ECWC/ኢኮሥኮ
14.3K subscribers
3.42K photos
35 videos
294 files
296 links
Official ECWC Telegram Channal
.የኮርፖሬሽኑ ዜናዎች
.የጨረታና የሥራ ማስታወቂያዎች
. በየወሩ የሚታተመው የዜና መጽሄት
. ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮች
.በየ 6ወሩ የሚታተመው የኮርፖሬሽኑ ዕይታ መጽሄት እና የኮርፖሬሽኑ ፕሮፋይል በዚህ ገጽ ላይ በየጊዜው ይቀርባል፡፡
Download Telegram
የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ዕድሳትና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ
--------------
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እየተገነባ የሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት የህንጻ ዕድሳት እና ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡
በኮንትራት ስምምነቱ መሰረት የባለ ስድስት ወለል ህንጻ የዕድሳት ሥራ፣ የባለ ሁለት ወለል ካፍቴሪያ ግንባታ፣ የግቢ ማስዋብ ሥራ፣ የአስፋልት ንጣፍ እና የአጥር ሥራዎችን የሚያጠቃልለው ፕሮጀክት በተቀመጠለት የጥራት ደረጃ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አክሊሉ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ሥርዓቶችን በመጠቀም ግንባታውን በተቀላጠፈ መንገድ ለመምራት ከፍተኛ ጥረት ማደረጉን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ በቅርቡ ርክክብ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡