Ethiopian Coffee and Tea Authority
6.03K subscribers
5.9K photos
30 videos
67 files
372 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
የቡና መጽሀፍ ተዘጋጅቶ ለንባብ በቃ!!
ሚያዝያ 29/2018
አዲስ አበባ
በዘርፉ ላይ ግማሽ ምዕተ አመት የሚጠጋ የካበተ ልምድ ባላቸው እና ከረዳት የቡና ልማት ሰራተኝነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት የበቁት አቶ ሬድዋን ከድር አማካኝነት "ኢትዮጵያዊው ወርቅ" በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የቀረበው መጽሀፍ በዛሬው እለት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ የግል ድርጅቶች የተውጣጡ የቡና ቤተሰቦች በተገኙበት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል፡፡ ይህ መጽሀፍ በሀያ የተለያዩ ምእራፎች ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ሲሆን ቡናን ከማሳ ዝግጅት አንስቶ እስከ ኤክስፖርት ድረስ ሊደረግባቸው የሚገቡ ተግባራትን፣ ቡናን በሜካናይዝድ ማልማት ስለሚቻልበት ዘዴ፣ የጠብታ መስኖ አጠቃቀም፣ ቡናና የሰው ልጅ ያላቸውን ተፈጥሯዊ መስተጋብር እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ ጉዳዮች አካቶ የያዘ መሆኑ ፀሀፈው አብራርተዋል፡፡
ክቡር አቶ ሻፊ የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳ/ር በምረቃ ስነ ስርአቶ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ቡና የአገሪቱ አንጡራ ሀብት እና የአገሪቱ ሩብ ህዝብ ቁጥር የኑሮ መሰረት በመሆኑ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ትርጉም ያለው በመሆኑ ልንጠብቅ እና ልንንከባከበው ይገባል ያሉት አቶ ሻፊ በዘርፉ ካለው የሰለጠነ ብቁ ባለሙያ እጥረት እና ቡናን በተመለከተ የተዘጋጁ ሳይንሳዊ መረጃዎች አናሳነት አንጻር ይህ መጽሀፍ ብዙ ክፍተቶችን ሊሞላ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
አቶ ታጋይ ኑሩ የባለስልጣን መ/ቤቱ ልማት ዘርፍ ኃላፊና ምክ/ዋና ዳ/ር በበኩላቸው ግለሰቡ ካላቸው በርካታ የካበተ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት አንጻር ይህን ሙያዊ መጽሀፍ ማበርከታቸው የሚደነቅ ተግባር መሆኑን ጠቁመው ሌሎችም የእሳቸውን ፈለግ በመከተል ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችሉ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ሊያበረክቱ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በእለቱ በክብር እንግድንት የተገኙት ክቡት አቶ ኡሰማን ሱሩር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊም እንደተናገሩት አገራችን በበርካታ የተፈጥሮ ፀጋ የታደለች እንደመሆኗ ቡና ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ ያበረከትነው ድንቅ ስጦታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ቡናን በዘመናዊ መንገድ ለማልማት እና በሜካናይዜሽን እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አልምቶ ለመጠቀም እንዲቻል በዘርፉ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች አስተዋጽዖ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመው ይህ ዛሬ ለምርቃት የበቃው መጽሀፍ በዚህ በኩል ለአርሶ አደሩ ማህበረሰብም ሆነ በዘርፉ ለተሰማራ ዜጋ ትልቅ ሚና ስለሚኖረው ታች ህብረተሰቡ ዘንድ እንዲደርስ በክልልላቸው በኩል ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡