Ethiopian Educational Channel
6.57K subscribers
1.55K photos
40 videos
1.73K files
565 links
እንኳን ደና መጣችሁ
በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኙት
1. ትምህርታዊ መረጃ መስጠት
2.የሳይኮሎጂ አስተማሪ ምክሮችንና አነቃቂ ንግግሮች
3.መፃህፍቶች በpdf እና የእንግሊዝኛ ትምህርት ይለቀቃሉ!
በዚህ ቻናል ሀይማኖታዊ እና ፓለቲካ ነክ አይለቀቅበትም !
የቴሌግራሙ ቻናል ሊንክ:👉https://t.me/EEC1227
Channel created by @BA1227
Download Telegram
የትምህርት ቤት መሠረታዊ መምህራን ማህበር ተወካይ ዋና ተግባራት!

1. የመምህራንን መብትና ጥቅም መጠበቅ።

2. በመምህራንና በትምህርት ቤቱ አስተዳደር መካከል የመገናኛ ድልድይ ሆኖ መስራት።

3. የመምህራንን ችግሮችና ጥያቄዎች ሰብስቦ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ።

4. የማህበሩን ውሳኔዎችና መመሪያዎች ለአባላት ማስተላለፍ።

5. በማህበሩ ስብሰባዎች ላይ መምህራንን መወከል።

6. የመምህራን አንድነትና ትብብር እንዲጠናከር መስራት።

7. የሙያ ሥነ-ምግባር እንዲከበር ማበረታታት።

8. የሥራ ሁኔታን ለማሻሻል ሀሳቦችን ማቅረብ።

9. በማህበሩ የሚዘጋጁ ሥልጠናዎችና ፕሮግራሞች ላይ መምህራንን ማሳተፍ።

10. በትምህርት ቤቱ ኮሚቴዎች ውስጥ የመምህራንን ድምፅ ማስተላለፍ።

11. በመምህራን መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት ለመፍታት መርዳት።

12. የማህበሩን ዓመታዊ ዕቅድ እና እንቅስቃሴ በትምህርት ቤቱ ማስፈጸም።

13. አዳዲስ አባላትን ማስመዝገብና ማበረታታት።

14. የመምህራንን የሙያ እድገትና ቀጣይ ሙያዊ ልማት (CPD) መደገፍ።

15. ለመምህራን የሚመለከቱ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲታወቁ ማስተዋወቅ።

16. የማህበሩን ሰነዶችና መዝገቦች በአግባቡ መያዝ።

17. ከወረዳ ወይም ከከፍተኛ የመምህራን ማህበር መዋቅሮች ጋር ቅንጅት መፍጠር።

18. የአባላትን ምስጢራዊነትና ክብር መጠበቅ።

19. የማህበሩን ሪፖርቶች ማዘጋጀትና ማቅረብ።

20. የትምህርት ጥራት እንዲሻሻል ከመምህራን፣ ከአስተዳደሩና ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር መስራት።

21. የመምህራንን የሥራ ሁኔታ በመከታተል የሚታዩ ችግሮችን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ።

22. በትምህርት ቤቱ ውስጥ የመምህራን መብትና ግዴታ እንዲከበር ግንዛቤ መፍጠር።

23. በመምህራን ላይ የሚደረጉ የሙያ ግምገማዎች ፍትሃዊነት እንዲጠበቅ መከታተል።

24. በትምህርት ቤቱ የሚካሄዱ የልማት እና የማሻሻያ መርሃ ግብሮች ላይ የመምህራንን ተሳትፎ ማበረታታት።

25. ለመምህራን የሚያጋጥሙ የሥነ-ምግባር ወይም የሙያ ጉዳዮች በአግባቡ እንዲፈቱ መተባበር።

26. ከወላጅ ማህበር፣ ከተማሪ ተወካዮችና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የትምህርት ቤቱን እንቅስቃሴ መደገፍ።

27. የመምህራን የደህንነትና የሥራ አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ መፍጠርና መከታተል።

28. የማህበሩን የፋይናንስና የንብረት አጠቃቀም ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲጠበቅ መተባበር።

29. በአስፈላጊ ጊዜ የመምህራንን የውይይት፣ የምክክርና የልምድ ልውውጥ መድረኮች ማዘጋጀት።

30. የማህበሩን ዓላማ፣ ራዕይና ተልዕኮ በትምህርት ቤቱ ውስጥ በብቃት እንዲተገበሩ መስራት።

31. የመምህራንን ጥቅም ማስከበር እንደ የደረጃ ዕድገትና ስልጠናዎችን በፍትሀዊ መንገድ እንድከናወኑ ማድረግና መስራት፡፡

32. የመምህራንን የወር ደመወዝ ፔሮል በጊዜና በወቅቱ ተሰርቶ እንድላክ መጠየቅና ማድረግ፡፡
#ተማሪ_ተኮር_የማስተማሪያ_ስነ-ዘዴዎችና_ጥቅሞች

ተማሪ ተኮር ማስተማር ማለት የትምህርቱን ሂደት በመምህሩ ብቻ ከመመራት ይልቅ ተማሪዎች በመማር፣ በመጠየቅ፣ በመመርመርና በመሳተፍ ንቁ ሚና እንዲወስዱ ማድረግ ነው።

| የማስተማሪያ ስነ-ዘዴ | አጭር መግለጫ | ዋና ጥቅም |
|---|---|---|
| የቡድን ሥራ ተማሪዎች በትንንሽ ቡድኖች ተከፍለው ተግባር ይሠራሉ። ትብብርን፣ የመግባባት ችሎታንና የኃላፊነት ስሜትን ያዳብራል።

| ውይይትና ጥያቄ-መልስ መምህሩ ጥያቄ ያቀርባል፤ ተማሪዎች ሀሳባቸውን ይገልጻሉ። ማሰብን፣ መከራከርንና በራስ መተማመንን ያበረታታል።

| ችግር ፈቺ ማስተማር ተማሪዎች እውነተኛ ወይም ምናባዊ ችግር በመመርመር መፍትሔ ያፈላልጋሉ።

የትንተናና የውሳኔ ሰጪነት ችሎታን ያሳድጋል።

| የፕሮጀክት ሥራ
ተማሪዎች ለተወሰነ ጊዜ ጥናትና ተግባር በማካሄድ ውጤት ያቀርባሉ።
ምርምርን፣ ፈጠራንና የተግባር እውቀትን ያዳብራል።

| ምርመራ-ተኮር ማስተማር
ተማሪዎች ጥያቄ ያነሳሉ፣ መረጃ ይሰበስባሉና ውጤት ያገኛሉ።

የሳይንሳዊ አስተሳሰብንና ጉጉትን ያበረታታል።

| ተግባራዊ ማስተማር
ሙከራ፣ ሚና ጨዋታ፣ ማሳያ ወይም ላቦራቶሪ ሥራ ይካሄዳል።
ትምህርቱን የሚታይና የሚታወስ ያደርጋል።

| የአቻ ማስተማር | ተማሪዎች እርስ በርስ በማብራራትና በመርዳት ይማራሉ።
ግንዛቤን ያጠናክራል፤ የመሪነትና የመግለጽ ችሎታን ያዳብራል።

| የተለያዩ ደረጃዎችን የሚያሟላ ማስተማር

የተማሪዎችን ችሎታ፣ ፍጥነትና የመማሪያ ልዩነት በመ
ተግባራት ይዘጋጃሉ። | ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ያግዛል።

| ጨዋታና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ማስተማር

የትምህርት ጨዋታዎች፣ ቪዲዮዎች፣ ሞዴሎችና ዲጂታል መሣሪያዎች ይጠቀማሉ። | ተሳትፎንና ፍላጎትን ያሳድጋል፤ አስቸጋሪ ሀሳቦችን በቀላሉ ያብራራል።

### አጠቃላይ ጥቅሞች

1. ተማሪዎችን ንቁ ተሳታፊ ያደርጋል።
2. የመማር ፍላጎትንና ተነሳሽነትን ያድጋል።
3. በራስ መተማመንንና ራስን መምራትን ያጠናክራል።
4. የትብብር፣ የመግባባትና የመሪነት ችሎታዎችን ያዳብራል።
5. ተማሪዎች ዕውቀትን በመያዝ ብቻ ሳይሆን በተግባር እንዲጠቀሙበት ያደርጋል።
6. የተለያዩ የመማር ፍጥነትና ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች ያካትታል።
7. የችግር መፍታት፣ የፈጠራና የሂሳዊ አስተሳሰብ ችሎታን ያዳብራል።
8. መምህሩ የተማሪዎችን ግንዛቤ በቀጥታ እንዲገመግምና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሰጥ ያስችለዋል።

ማጠቃለያ፦ ተማሪ ተኮር ማስተማር ተማሪውን የትምህርት ተቀባይ ብቻ ሳይሆን የዕውቀት ፈጣሪና ንቁ ተሳታፊ ያደርገዋል። ወቅታዊ ፈጣን እና ትምህርታዊ መረጃ ሙሉ በሙሉ ለማግኜት
ለበለጠ መረጃ Telegram 👇👇👇https://t.me/EEC1227
❤3
አንዳንድ የበላይ አካላት(በተለምዶ የበላይ አካላት) መምህርን በአንደበታቸው ያወድሳሉ፤ በተግባራቸው ግን የሚገባውን ክብርና ድጋፍ ለመስጠት ሲመጣ ይረሱታል። ይህ የአመለካከት ችግር ብቻ ሳይሆን ለትምህርት ሥርዓትና ለትውልድ ዕጣ ፈንታ አደገኛ የሆነ አስተዳደራዊ ተቃርኖ ነው። መምህር በቂ ደመወዝ፣ ፍትሐዊ የሥራ ሁኔታ፣ ሙያዊ ነፃነትና ማህበራዊ ክብር ሳያገኝ የትምህርት ጥራትን በተሟላ ሁኔታ እንዲያረጋግጥ መጠበቅ ፍትሐዊ አይደለም። መምህር ለምን ይቀልጣል? አንተ አንተ በምቾት እየተዝናናህ፣ እሱ ለምን የሌሎችን ነገ ለማብራት የራሱን ዛሬ በችግር ውስጥ ያሳልፋል? ይህ ጥያቄ የግል ጥላቻ ሳይሆን የማህበራዊ ፍትሕና የኃላፊነት ጥያቄ ነው!
መምህር የሚገባው ክብር በምስጋና ንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባር መረጋገጥ አለበት። መምህር የሚያስተምረው ሌሎች ከፍ እንዲሉ ነው፤ እሱም በክብር እንዲኖር የሚያስችለው ሁኔታ መፈጠር አለበት። የመምህርን መስዋዕትነት እያወደሱ የኑሮ ችግሩን መተው፣ የሻማውን ብርሃን እየተጠቀሙ ሻማው እንዲቃጠል እንደመተው ነው። ስለዚህ የበላይ አካላት የመምህርን ተልዕኮ ከማወደስ ባለፈ ለሙያው የሚገባውን ዋጋ ሊሰጡት ይገባል። የተከበረ መምህር የተሻለ ትምህርትን ለመገንባት የተሻለ ዕድል አለው፤ የተከበረ ትምህርት ደግሞ የተሻለ ትውልድን ይፈጥራል። መምህር ለትውልድ ብርሃን ይሁን፤ ግን ያንን ብርሃን ለማብራት ሲል ሕይወቱን በችግር እንዲያቃጥል አንጠይቀው!
ጥቅምት 14/02/2019 ዓ.ም
✍️ በመንግሥቱ ስነፀሐይ ተፃፈ
❤3
🩺 ሐኪምን ማበረታታት ጤናን ማዳን ነው፤
📚 መምህርን ማበረታታት ግን ትውልድን መገንባት ነው!

የጤና ሚኒስቴር ለሐኪሞች ጥቅማ ጥቅም እና የዱዩቲ ክፍያ ለማስከበር ሲታገል፣ የትምህርት ሚኒስቴር ግን መምህራንን ከፈተና ወደ ፈተና እያሸጋገረ ይገኛል።

ሐኪም የዛሬን ሕይወት ይታደጋል፤ መምህር ደግሞ የነገን ትውልድ ይገነባል። ስለዚህ መምህራንን መፈተን ብቻ ሳይሆን፣ ማክበር፣ ማበረታታትና ጥቅማቸውን ማስከበርም ያስፈልጋል።

መምህርን የሚያከብር ሀገር፣ የወደፊቱን ትውልድ ያከብራል! 🇪🇹❤️ ሙያዊ መረጃን እና ዶክመንቶችን ለማግኜት 👇👇👇
https://t.me/EEC1227
ተማሪ ተኮር እና መምህር ተኮር አካሄዶች፦ ልዩነትና አንድነት

1. መምህር ተኮር (Teacher-Centered)

ትምህርቱ በመምህር ዙሪያ የሚሽከረከርበት አካሄድ ነው።

· መምህር የእውቀት ምንጭ፣ የክፍሉ ሥልጣንና ውሳኔ ሰጪ ነው።
· ተማሪ የሚያዳምጥ፣ የሚያስታውስና የሚደግም ተቀባይ ነው።
· ዘዴዎች፦ ሌክቸር፣ ማሳያ፣ የመምህር ማብራሪያ፣ አጠቃላይ ክፍል ትምህርት።
· ግምገማ፦ በፈተና፣ በውጤትና በደረጃ ላይ ያተኩራል።
· ጥንካሬ፦ ብዙ ይዘት በአጭር ጊዜ ማሸፈን፣ ትዕዛዝ ማስፈን፣ ለትልቅ ክፍል ተስማሚ።
· ድክመት፦ የተማሪ ንቁ ተሳትፎ፣ የፈጠራ አስተሳሰብና የትብብር ክህሎት ሊያንስ ይችላል።

2. ተማሪ ተኮር (Student-Centered)

ትምህርቱ በተማሪ ፍላጎት፣ ተሳትፎና ተሞክሮ ዙሪያ የሚያተኩርበት አካሄድ ነው።

· መምህር አመቻች፣ መንገድ አሳይና አስተባባሪ ነው።
· ተማሪ እውቀትን በንቃት የሚገነባ፣ የሚመረምርና የሚተባበር ነው።
· ዘዴዎች፦ ፕሮጀክት፣ የቡድን ሥራ፣ ውይይት፣ ችግር መፍታት፣ ጥያቄና መልስ፣ ተግባራዊ ልምምድ።
· ግምገማ፦ ቀጣይ ግምገማ፣ ፖርትፎሊዮ፣ ፕሮጀክት፣ ራስንና እኩዮችን መገምገም።
· ጥንካሬ፦ የተማሪ ተነሳሽነት፣ የፈጠራ አስተሳሰብ፣ ትብብር፣ የችግር መፍታት ክህሎት ያዳብራል።
· ድክመት፦ ጊዜ፣ ሀብትና የሰለጠነ መምህር ይፈልጋል፤ በትልቅ ክፍል ለመተግበር ይከብዳል።

3. ዋና ዋና ልዩነቶች

መስፈርት መምህር ተኮር ተማሪ ተኮር
ማዕከል መምህር ተማሪ
የመምህር ሚና አስተማሪ፣ ሥልጣን አመቻች፣ መንገድ አሳይ
የተማሪ ሚና ተቀባይ፣ አዳምጥ ንቁ ተሳታፊ፣ ገንቢ
የእውቀት ምንጭ መምህርና መጽሐፍ ተማሪ፣ ተሞክሮ፣ ማህበረሰብ
የማስተማር ዘዴ ሌክቸር፣ ማሳያ ፕሮጀክት፣ ውይይት፣ ቡድን
ስርዓተ ትምህርት ቋሚ፣ ማዕከላዊ ተለዋዋጭ፣ ከፍላጎት ጋር የሚስማማ
ግምገማ ድምር፣ ፈተና ቀጣይ፣ ፖርትፎሊዮ
ተነሳሽነት ውጫዊ ውስጣዊ
የክፍል አየር ጸጥተኛ፣ በሥርዓት ተሳታፊ፣ ትብብራዊ

4. አንድነት / የሚያመሳስላቸው

· ሁለቱም የትምህርት ሂደት ናቸው፤ ዓላማቸው የተማሪን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ማሻሻል ነው።
· በሁለቱም ውስጥ መምህር ያስፈልጋል፤ ልዩነቱ በሚጫወተው ሚና ላይ ነው።
· ሁለቱም ግልጽ ዓላማ፣ የተዘጋጀ ይዘት፣ የማስተማሪያ ዘዴና ግምገማ ይፈልጋሉ።
· ሁለቱም የተማሪን ፍላጎት፣ ዕድሜ፣ የመማር ፍጥነትና ልዩነት ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
· ሁለቱም ደህንነቱ የተጠበቀ የመማር አካባቢ፣ ግብረመልስና ክትትል ይፈልጋሉ።
· በተግባር ሊዋሃዱ ይችላሉ። ለምሳሌ፦ መምህር መሠረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ አስተምሮ፣ ተማሪዎች በቡድን ፕሮጀክት ሲሠሩ ሁለቱም አካሄዶች ይጣመራሉ።
· ውጤታማ ትምህርት ሁለቱን በማጣመር የመምህርን መመሪያና የተማሪን ንቁ ተሳትፎ ሚዛናዊ ማድረግ ነው።

5. ማጠቃለያ

ተማሪ ተኮርና መምህር ተኮር ፍጹም ተቃራኒ አይደሉም። በተከታታይ የሚገኙ አካሄዶች ናቸው። ምርጫው በትምህርት ዓላማ፣ በተማሪ ዕድሜ፣ በክፍል መጠን፣ በሀብትና በመምህር ክህሎት ይወሰናል። ምርጥ አስተምህሮ የሁለቱን ጥቅም በማጣመር የተማሪን አቅም ማሳደግ ነው።
🏫የትምህርት ቤት ወላጅ–መምህራን ህብረት (ወመህ) ተግባርና ሀላፊነት❕🥰

የወላጅ–መምህራን ህብረት በትምህርት ቤት ውስጥ የተማሪዎችን ትምህርት፣ ስነ-ምግባር እና ደህንነት ለማሻሻል ወላጆችና መምህራን ጋር በጋራ የሚሰራ ዋና የህብረት አካል ነው።

📝 የወመህ ዋና ዋና ተግርና ሀላፊነት፦

1. የተማሪ ችግር መፍታት ላይ ተሳትፎ
የተማሪዎች የባህሪና የስነምግባር ችግር በጋራ መወያየትና መፍታት።

2. የተማሪዎች ስነ-ምግባርና ደህንነት
በት/ቤቱ ውስጥ የተማሪዎች ስነ-ምግባር እንዲሻሻል፣ ዲሲፕሊን እና ደህንነት እንዲጠናከር መደገፍ።

3. የት/ቤት–ወላጅ ግንኙነት ማጠናከር
መደበኛ ስብሰባዎችን መዘጋጀት፣ መረጃ መለዋወጥ እና ግንኙነት ማሻሻል።

4. የት/ቤት አስተዳደር መደገፍ
ከዳይሬክተርና ከአስተዳደር ጋር በመተባበር የት/ቤቱን እቅድ እና የስራ አፈጻጸም መደገፍ።

5. የፋይናንስና የንብረት ድጋፍ
በህጋዊ መንገድ ገንዘብ መሰብሰብ፣ የት/ቤት መሠረተ ልማቶችን ማሻሻል (ክፍሎች፣ መጻሕፍት ቤት ወዘተ)።

6. የትምህርት ጥራት ማሻሻል
የትምህርት ሂደትን መደገፍና የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ከት/ቤቱና ከመምህራን ጋር መስራት።

7. የህግና የስነ-ምግባር ክብር
የትምህርት ህጎችንና ደንቦችን ማክበር።

8. ማህበረሰብ ተሳትፎ ማበረታታት
ከአካባቢ ማህበረሰብ እና ሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር ት/ቤቱን መደገፍ።

9. የተማሪ ድጋፍና ማበረታቻ
ደካማ ተማሪዎችን መርዳት፤ ተሸላሚ ተማሪዎችን ማበረታታት።
❤3
Words That Begin with Capital Letters in Any Place!

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ቃላትን በዓረፍተ ነገር መጀመሪያ፣ መካከል ወይም መጨረሻ ቢመጡም የመጀመሪያ ፊደላቸውን Capital Letter (Uppercase Letter) አድርገን እንፅፋለን፡፡

በየትኛውም ቦታ የመጀመሪያ ፊደላቸው Capital Letter የሚሆኑ የእንግሊዝኛ ቃላት ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦

1. The first word of every sentence - የዓረፍተ ነገር መጀመሪያ ቃል

Any sentence begins in a capital letter or any new sentence begins in a capital letter

ማንኛውም የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር የመጀመሪያ ቃል በCapital Letter ይጀምራል።

Example፡

The boy is reading.
She is a student.
We are learning English.

2. Names of People

Example፡

Abebe
Kebede

ምሳሌ፦

My friend Abebe is a teacher.
I met Abebe yesterday.
I gave the book to Abebe.

3. Names of Countries

Ethiopia
Kenya
Uganda
United States

ምሳሌ፦

Ethiopia is in Africa.
I live in Ethiopia.
She travelled to Ethiopia.

4. Names of Cities and Towns

Addis Ababa
Bahir Dar
Gondar
Dessie
Debre Markos

5. Names of Continents

Africa
Asia
Europe
North America
South America
Antarctica
Australia

ምሳሌ፦ Ethiopia is in Africa.

6. Names of Languages (የቋንቋዎች ስሞች)

English — እንግሊዝኛ
Amharic — አማርኛ
Afaan Oromo — አፋን ኦሮሞ
Tigrinya — ትግርኛ
Somali — ሶማሊኛ
Arabic — አረብኛ
French — ፈረንሳይኛ

ምሳሌ፦

I speak English.
She is learning Amharic.

7. Nationalities and People from Countries

Ethiopian
Kenyan
Ugandan
Nigerian

ምሳሌ፦ He is an Ethiopian.

8. Days of the Week (የሳምንቱ ቀናት)

Monday
Tuesday
Wednesday
Thursday
Friday
Saturday
Sunday

ምሳሌ፦

I go to school on Monday.
We met on Sunday.

9. Months of the Year (የዓመቱ ወራት)

January
February
March

ምሳሌ፦

My birthday is in October.
The school opened in September.

10. Names of Religions

Christianity — ክርስትና
Islam — እስልምና
Judaism — አይሁድነት
Buddhism — ቡድሂዝም
Hinduism — ሂንዱዝም

11. Names of Holy Books

The Bible
The Quran
The Torah

12. Names of Organizations and Institutions (የድርጅቶችና ተቋማት ስሞች)

United Nations (UN)
African Union (AU)
World Health Organization (WHO)
Ethiopian Airlines
Ministry of Education
British Embassy
French Embassy

13. Names of Schools, Hospitals Hotels and Universities

University of Hondar
Oxford University
Bahir Dar University
Addis Ababa University
Terara High School
Bonga College
Nuritu Hotel

ለምሳሌ፦ college, university, hospital, hotel እና school የሚሉት የተቋሙ ስሞ ካልተጨመረ በዓረፍተ ነገር መካከል ሲመጡ small letter ይጀምራሉ። የተቋሙ ስም ከተጨመረ ግን capital leter ይሆናሉ፡፡

Example፡

* university እና Bonga University
* hotel እና Selam Hotel
* hospital እና Agere Hospital

14. Names of Streets and Roads

Churchill Avenue
Bole Road
Wall Street
Main Street
King’s Road

14. Names of Mountains (የተራሮች ስሞች)

Mount Everest
Mount Kilimanjaro
Ras Dashen
Simien Mountains
Bale Mountains

አስታውሱ፡

mountain የሚለው የ"sea" ስሞ ካልተጨመረ በዓረፍተ ነገር መካከል ሲመጡ small letter ይጀምራሉ። የ"mountain" ስሞ ከተጨመረ ግን capital leter ይሆናሉ

Example፡

mountain እና Bale Mountain

15. Names of Rivers (የወንዞች ስሞች)

Blue Nile
Awash River
Omo River
Tekeze River
Amazon River
Nile River
Congo River
Zambezi River
Mississippi River

አስታውሱ፦

river የሚለው የ"sea" ስሞ ካልተጨመረ በዓረፍተ ነገር መካከል ሲመጡ small letter ይጀምራሉ። የ"river" ስሞ ከተጨመረ ግን capital leter ይሆናሉ፡፡

Example፡

river እና Awash River

16. Names of Oceans and Seas (የውቅያኖሶችና ባሕሮች ስሞች)

Pacific Ocean
Atlantic Ocean
Indian Ocean
Arctic Ocean
Red Sea
Mediterranean Sea
Arabian Sea
Dead Sea

አስታውሱ፦

sea እና ocean የሚሉት የ"sea እና ocean" ስሞ ካልተጨመረ በዓረፍተ ነገር መካከል ሲመጡ small letter ይጀምራሉ። የ"sea እና ocean" ስሞ ከተጨመረ ግን capital leter ይሆናሉ፡፡

Example፡

* sea እና Mediterranean Sea

* arctic እና Arctic Ocean

17. Names of Planets (የፕላኔቶች ስሞች)

Mercury
Venus
Earth
Mars
Jupiter
Saturn
Uranus
Neptune

ምሳሌ፦ The Earth moves around the Sun.

18. Names of Historical Events (የታሪካዊ ክስተቶች ስሞች)

World War I
The French Revolution
The American Revolution
The Industrial Revolution
The Battle of Adwa
The Ethiopian Revolution

19. Names of Festivals and Holidays (የበዓላት ስሞች)

Christmas
Easter
Eid al-Fitr
Eid al-Adha
New Year
Independence Day

20. Names of Languages' Literary Works, Books and Movies (የመጻሕፍትና የፊልሞች ስሞች)

The Bible
Animal Farm
Things Fall Apart
The Old Man and the Sea
Romeo and Juliet
The Lord of the Rings
❤2
21. Names of Government Offices and Positions (የመንግሥት ተቋማትና የሥራ መደቦች ስሞች)

President
Prime Minister
Minister
Director
Principal
Professor
Doctor
Captain

ምሳሌ፦

President Abraham Lincoln was an American leader.

The president gave a speech.

አስታውሱ፦

በመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር President ከስም በፊት ተጠቅሟል። በሁለተኛው ዓረፍተ ነገር president ስም ስላልተከተለው አጠቃላይ የሥራ መደብ ስለሆነ በትክክለኛው የዓረፍተ ነገር አጻጻፍ መሠረት በsmall letter ተጽፏል።

22. Pronoun "I" (የእንግሊዝኛው የመጀመሪያ መደብ ተውላጠ ስም)

I = እኔ

የእንግሊዝኛው ተውላጠ ስም I በየትኛውም ቦታ ቢመጣ ሁልጊዜ Capital Letter ይሆናል።

ምሳሌዎች፦

I am a teacher.
She gave me a book because I needed it.
The teacher asked me whether I was ready.

23. Names of Political Parties

ምሳሌዎች፦

Prosperity Party
Democratic Party
Republican Party

24. Names of Companies and Brands

Toyota
Coca-Cola
Tecno
Ethiopian Airlines
Safaricom
Ethio Telecom

25. Names of Nationalities, Ethnic Groups and Tribes (የብሔርና የሕዝብ መጠሪያዎች)

Amhara — አማራ
Oromo — ኦሮሞ
Tigrayan — ትግራዋይ
❤1
የመምህራን ክብር ወደ ቀድሞው ማንነቱ ይመለስ
የቤት ኪራይ በቅራሽ ዋጋ በመንግስት ቤት ተሰጥቶት ይከራይ፤ ደሞዝ ይጨምር ግብር ይቀንስ ህክምና በነፃ ይሁን‼

👉30ዓመት ካስተማረው መምህር ይልቅ 3 አመት የሰራው አመራር የተሸለ ኑሮ በሚኖርበት ስለ ትምህርት ጥራት ማውራት ፌዝ ነው የሚመስለኝ። መምህራን በኑሮ ውድነት አለንጋ አየተገራፉ ስለ ትምህርት ጥራት?
👉ሦስት ወር የሰሩት አመራሮችቤት ሲኖራቸው 30 ዓመት የስራው  መምህር የሱን ቤት ተከራይቶ እየኖረ ያለባት ሀገር ላይ እየኖርን ስለትምህርት ጥራት ማውራት ምን ዋጋ ይኖራል
👉መምህራን በረሃብ አንጀቱን ይዞ ተማሪ ፊት የመቆም ግዴታ የለበትም!!
👉በአፍ ሽንገላ ወይም ማስመሰል ይቅር
የመምህራን መብትና ጥቅማጥቅማቸዉ ይከበር🙌
እውነተኛ የትም/ት ጥራት እንዲመጣና የመ/ራንን ሙያ ለማጎልበት ከተፈለገ መ/ራንን በየጊዜው የሙያ ማጎልበቻ ስልጠና እና የትምህርት ዕድል ሊሰጥ  ይገባል፡⁈
❤16👍6👏2
<<ተማር ልጄ ላልተማረ ሰው ቀኑ ጨለማ ነው>> ተብለን ተምረን አሁን ለተማረ ሰው ቀኑ ጨልሟል !!
ሀገራችን ችግር ውስጥ ናት። የሚሉ የመደለያ የሽንገላ ቃላት ይቁም !!
ሰበብ አያስፈልግም እኛ መምህራን የጦርነት መንስኤ አይደለነም።
👍10❤2
የፈተና ቢጋር አዘገጃጀት.pdf
394.6 KB
የፈተና ቢጋር (Table of Specifications /TOS) አዘገጃጀትን በሚመለከት ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እንደ guideline የሚሆን፣ ለመረዳት ግልፅ የሆነ፣ በምሳሌ የተደገፈ በpdf የተዘጋጀ ሰነድ
👉https://t.me/EEC1227
❤8
action_research_proposal_መካተት_ያለባቸው_ዝርዝሮች.doc
25.5 KB
👉 ፕሮፖዛል ስትሰሩ ከላይ በተላከላችሁ የፕሮፖዛል ቅደም ተከተል አሰራር ተከትላችሁ እንድትሰሩ
👉 ፕሮፖዛል የሚይዘው እስከ ምዕራፍ 3 ብቻ ነው ። ምዕራፍ 4 እና 5  በዋናው ተግባራዊ ጥናት ላይ ነው የሚካተተው።
​"መጽሐፍ ማንበብ ማለት የሌላ ሰውን አእምሮ በነፃ መዋስ ነው⏰
​
አንድ መጽሐፍ ስታነብ ደራሲው በብዙ ዓመታት ልምድ፣ ስህተትና ምርምር ያገኘውን ዕውቀት አንተ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ትወስደዋለህ።


​ንባብ አእምሮን ያበራል
​አስተሳሰብን ያሰፋል
​የቃላት አጠቃቀምን ያዳብራል
​ቀንህ በዕውቀትና በስኬት የተሞላ ይሁን
​ማንበብን የዘወትር ባህላችን እንድርግ
አሳዛኝ መረጃ‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ሀይቅ ከተማ ጃሪ ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች ካምፕ መጠለያ ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት ንፁሃን ሰዎች እንደሞቱ እና እንደተጎዱ ከነዋሪዎች የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል።
ከጥቃቱ በኋላ ወደ ካምፑ ሄጄ ነበር ያሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ 12 ሰዎች መሞታቸውን አይቻለሁ ያሉ ሲሆን የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። የተጎዱ ብዙ ናቸው ብለዋል። ጥቃቱ አሳዛኝ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ምንጨ: አዩዘሀበሻ
😭😭😭ፈጣሪ ሆይ አላዋቂዎች የንፁሃን ደም እያፈሰሱ ነውና ተመልከተን
😭5❤1
ምርጥና ተወዳጅ መምህራን መለያ ባህሪዎች

1•ትዕግስተኛ መሆንና ለተማሪዎች ክብር መስጠት – ተማሪዎች
በተለያየ ፍጥነት እንደሚማሩ መረዳትና ማክበር።

2. ጥሩ የማስተማር ችሎታ – አስቸጋሪ ነገርን በቀላል መንገድ ማስረዳት።

3. የትምህርት ዝግጅት – ከክፍል በፊት ትምህርቱን በደንብ ማቀድ።

4. ተማሪን ማዳመጥ – የተማሪውን ጥያቄና ችግር በትኩረት ማዳመጥ።

5. ጥሩ ግንኙነት – ከተማሪዎች ጋር ክብርን የተመሠረተ ግንኙነት መፍጠር።

6. ተማሪን ማበረታታት – “አትችልም” ከማለት ይልቅ “እንደገና ሞክር” ማለት።

7. ፍትሃዊነት – ሁሉንም ተማሪዎች ያለ አድልዎ መመልከት።

8. ጥሩ የጊዜ አጠቃቀም – የትምህርት ጊዜን በአግባቡ መጠቀም።

9. ግልጽ አቀራረብ – መመሪያና ማብራሪያዎችን ግልጽ ማድረግ።

10. የተማሪን ልዩነት መረዳት – ተማሪዎች በችሎታ፣ በፍጥነትና በፍላጎት እንደሚለያዩ መገንዘብ።

11. የተማሪን እድገት መከታተል – የተማሪውን ውጤት በተደጋጋሚ መገምገም።

12. ጥሩ ምሳሌ መሆን – በባህሪ፣ በንግግርና በሥራ ለተማሪዎች አርአያ መሆን።

13. ፈጠራ መኖር – ተማሪዎችን የሚያሳትፉ የተለያዩ የማስተማሪያ ዘዴዎችን መጠቀም።

14. ቀጣይነት ያለው መማር – መምህሩም ራሱን በየጊዜው ማሻሻልና አዳዲስ እውቀቶችን መማር።

15. ፍቅርና ኃላፊነት – ለሙያውና ለተማሪዎቹ ቁርጠኛ መሆን።

በአጠቃላይ
> ብቁ መምህር ማለት ትምህርትን ብቻ የሚያስተምር ሳይሆን፣ ተማሪው እንዲያስብ፣ እንዲሞክርና በራሱ እንዲተማመን የሚያግዝ መምህር ነው።
❤3
📚 #ለሁሉም_መምህራን_ሊደርስ_የሚገባው_አስፈላጊ_የሙያ_ግንዛቤ!

         ➽ #CPD_ምንድ_ነው? እንዴት ይጠናል? ለምንስ ያስፈልጋል?

   ➽ብዙ መምህራን #CPD የሚለውን ቃል ያውቃሉ። በስብሰባ ይሰማሉ፣ በዕቅድ ውስጥ ያዩታል፣ በፖርትፎሊዮ ውስጥም ይመዘግባሉ። ግን CPD በትክክል ምን እንደሆነ፣ እንዴት መጠናት እንዳለበትና ከዕለት ተዕለት የማስተማር ሥራ ጋር ያለው ግንኙነት ምን እንደሆነ በበቂ ሁኔታ ለመረዳት የሚቸገሩ መምህራን አሉ።

        ➳ይህ ጽሑፍ ለዚህ ግንዛቤ ክፍተት #መፍትሔ ይሆናል በሚል ተስፋ ቀርቧል።

      1. #CPD_ምንድን_ነው?

➳ CPD የሚለው ምህፃረ ቃል #Continuous_Professional_Development ነው። በአማርኛ ቀጣይነት ያለው ሙያዊ ልማት ማለት ነው።

     ➽#በቀላሉ_ሲተረጎም፦

➳ CPD ማለት አንድ መምህር በሙያው የተሻለ ዕውቀት፣ ክህሎት፣ አመለካከትና የማስተማር ብቃት እንዲኖረው በቀጣይነት የሚያደርገው የመማር፣ የራስን የመገምገም፣ የምርምርና የተግባር ሂደት ነው።

    ➽ ማለትም  መምህር ዛሬ የሚያስተምረውን ነገ በተሻለ ዘዴ፣ በተሻለ ዕውቀትና በተሻለ ብቃት ለማስተማር የሚያደርገው ቀጣይ ሙያዊ ጥረት ነው።

    ➽ አንድ   መምህር የተሻለ መምህር ለመሆን ከተማረበት ዕውቀት ብቻ መመካት የለበትም፤ በየጊዜው መማርና ራሱን ማሻሻል አለበት።

      2. #CPD_ለምን_ያስፈልጋል?

➽ CPD የሚያስፈልገው የመምህሩን ፋይል ለማሳመር ወይም የሥልጠና መረጃ ለመሙላት ብቻ አይደለም። ዋና ዓላማው የትምህርትና የመማር ጥራትን ማሻሻል ነው።

        #ዋና_ጠቀሜታው ፦

    1. የመምህሩን የሙያ ዕውቀትና ክህሎት ያሳድጋል።
     2. አዳዲስ የማስተማር ዘዴዎችን ለመተግበር ያስችላል።
     3. በክፍል ውስጥ ያሉ የመማርና የማስተማር ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል።
     4. የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ለማሻሻል ያግዛል።
      5. ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርትና ከብቃት ተኮር ትምህርት ጋር ለመላመድ ያስችላል።
      6. የመምህራንን የትብብርና የቡድን ሥራ ባህል ያዳብራል።
      7. በሙያዊ ሥነ-ምግባርና በራስ መተማመን እንዲያድጉ ይረዳል።

3. #CPD_እንዴት_መጠናት_አለበት?

➽ CPD በተደራጀና በተከታታይ ሂደት መከናወን አለበት። የሚከተሉት ዋና ዋና ደረጃዎች ናቸው።

#ደረጃ 1፦ #የራስን_የሙያ_ክፍተት_መለየት (Self-Assessment)

መምህሩ በመጀመሪያ ራሱን መገምገም አለበት።

ለምሳሌ፦

- የተማሪዎችን ተሳትፎ በትክክል ማሳደግ እችላለሁ?
- የተለያዩ የማስተማር ዘዴዎችን እጠቀማለሁ?
- ቀጣይነት ያለውን ምዘና በትክክል እተገብራለሁ?
- የተማሪዎችን የመማር ችግር በተግባር መለየት እችላለሁ?

#ደረጃ 2፦ #የCPD_ዕቅድ_ማዘጋጀት (Planning)

ከራስ ግምገማ በኋላ የተለዩትን ክፍተቶች ለመሙላት የግል CPD ዕቅድ ማዘጋጀት አለበት።

➽ #ዕቅዱ_የሚከተሉትን_መያዝ ይገባል፦

- የሚጠናው ርዕስ፤
- የጥናቱ ዓላማ፤
- የሚከናወንበት ጊዜ፤
- የጥናቱ ዘዴ፤
- የሚጠበቀው ውጤት።

#ደረጃ 3፦ #ጥናቱን_ማከናወን (Implementation)

በዚህ ደረጃ መምህሩ የመረጠውን ርዕስ በራሱ ወይም ከሌሎች መምህራን ጋር በመተባበር ያጠናል።

➽ #የጥናት_ዘዴዎች፦

- የግል ንባብና ራስን ማስተማር (Self-learning)።
- በቡድን ውይይት (Group Discussion)።
- ከሌሎች መምህራን መማር (Peer Learning)።
- የሌላ መምህርን የማስተማር ሂደት መመልከት (Classroom Observation)።
- የሙያ ሥልጠና (Training)።
- በተግባር ምርምር ማድረግ (Action Research)።

#ደረጃ 4፦ #የተማሩትን_በክፍል_ውስጥ_መተግበር (Application)

ይህ የCPD ዋና ልብ ነው!

ለምሳሌ፦ መምህሩ በተማሪ ተኮር የማስተማር ዘዴ (Student-Centered Learning) ላይ ካጠና፣ በቀጣይ የክፍል ትምህርቱ ውስጥ የቡድን ሥራ፣ የጥያቄና መልስ ዘዴ፣ የችግር ፈቺ ተግባራትን በመጠቀም የተማረውን መተግበር አለበት።

ደረጃ 5፦ ውጤትን መገምገምና ማስተካከል (Reflection and Evaluation)

- የተማርኩት ምን ለውጥ አመጣ?
- የተማሪዎች ተሳትፎ ጨምሯል?
- የትምህርት ውጤት ተሻሽሏል?
- ምን ችግር አጋጠመኝ?
- በቀጣይ ምን ማሻሻል አለብኝ?

በእነዚህ ጥያቄዎች ራሱን መገምገም አለበት።

            4. #በዓመት_ስንት_ሰዓትCPD_መጠናት_አለበት?

ይህ ብዙ መምህራን ግልጽ መረጃ ሊኖራቸው የሚገባው ጉዳይ ነው።

በኢትዮጵያ የመምህራን CPD ማዕቀፍ እና በተግባር የሚጠቀሰው መመዘኛ መሠረት፣ ለመደበኛ CPD ተሳትፎ የሚጠበቀው፦

በዓመት ቢያንስ 60 ሰዓት ነው።

ይህ ማለት መምህሩ በዓመት 60 ሰዓት በተደራጀ የሙያ ልማት ተግባር መሳተፍ አለበት ማለት ነው።

ለምሳሌ፦

- በወር 5 ሰዓት፤
- በ12 ወራት 60 ሰዓት።

#የ60 ሰዓቱ አደረጃጀት በትምህርት ቤቱ ዓመታዊ ዕቅድና በመምህሩ የግል CPD ፍላጎት መሠረት ሊለያይ ይችላል።

ማሳሰቢያ፦ አዲስ የተቀጠሩ መምህራን የInduction ፕሮግራም የሚመለከታቸው የተለየ የመጀመሪያ ደረጃ ሂደት አላቸው። በትምህርት ቢሮው ወይም በትምህርት ቤቱ የሚተገበረውን ወቅታዊ መመሪያ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

            5. #CPD_ላይ_የሚጠኑ_ዋና ዋና ርዕሶች

መምህራን እንደ ሙያዊ ፍላጎታቸውና እንደ ትምህርት ቤታቸው ቅድሚያ የሚከተሉትን ርዕሶች ሊያጠኑ ይችላሉ።

1. Student-Centered Teaching Methods – ተማሪ ተኮር የማስተማር ዘዴዎች።
2. Active Learning – ንቁ የመማር ዘዴዎች።
3. Continuous Assessment – ቀጣይነት ያለው ምዘና።
4. Classroom Management – የክፍል አስተዳደር።
5. Inclusive Education – አካታች ትምህርት።
6. Competency-Based Education – ብቃት ተኮር ትምህርት።
7. Action Research – ተግባራዊ ምርምር።
8. Educational Technology – የትምህርት ቴክኖሎጂ።
9. Professional Ethics – ሙያዊ ሥነ-ምግባር።
10. Assessment and Feedback – ምዘናና ገንቢ አስተያየት።

         6. #የCPD_Portfolio_ምንድን ነው?

P1ortfolio ማለት መምህሩ በዓመቱ ውስጥ ያደረጋቸውን የሙያ ልማት ተግባራትና ያገኛቸውን ውጤቶች በማስረጃ የሚያስቀምጥበት የሥራ ማህደር ነው።

በውስጡ ሊካተቱ የሚገቡት፦

- የግል የCPD ዕቅድ።
- የራስ ግምገማ።
- የጥናት ማስታወሻዎች።
- የቡድን ውይይት ሪፖርቶች።
- የሥልጠና ማስረጃዎች።
- የክፍል ውስጥ የተግባር ማስረጃዎች።
- የAction Research ውጤት።
- የራስ ግምገማና የማሻሻያ ሪፖርት።

#አስፈላጊ፦ Portfolio ማለት ወረቀት በማከማቸት ብቻ የሚሞላ ፋይል አይደለም። የመምህሩን የእውነተኛ ሙያዊ ዕድገትና የተግባር ለውጥ ማሳየት አለበት።

             7. #አንድ_አስፈላጊ_መልዕክት_ለመምህራን

CPD ማለት የትምህርት ቤቱን አመራር ለማስደሰት፣ የወረቀት ሥራ ለመሙላት፣ ወይም ለቁጥጥር ብቻ የሚደረግ ተግባር መሆን የለበትም።

እውነተኛ CPD በመምህሩ የማስተማር ችሎታ፣ በተማሪዎች ተሳትፎ፣ በትምህርት ውጤትና በክፍል ውስጥ በሚታይ ለውጥ መለካት አለበት።
❤1
#የCPD_ዋና ጥያቄ፦

ዘንድሮ ምን አጠናሁ? ምን አዲስ ነገር ተማርኩ? በክፍሌ ውስጥ ምን ቀየርኩ? የተማሪዎቼ የመማር ውጤትስ ምን ያህል ተሻሻለ?

ይህን መመለስ ካልቻልን የCPD ዓላማችንን እንደገና መመርመር ይገባናል።

የተማረ መምህር የተሻለ ተማሪን ያፈራል፤ በቀጣይነት የሚማር መምህር ደግሞ በቀጣይነት የሚሻሻል ትምህርትን ይፈጥራል።

📢 #ለሁሉም_መምህራን፦ CPD እንደ ግዴታ ብቻ ሳይሆን እንደ ሙያዊ ዕድገትና ራስን የማሻሻል እድል እንመልከተው!
👍1
1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም_2.pdf
366.9 KB
የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018

ሌሎች ተጨማሪ ልዩ ልዩ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ሼር በማድረግ  በቀላሉ ያግኙ።
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/EEC1227
🚨 #የትምህርት_ዘርፉን_ማዳን_ከፈለግን፣ #መጀመሪያ_መምህሩን_ከኑሮ_ቀውስ_ማዳን_አለብን!

🖋 #የትምህርት ጥራት በየዓመቱ በሚወጡ #መመሪያዎች፣ በሚዘጋጁ #ስብሰባዎች፣ በሚታተሙ #የስልጠና_ሰነዶችና በሚነገሩ ባዶ #መፈክሮች ብቻ አይመጣም!

➽ #መምህሩ በረሃብ እየተሰቃየ፣ በኪራይ እየተጨነቀ፣ በዕዳ እየተዋጠና የቤተሰቡን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላት እያቃተው ለተማሪዎቹ የላቀ የትምህርት ጥራት እንዲያመጣ መጠበቅ ከእውነታው የራቀ ጥያቄ ነው!

➽ #የሚገርመው ደግሞ መምህሩ ተማሪውን ስለ ሀገር ልማት፣ ስለ ታማኝነት፣ ስለ ታታሪነትና ስለ ብልጽግና እንዲያስተምር ይጠበቅበታል፤ ነገር ግን ራሱ በድህነት፣ በኑሮ ውድነትና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዲኖር ይገደዳል።

➽ ይህ ብቻ ሳይሆን፣ መምህሩ በየቀኑ የሚያስተምረው የሀገር የወደፊት ተስፋ ሲሆን፣ የራሱ የወደፊት ተስፋ ግን በኑሮ ጫና እየተደበደበ ነው።

➽ይህን ተቃርኖ ሳንፈታ የትምህርት ለውጥ ማምጣት እንዴት ይቻላል?

#እውነቱን_በግልጽ_እንናገር፦

➽ 🔴 #የመምህር ደመወዝ ከኑሮ ውድነት ጋር መጣጣም አለበት!

➽ 🔴 #መምህር በደመወዙ ቤተሰቡን ማስተዳደር፣ ቤት መከራየት፣ ምግብ መግዛትና የልጆቹን ትምህርት መሸፈን መቻል አለበት!

➽ 🔴 #የመምህራን ሙያዊ ክብር፣ ማበረታቻ፣ የሙያ ዕድገትና የሥራ ሁኔታ በተግባር መሻሻል አለበት!

➽ 🔴 #መምህርን በግዴታና በተጨማሪ ጫና ሳይሆን በክብር፣ በፍትሐዊ አያያዝና በተገቢ ድጋፍ ማበረታታት አለበት!

➽ አንዱ ትልቅ እውነት ልንረዳ ይገባል፤ የተራበን መምህር በስልጠና ብቻ፣ የተጨነቀን መምህር በስብሰባ ብቻ፣ ተስፋ የቆረጠን መምህር በመፈክር ብቻ ማነቃቃት አይቻልም!

➽ የትምህርት ስርዓት ማለት ሕንፃ፣ መጽሐፍ፣ መመሪያና የትምህርት ፕሮግራም ብቻ አይደለም። ከሁሉም በላይ ሰው ነው፤ ያንን ሰው የሚያንቀሳቅሰው ደግሞ #መምህር ነው!

#ስለዚህ_የትምህርት ለውጥ ከመምህሩ ኑሮ ለውጥ ይጀምር!

➽ መምህሩን ሳናከብር ትምህርትን ማክበር አንችልም።
➽ መምህሩን ሳናበረታታ የተማሪን ውጤት ማሻሻል አንችልም። ➽ መምህሩን ከድህነት ሳናወጣ የትምህርት ዘርፉን ከቀውስ ማውጣት አንችልም!

#መምህር የሀገር ግንባታ መሠረት ከሆነ፣ የመምህር ኑሮ የሀገር ቅድሚያ ጉዳይ መሆን አለበት!

✊ #የመምህር_ኑሮ_ይሻሻል! ✊ #የመምህር_ክብር_ይመለስ! ✊ የትምህርት ጥራት በተግባር ይገንባ!

📢 ➽ #ይህ የአንድ መምህር ጥያቄ ብቻ አይደለም፤ የትምህርት ዘርፉ የወደፊት እጣ ፈንታ ጥያቄ ነው!
የጠንካራ አመራር መገለጫዎች!

የማዳመጥ ችሎታ ያለው — የሚመራቸውን ሰዎች ሐሳብና ቅሬታ ያዳምጣል።

ግልጽ ራዕይ ያለው — የሚመራው ተቋም የት መድረስ እንዳለበት ያውቃል።

ቆራጥ የሆነ — ከተገቢው መረጃ በመነሳት በጊዜው ውሳኔ ይሰጣል።

ተጠያቂነትን የሚቀበል — ለራሱ ውሳኔና ተግባር ኃላፊነት ይወስዳል።

በሕግ የሚመራ — የግል ፍላጎቱን ሳይሆን ሕግንና ደንብን ያከብራል።

ፍትሐዊ የሆነ — ሰዎችን ያለ አድልዎ ያስተናግዳል።

እውነተኛ የሆነ — እውነትን ይናገራል፤ ሐሰትንና ማታለልን ይቃወማል።

ችግር ፈቺ የሆነ — ችግሮችን በማወቅ ዘላቂ መፍትሔ ይፈልጋል።

የሰው ኃይል አልሚ የሆነ — የሠራተኞችን እውቀትና ክህሎት ያሳድጋል።

በተግባር የሚመራ — ከማውራት ይልቅ በሥራ ያሳያል።
ታታሪ የሆነ — ለተቋሙ ዓላማ በትጋት ይሠራል።

ጊዜን በአግባቡ የሚጠቀም — ሥራዎችን በቅደም ተከተል ያከናውናል።

ግልጽነትን የሚያስፋፋ — የሥራ ሂደቶችንና ውሳኔዎችን ግልጽ ያደርጋል።

ሙስናን የሚቃወም — ሥልጣኑንና የሕዝብ ሀብትን ለግል ጥቅም አይጠቀምም።

የሌሎችን ሐሳብ የሚቀበል — ከተለያዩ ሰዎች ልምድና እውቀት ይማራል።

ተግባቢ የሆነ — መልዕክቱን በግልጽና በተረዳ መንገድ ያስተላልፋል።

ስሜቱን መቆጣጠር የሚችል — በቁጣ፣ በግፊትና በችግር ጊዜ ራሱን ይቆጣጠራል።

የሌሎችን ስሜት የሚረዳ — የሠራተኞችን ሁኔታና ፍላጎት ይገነዘባል።

ለለውጥ ዝግጁ የሆነ — አዳዲስ ሐሳቦችንና የሥራ ዘዴዎችን ይቀበላል።

ተስፋ የማይቆርጥ — ከውድቀት ተምሮ ወደ ስኬት ለመድረስ ይጥራል።

ተግባርን የሚያስፈጽም — የተያዙ ዕቅዶች በተግባር እንዲውሉ ይከታተላል።

ተተኪ መሪዎችን የሚያፈራ — ሌሎች አመራሮች እንዲያድጉ ዕድል ይፈጥራል።

በትብብር የሚሠራ — የቡድን ሥራንና የጋራ ውሳኔን ያበረታታል።

ውጤትን የሚለካ — ሥራዎች የታሰበውን ውጤት ማምጣታቸውን ይገመግማል።

ራሱን የሚገመግም — ድክመቱን ያውቃል፣ ከስህተቱ ይማራል፣ ራሱንም ያሻሽላል።

#ጠንካራ አመራርና አምባገነን አመራር ያላቸው ልዩነቶች!

ጠንካራ አመራር በሕግ ይመራል፤ አምባገነን አመራር የግል ፍላጎቱን ከሕግ በላይ ያደርጋል።

ጠንካራ አመራር ቅሬታን ያዳምጣል፤ አምባገነን አመራር ትችትን ያልፋል።

ጠንካራ አመራር ለስህተቱ ኃላፊነት ይወስዳል፤ ደካማ ተጠያቂነት ያለው አመራር ጥፋቱን በሌሎች ላይ ያሳብባል።

ጠንካራ አመራር በአመክንዮና በማስረጃ ይወስናል፤ አምባገነን አመራር በግል ፍላጎትና በግዴታ ይወስናል።

ጠንካራ አመራር ሠራተኞችን ያበቃል፤ አምባገነን አመራር ሥልጣኑን ለመጠበቅ የሌሎችን እድገት ይገድባል።

ጠንካራ አመራር በውጤትና በእምነት ይመራል፤ አምባገነን አመራር በፍርሃትና በማስፈራራት ሊመራ ይመራል።

#የጠንካራ አመራር ዋና መለኪያ

ጠንካራ አመራር የሚለካው በሥልጣኑ መጠን ሳይሆን፣ በሚያመጣው ውጤት፣ በሕግ ማክበሩ፣ በፍትሐዊነቱ፣ በሕዝብ እምነትና በተጠያቂነቱ ነው።

ለምሳሌ፦

በአንድ የወረዳ ጽሕፈት ቤት ውስጥ ጠንካራ አመራር ያለው ኃላፊ የሠራተኞችን ቅሬታ ያዳምጣል፣ የሥራ ውጤትን በግልጽ መስፈርት ይገመግማል፣ የሕዝብ ጥቅምን ያስቀድማል፣ ከስህተቱም ይማራል።

#ማጠቃለያ

ጠንካራ መሪ ማለት ሁሉም ሰው የሚፈራው ሰው ሳይሆን፣ ሰዎች በብቃቱ፣ በፍትሐዊነቱና በታማኝነቱ የሚያከብሩት ሰው ነው።
❤3