EEP Communication
15.5K subscribers
10.9K photos
33 videos
32 files
2.03K links
EEP Communication
Download Telegram
ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የቢሾፍቱ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ
………………..///………………
ከአዲስ አበባ በ45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የተገነባው ባለ 400/230/15 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ ዳዊት ገብረ እግዚአብሄር ገለጹ፡፡
አቶ ዳዊት እንደገለፁት የማከፋፈያ ጣቢያው የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡
ከነባሩ አቃቂ - ገላን ባለ 400/230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ እስከ ቢሾፍቱ ማከፋፈያ ድረስ 46 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ጥንድ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታም ተከናውኗል፡፡
የፕሮጀከቱ የሳይት ተቆጣጣሪ መሃንዲስ አቶ ዘውዱ ለገሰ እንደገለፁት ማከፋፈያ ጣቢያ ሁለት ባለ 600 ሜጋ ቮልት አምፒር እና ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡
ጣቢያው ጥንድ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመር እና ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት እንዲሁም 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
የማከፋፋያ ጣቢያውን የገነባው ላርሰን ኤንድ ቱብሮ የተባለ የህንድ ኩባንያ ሲሆን ግንባታው ለመጨረስ ከ25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው መገንባት በቢሾፍቱ ከተማ እና በዙሪዋ ለሚገኙ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችና የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ለህብረተሰቡ የኃይል ፍላጎት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይታመናል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም.
ፓርቲው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
...............//////................
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ( ኢዜማ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የግማሽ ሚሊዮን ብር ስጦታ አበረከተ።
በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በልዩነት ብቻ የተመሰረተውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በማሻሻል በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ፓርቲው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያደረገው ድጋፍም የትብብሩ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንዳሉት ስጦታው በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ከሚኖሩ የፓርቲው አባላት ለዚሁ ዓላማ የተሰበሰበ ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ባለፈው ታሪካችው በሀገራዊ የጋራ አጀንዳዎች ላይ የማይደራደሩ መሆናቸውን አስታውሰው ሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በልዩነት ምክንያት ሀገራዊ ጥቅማቸውን ለአፍታም ቢሆን አሳልፈው መስጠት እንደሌለባቸው አሳስበዋል፡፡
ኢዜማ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የማያወላውል አቋም እንዳለውና ወደፊትም ድጋፉን እንደሚቀጥል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አረጋግጠዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብራሄራዊ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ታገል ቀኑብህ በበኩላቸው ኢዜማ ያደረገው ድጋፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አንድ መሆን እንዳለባቸው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ከአሁን በፊት ፓርቲዎች በእንደዚህ ዓይነት ሀገራዊ ልማት ላይ የሚያሳዩት ተሳትፎ ብዙም እንዳልነበር አቶ ታገል ጠቁመዋል፡፡
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነገ መንግሥት ሆነው ቢመረጡ የሚያስተዳድሩት አሁን በልዩነት ሁነው የሚሰሩትን መልካም ሥራ በመሆኑ በጋራ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric/?modal=admin_todo_tour
መስከረም 12 ቀን 2013ዓ/ም
የጊንጪ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ
…………………../////……………..
ላርሰን ኤንድ ቱብሮ በተባለ የህንድ ኩባንያ የተገነባው የጊንጪ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ፡፡
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ገ/እግዝአብሔር እንዳስታወቁት የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ በጊንጭና በዙሪያው የሚገኙ ከተሞችን የኃይል መቆራረጥ ከማስቀረቱም በተጨማሪ ወደ ፊት አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል የሚያገኘው ከገፈርሳ - ጌዲዮን ከተዘረጋው ባለ 230 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተተክለውለታል፡፡
ጣቢያው ሁለት ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ እና 10 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡
በ2008 ዓ.ም የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪው 67 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric
መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም.
የኃይል ሽያጭ ስምምነት ተደረገ
………………..////…………………
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል ሽያጭ ስምምነት አደረጉ፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈረው ተሊላ ተፈራርመዋል፡፡
ትናንት በተካሄደው የፊርማ ሥነ-ስርዐት ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ስምምነቱ ተቋማቱ በተሻለ መንገድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡
ተቋማቱ በኃይል ኔትወርክ የተገናኙ እንደመሆናቸው ስምምነቱ ያላቸውን ቅንጅትና ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እና የስራ አፈጻጸማቸውን ለማሻሻል የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈረው ተሊላ በበኩላቸው መስሪያ ቤቶቹ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በህግ በተወሰነው አግባብና በስምምነታቸው መሰረት እንዲወጡ እንደሚያስችላቸው ነው ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማርኬቲንግ እና ገበያ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ታምራት እንደተናገሩት ስምምነቱ የሁለቱ ተቋማትን የኤሌክትሪክ ግብይት በህግ አግባብ ለማከናወን ያስችላቸዋል፡፡
በተቋማቱ መካከል ቀደም ሲል የነበረው የኤሌክትሪክ ግብይት በ40/60 ሽያጭ ስምምነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የአሁኑ ስምምነት ግን የቀድሞውን አሰራር በመለወጥ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሚገጠም ቆጣሪ ንባብ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ይሆናል፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric
መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም.
በዱከም እና በሞጆ የተገነቡት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች ሊመረቁ ነው
…………………./////………………..

ለዱከም እና ለሞጆ ከተሞችና እና አካባቢያቸው እንዲሁም በዙሪያቸው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የኃይል ፍላጎት ምላሽ የሚሰጡ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡

ከአዲስ አበባ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በዱከም ከተማ የተገነባው ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል፡፡
ከአዲሱ የቢሾፍቱ 400/230/15 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ተነስቶ እስከ ዱከም ማከፋፈያ ድረስ 16 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታም ተከናውኗል፡፡

በሞጆ ከተማ የተገነባው ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያም በተመሳሳይ የግንባታ፣ የፍተሻ እና የሙከራ ስራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል፡፡

ሁለቱም ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጥንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመር እና አስር ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሏቸው ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተተክለውላቸዋል፡፡

የማከፋፈያ ጣቢያዎቹ ከጊንጪና ቢሾፍቱ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ጋር በአንድነት በቅርቡ ይመረቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፌስ ቡክ ገፃችንን በመወዳጀት ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
https://www.facebook.com/Ethioelectric
መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም.
ጤና ሚኒስቴር ለፕሮጀክቱ ግብዐትና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን አደርጋለው አለ
......................../////.................
የጤና ሚኒስቴር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ኮሮናን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ አስታወቀ።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አብርሃም በላይ እንዲሁም የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በፕሮጀክት ሳይቱ ላይ ኮሮናን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ ገምግመዋል።
የህዳሴ ግድብ የሀገራችን ብልጽግና የሚረጋገጥበት ታላቅ ፕሮጀክት በመሆኑና በተያዘው ዓመት ለማሳካት የታለመው የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትና የቅድሚያ ኤሌክትሪክ ማመንጨት እቅድ በኮቪድ ምክንያት እንዳይስተጓጎል ለፕሮጀክቱ ቅድሚያ በመስጠት በግብዐትና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ ከተቋሙ ጋር በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል።
ይህን የሚከታተልና የሚያስፈጽም ከጤና ሚኒስቴር፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጤና ቢሮና ከህዳሴ ፕሮጀክት የተውጣጣ ኮሚቴ በማዋቀር የተጀመረውን የኮሮና መከላከል ስራ በተጠናከረ መልኩ የሚከታተል ግብረ ኃይል እንደሚቋቋም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
ቫይረሱን ለመከላከል የሚሰራው ስራ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የስራ ኃላፊዎቹ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
መስከረም 16ቀን 2013 ዓ/ም
የቱለፋ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ ለምርቃት ዝግጁ ሆነ
..................///...................
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማርያም ወረዳ የተገነባው የቱለፋ ባለ 132/33/15 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታው መጠናቀቁንና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የመካከለኛ ሪጅን ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ዳይሬክተር አቶ አበባው ያለው እንዳስታወቁት የማከፋፈያ ጣቢያው መጠናቀቅ በቱለፋ ከተማ እና በዙሪያው በሚገኙ ከተሞች ይስተዋል የነበረውን የኃይል መቆራረጥ ከማስቀረቱም በተጨማሪ በአካባቢው ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል፡፡
ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነው ይህ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 63 ሜጋ ዋት አቅም መሸከም የሚችል ኤ.አይ.ኤስ ብሬከር ሲስተም (Air Insulated System) የተገጠመለትም ነው ተብሏል፡፡
አቶ አበባው እንዳሉት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው አራት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ያሉት ሲሆን አቅማቸውም 63/23/40 ሜጋ ቮልት አምፒር ነው፡፡
ከነባሩ የደብረ-ብርሃን - ለገጣፎ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ላይ መስመር በመዘርጋት ከኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ጋር ማገናኘት ተችሏል ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ባለ 33 ኪሎ ቮልት መስመር ብቻ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ነው ኃላፊው የጠቆሙት፡፡
የማከፋፈያ ጣቢያውን የገነባው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ትራንስሚሽን ሰብስቴሽን ኮንስትራክሽን (የራስ ኃይል) ሲሆን ግንባታውን ለመጨረስ ከ4 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡
ፕሮጀክቱን በማማከርም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስሚሽን ኢንጂነሪንግ ቢሮ ተሳትፎ አድርጓል፡፡
የቢሾፍቱ፣ ዱከም እና ሞጆ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተከናወነ ነው
...................///...............
የቢሾፍቱ ባለ 400/230/15፣ የዱከም ባለ 230/15 እና የሞጆ ባለ 230/15 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንዲሁም አባ ገዳዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የወላይታ ሶዶ የኮንቨርተር ጣቢያ የሙከራ (commissioning) ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል
.........................///.........................
የወላይታ ሶዶ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት የሙከራ ስራ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

በፕሮጀክቱ የሰብስቴሽን ኢንቻርጅ ባለሙያው አቶ ሃብታሙ ግርማ እንደገለፁት የኮንቨርተር ጣቢያውን የግንባታ ስራ በማጠናቀቅ በአሁኑ ወቅት የሙከራ ስራው በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከወላይታ ሶዶ ከተማ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እየተገነባ የሚገኘውን የኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት የሙከራ ስራ በቅርቡ በማጠናቀቅ የፍተሻ ስራውን ለመጀመር እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም አቶ ሃብታሙ ገልፀዋል፡፡

እንደ አቶ ሃብታሙ ገለፃ የሙከራ ስራው ከስራ ተቋራጩ፣ ከአማካሪ ድርጅቱ እንዲሁም ከተቋሙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች በተውጣጡ ባለሙያዎች በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የኮንቨርተር ጣቢያው ከወላይታ ሶዶ ነባሩ የማከፋፈያ ጣቢያ የወጡ አራት ባለ 400 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመሮች እንዳሉት ነው ባለሙያዉ የጠቆሙት፡፡

ጣቢያው በዲዛይን፣ በቴክኖሎጂ እና በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሆነ ያነሱት አቶ ሃብታሙ ይህም ቀጥተኛ ዥረት (Directe current) መሆኑ እና 12 ኮንቨርተር ትራንስፎርመሮች የተገጠሙለት በመሆኑ ከሌሎች ማከፋፈያ ጣቢያዎች ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ይህ ባለ 500 ኪሎ ቮሎት የኮንቨርተር ጣቢያ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ማስተላለፊያ መስመር የማሻገር አቅም ያለው እንደሆነም ነው ባለሙያው ያብራሩት።

የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ኬንያን ጨምሮ ታንዛኒያን እና ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የኢትዮ- ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የኮንቨርተር ጣቢያ መገንባት የክፍለ-አህጉራዊ የኃይል ትስስርን ከማጠናከሩም ባሻገር የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግ ያግዛልም ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱን የግንባታ ስራ ሲመንስ የተሰኘ የጀርመን ኩባንያ በማከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በማማከር ስራው ላይ ደግሞ ትራክ ቤል የተሰኘ ኩባንያ ተሳትፎበታል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል በመገንባት ላይ የሚገኘው የኢትዮ -ኬንያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር እና ኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት የግንባታ ስራ ቢጠናቀቅም ወደ አገልግሎት ለማስገባት የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆነውንና በኬኒያ መንግስት በኩል እየተገነባ የሚገኘውን ፕሮጀክት መጠናቀቅ ይጠብቃል ነው የተባለው፡፡

የኮንቨርተር ጣቢያው ከዓለም ባንክና ከአፍሪካ ልማት በብድር በተገኘ ከ285 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በጀት ተይዞለት በመከናወን ላይ የሚገኝ መሆኑን ከፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ ውስጥም 243 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላሩ በዓለም ባንክ እንዲሁም ቀሪው ከ42 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላዩ ደግሞ በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡

የኮንቨርተር ጣቢያው የግንባታ ስራ በ2009 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
ሚኒስትሩ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ጎበኙ
***********************
የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ከቬራ ሶንግዌ ጋር በመሆን የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታንና በሥራ ላይ የሚገኘውን ጊቤ ሶስት የውሃ ኃይል ማመንጫን ጎበኙ፡፡

ጉብኝቱ ኢትዮጵያ ያሏትን የውሃ ሃብቶች ለዘላቂ እድገትና ለዜጎች ህይወት መሻሻል እንዴት በአግባቡ እየተጠቀመች እንደሆነ ለማየት አጋጣሚ እንደፈጠረላቸው ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

“በኦሞ ወንዝ ላይ የተለያዩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ማድረጋችን በተመሳሳይ ሌሎች ወንዞቻችንንም እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል” ሚኒስትሩ፡፡

ጊቤ ሶስት የውሃ ኃይል ማመንጫ በአሁኑ ሰዓት 1870 ሜጋ ዋት ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው ላይ ሲሆን አሁን ግንባታው 39 በመቶ የደረሰው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ደግሞ ሲጠናቀቅ ደግሞ 2160 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚያመነጭ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

“የኮይሻና የሕዳሴ ግድቦች ሲጠናቀቁ አሁን ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት በ170% በማሳደግ በ2022 ሙሉ በሙሉ ለዜጎች ኃይል ለማቅረብ በምናደርገው ጥረት ላይ ትልቁን ሚና ይጫወታሉ” ማለታቸውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ዘግቧል።

በጉብኝቱ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ ተገኝተዋል።

መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ/ም