EEP Communication
15.5K subscribers
10.9K photos
33 videos
32 files
2.03K links
EEP Communication
Download Telegram
ሚኒስትሩ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ
***********************
የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ከቬራ ሶንግዌ ጋር በመሆን የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታንና በሥራ ላይ የሚገኘውን ጊቤ ሶስት የውሃ ኃይል ማመንጫን ጎበኙ፡፡

ጉብኝቱ ኢትዮጵያ ያሏትን የውሃ ሃብቶች ለዘላቂ እድገትና ለዜጎች ህይወት መሻሻል እንዴት በአግባቡ እየተጠቀመች እንደሆነ ለማየት አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

“በኦሞ ወንዝ ላይ የተለያዩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ማድረጋችን በተመሳሳይ ሌሎች ወንዞቻችንንም እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል” ሚኒስትሩ፡፡

ጊቤ ሶስት የውሃ ኃይል ማመንጫ በአሁኑ ሰዓት 1870 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው ላይ ሲሆን አሁን ግንባታው 39 በመቶ የደረሰው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ደግሞ ሲጠናቀቅ ደግሞ 2160 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚያመነጭ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

“የኮይሻና የሕዳሴ ግድቦች ሲጠናቀቁ አሁን ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት በ170% በማሳደግ በ2022 ሙሉ በሙሉ ለዜጎች ኃይል ለማቅረብ በምናደርገው ጥረት ላይ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ” ማለታቸውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ዘግቧል።

በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ ተገኝተዋል።

መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ/ም
ሚኒስትሩ የታላቁ ህዳሴ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ
*******************
የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከዓለምአቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ፡፡

ኃላፊዎቹ ስለግድቡና ስለግንባታው ሂደት በሚኒስትሩ ገለፃ ተደርጎላቸው ግንባታውን እየተዘዋወሩ ተመልክተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላም በግድቡ ግዝፈትና በግንባታው ሂደት ውስብስብነት መደነቃቸውን ኃላፊዎቹ ለሚኒስትሩ ገልፀውላቸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንዲሁም የተቋሙ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ንጉሴ ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያውያን የገንዘብ ድጋፍ በመገንባት ላይ የሚገኘው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አጠቃላይ አፈፃፀም 76 ነጥብ 3 በመቶ ላይ ደርሷል።

መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ/ም
በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የቆጣሪ ገጠማ ሥራ በመከናወን ላይ ነው
……………///……………..
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የቆጣሪ ገጠማ ስራ በማከናወን ላይ መሆኑን በተቋሙ የስማርት ሜትር ፕሮጀክት ቢሮ ስራ አስኪያጅ አስታወቁ፡፡
ሥራ አስኪያጇ ወ/ሮ ሃይማኖት ተፈራ እንደገለጹት ተቋሙ 130 በሚሆኑ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የቆጣሪ ገጠማ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የቆጣሪዎቹ መገጠም የተቋሙ ደንበኞች ለተጠቀሙት ኃይል ትክክለኛውን ክፍያ እንዲከፍሉ ለማድረግ እንደሚያግዝ ስራ አስኪያጇ አስታውቀዋል፡፡
ይህም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ ቀደም በ40/60 የክፍፍል ስምምነት መሰረት የሚገኘውን ክፍያ በማስቀረት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የወጣውን ኃይል ቆጥሮ በማስከፈል የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ ይጠቅማል ብለዋል፡፡
እንደ ወ/ሮ ሐይማኖት ገለፃ የቆጣሪ ገጠማ ስራው የኃይል ብክነትን ለመለየት እና አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድም ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
በመገጠም ላይ የሚገኙት ቆጣሪዎች በእንግሊዝ ሀገር የተመረቱ “CEWE Prometer 100” የተባሉ ሲሆን የገጠማ ስራውንም “Siemens Proprietary Limited” የተባለ ድርጅት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ 1 ሺ 476 ቆጣሪዎችን እንዲያቀርብ ስምምነት ላይ መደረሱን የጠቀሱት ወ/ሮ ሐይማኖት ከዚህ ውስጥ 1 ሺ 226 ቆጣሪዎች በጣቢዎች ላይ የሚገጠሙ ሲሆን ቀሪ 250 ቆጣሪዎች ደግሞ ለመጠባበቂያነት የሚያገለግሉ ናቸው ብለዋል፡፡
በጣቢያዎች ላይ ለመግጠም ከታሰቡ ቆጣሪዎች መካከል ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ድረስ በ42 ጣቢያዎች ላይ 353 ቆጣሪዎች ተገጥመው የሙከራና የፍተሻ ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡
እንደ ስራ አስኪያጇ ገለፃ በእያንዳንዱ ማከፋፈያ ጣቢያ የሚገጠመው የቆጣሪ ብዛት እንደ ጣቢያው ወጪ መስመር ብዛት የሚወሰን ይሆናል፡፡
የቆጣሪዎች ተከላ የዲዛይን፣ የማምረት እና የማጓጓዝ ስራው በ2012 በጀት ዓመት የተገባደደ መሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ሐይማኖት እስከ ታህሳስ 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የገጠማ ስራውን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡
በቆጣሪ ገጠማ ስራው ላይ ከተቋሙ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ ባለሞያዎች እንዲሳተፉ መደረጉን የተናገሩት ስራ አስኪያጇ ይህም በቀጣይ ለሚከናወኑ የቆጣሪ ገጠማ ስራዎች በራስ አቅም ለመስራት የሚያስችል ልምድ ለማግኘት ታስቦ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
በ130 ጣቢያዎች ላይ ለሚከናወነው የቆጣሪ ገጠማ አጠቃላይ ስራ የአቅርቦት፣ የተከላ፣ የፍተሻና ሙከራ ስራዎች ለማከናወን በዓለም ባንክ የሚሸፈን ከ25 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ብር እና ከ2 ነጥብ 17 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካ ዶላር በጀት ተይዞለታል፡፡
በፕሮጀክቱ ንብረቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ስርቆት ተቋሙን ለተጨማሪ ወጪ ዳርጎታል
……………..////………………….
የኢትዮ- ኬንያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀሎች እየተፈፀሙበት እንደሚገኝ የኢትዮ - ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት የግንባታ አስተባባሪ ገለፁ፡፡
አስተባባሪው አቶ ሰይፉ ፈይሳ እንደገለፁት በኢትዮጵያ በኩል የሚገነባው የ433 ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡
ይሁን እንጅ በወላይታ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች በማስተላለፊያ መስመሩ ሽቦዎች እና የምሰሶ ብረቶች ላይ በተደጋጋሚ የስርቆት ወንጀሎች እየተፈፀመበት ይገኛል ብለዋል፡፡
ይህም ተቋሙን ለተጨማሪ ወጪ በመዳረግ ከ34 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራም እንዳደረሰበት ነው ያስታወቁት፡፡

ኪሳራው የደረሰው በስርቆቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን የማስተላለፊያ መስመሩን አካላት በአዲስ ለመተካትና ለመቀየር፣ እንዲሁም ለመበየድ፣ ለዕቃ ግዥ እና ለምሶሶ (Tower) ቅየራ ተጨማሪ ወጪ በመውጣቱ ነው፡፡

የማስተላለፊያ መስመሩ 994 ምሶሶች ያሉት ሲሆን በተፈፀመው ስርቆት ጉዳት ከደረሰባቸው ምሶሶዎች መካከል አንዱን ሙሉ በሙሉ መቀየሩን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

የግንባታ ሰራው በ2008 ዓ. ም የተጀመረው የኢትዮ- ኬንያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ከ183 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በጀት ተይዞለት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
መስከረም 27 2013 ዓ.ም.
የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ እና ወጪውን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው
……………….////…………

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገቢውን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ እና ወጪውን ለመቀነስ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከፕሮጀክቶች አዋጭነት ጥናት ጀምሮ እስከ ኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ድረስ እንዲሁም በደጋፊ የስራ ሂደቶች ወጪዎችን በመቀነስ እና አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በመለየት ተግባራዊ ለማድረግ አማካሪ ድርጅት ተቀጥሮ እየሰራ ላይ ይገኛል፡፡

በአማካሪ ድርጅቱ የተጀመረው ስራ የተቋሙን ገቢ ለማሳደግ እና ወጪውን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት የሚችል ሲሆን ጥናቱን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የተቋሙን ወጪ ለመቀነስ እና ገቢውን ለማሳደግ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኛና አመራር የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ለተለያዩ ጉዳዮች የሚወጣውን ወጪ በመቀነስና ብክነትን በማዳን እንዲሁም በየክፍሉ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎችን ወደ ገቢ በመቀየር ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/
መስከረም 28 / 2013 ዓ.ም.
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76.35 በመቶ ደረሰ
***********
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም 76 ነጥብ 35 በመቶ መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፣ በመስኖ ልማት፣ በኢነርጂ እንዲሁም በተፋሰስና የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ የ2013 የሩብ ዓመት የስራ ዕቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በተያዘው 2013 ዓ.ም ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ ለማስቻል በሩብ ዓመቱ የግንባታውን አፈፃፀም በ1 ነጥብ 6 በመቶ ለማሳደግ ታቅዶ በ2 ነጥብ 05 በመቶ ለማሳደግ መቻሉን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ገልፀዋል፡፡
በዚህም በሩብ ዓመቱ የግንባታውን አፈፃፀም ከታቀደው በላይ ለማከናወን መቻሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በመስኖ ግድቦች ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመያዙ የተያዘውን ውሃ ወደ ልማት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ዶ/ር ስለሺ ገልፀዋል፡፡
በንፁህ መጠጥ ውሃ እና በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ዙሪያም በሩብ ዓመቱ አበረታች ሥራ መሰራቱን ሚንስትሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአየር ክልል ከበረራ ነፃ እንዲሆን የተደረገው ያለውን የደህንነት ስጋት ለማስቀረት ነው ብለዋል፡፡
በዕቅዱ መሰረት በተያዘው ዓመት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡
# ኢቢሲ
በተቋሙ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ተከበረ
-----------------------//////-----------------------
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓልን በዋናው መ/ቤት አክብሯል፡፡
በዓሉ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመከላከል በወጣው ፕሮቶኮል መሠረት በጥቂት ሰዎች ሰንደቅ ዓላማውን በክብረ በመስቀል እንዲከበር ተደርጓል፡፡
የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሠላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለሀገራዊ ብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ጀምሮ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
ክልሎችና ተቋማት ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በዓሉን እንዲያከብሩ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሰጠው አቅጣጫ መሠረት በተቋማችንም እንዲከበር ተደርጓል፡፡
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በየዓመቱ የጥቅምት ወር መጀመሪያ ሰኞ እንዲከበር መወሰኑ ይታወሳል፡፡
ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም.