ መሪዎች በቆይታቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁን ያለውን ገፅታ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ፣ ገለፃም ተደርጎላቸዋል፡፡

መሪዎቹ ዛሬ ጠዋት የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ጎብኝተው እንደነበር ኢቢሲዘግቧል።
ግድቡ አሁን ከያዘው በ3 እጥፍ የሚበልጥ ውሃ እንዲይዝ ይደረጋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
*********
ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በዘንድሮው ዓመት አሁን ከያዘው በ3 እጥፍ የሚበልጥ ውሃ እንደሚይዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በጋራ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጉብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የግድቡ ግንባታ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውንም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለተሳተፉ እና አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ደረጃ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ኩራት መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን የተሠራው ሥራ ትልቅ ስኬት ቢሆንም በስኬቶች ከመኩራራት በየጊዜው አዳዲስ ግቦችን በመቅረፅ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ለመውሰድ እንደሚሠራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት ግድቡ ከፍ እንዲል ማድረግ እና አሁን ካለው ውሃ ሦስት እጥፍ እንዲይዝ ለማድረግ የሚሠራ በመሆኑ ይህ ዓመት የግድቡ ዋነኛ ሥራ የሚሠራበት ነው ብለዋል።

በተያያዘም በዚህ ዓመት ኃይል ማመንጨት የሚጀምሩ ተርባይኖች ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ተርባይኖቹ ለስድስት ወራት ሙከራ ካደረጉ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ኃይል ወደ ማመንጨት ይገባሉ ነው ያሉት።

የግድቡን የግንባታ ሂደት የጎበኙበት ምክንያት የሥራውን እንቅስቃሴ ለማየት እና ወደ ፊት በግድቡ አካባቢ ለመሠራት ለታቀዱት ከተሞች የአመቺነት ሁኔታን ለማየት እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት።

ግድቡ ሲሞላ ብዙ ደሴቶችን ስለሚፈጥር ከወዲሁ ያንን እያዩ መዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የግድቡ ሁኔታ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ ውጤታማ እንደሚሆን ለሁሉም ወገን የሚያመላክት ነው ያሉት ዶ/ር ዐቢይ፣ "በየጊዜው ያንን እያረጋገጥን ስኬታችንን እውን ማድረጋችን አይቀርም" ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ/ም
ፕሮጀክቱን ዘንድሮ ከ90 በመቶ በላይ ለማድረስ እየተሰራ ነው፡፡
…………..////…………
የባህርዳር - ወልዲያ - ኮምቦልቻ ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታን በተያዘው በጀት ዓመት ከ90 በመቶ በላይ ለማድረስ እየተሰራ ነው፡፡
በፕሮጀክቱ እንደሚተከሉ ከሚጠበቁት 829 ምሰሶዎች ውስጥ በአሁኑ ሰዓት 746 ምሰሶ ለመትከል የሚያስችል የመሰረት ቁፋሮ ተጠናቋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ደግሞ 115 ምሰሶዎች ተከላ የተከናወነ ሲሆን ቀሪ ምሰሶዎችን የመትከል እና ገመድ የመዘርጋት ሥራዎችንም በ2013 በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው፡፡
ለፕሮጀክቱ መስመር ዝርጋታ የሚሆኑ አብዛኛዎቹ የምሰሶ መትከያ ብረቶችና ገመዶች የፕሮጀክቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ገብተዋል፡፡
የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታውን የቻይናው ሻንጋይ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን በማከናወን ላይ ሲሆን የማስተላለፊያ መስመሩ ግንባታ ደግሞ የህንዱ ታታ ፕሮጀክትስ ሊሚትድ (TATA PROJECTS LTD) እያከናወነው ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱን በማማከር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኢነጂነሪንግ ቢሮ ነው፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም.
የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካይ 436 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ያስገኛል
…………///………..
በኢትዮጵያ ከአዳማ I እና II እንዲሁም ከአሸጎዳ በመቀጠል በአራተኛነት እየተገነባ ያለው የአይሻ II የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት በአማካይ 436 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል፡፡
ዶንግ ፋንግ ኢንተርናሽናል ኮርፖሬሽን (DEC) በተባለ የቻይና ኩባንያ በመገንባት ላይ ያለው ፕሮጀክቱ 48 የንፋስ ተርባይኖች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው 2.5 ሜጋ ዋት በድምሩ 120 ሜጋ ዋት ወይም በዓመት በአማካይ 436 ጊጋ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ይኖረዋል፡፡

በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ክላስተር የስምንት ተርባይኖችና ትራንስፎርመሮች ተከላ ሥራ ተጠናቆ ለፍተሻና ሙከራ ሥራ ዝግጁ ሆኗል፤ ስምንቱን ተርባይኖች በኢትዮ ጅቡቲ መስመር አማካኝነት ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር አገናኝቶ የሙከራ ሥራ ለማስጀመር ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል፡፡

በሁለተኛው ክላስተር የሚገኙ ስምንት ተርባይኖች እንዲሁም በሶስተኛው ክላስተር የሚገኙ ሶስት ተርባይኖች ተከላም ተጠናቋል፡፡

የፕሮጀክቱ የሲቪልና ኤሌክትሮ መካኒካል ግንባታ እየተፋጠነ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻፀም 64 በመቶ ደርሷል፡፡

የአይሻ II የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ በ700 ኪሎ ሜትር፣ ከድሬዳዋ ከተማ በሰሜን ምስራቅ 170 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከጅቡቲ በሰሜን ምዕራብ 150 ኪሎ ሜትር መካከል በሶማሌ ክልል አይሻ ደወሌ ወረዳ ይገኛል፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/

ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም.