Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.54K subscribers
5.18K photos
29 videos
66 files
356 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
የቡና ጥራት ከማስጠበቅ ባሻገር በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የቡና አምራች አርሶ አደሮች ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፦
==== ====== ====== ======
#ታህሳስ_14_2018_ዓ_ም

ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ ፊት ከወጡ አያሌ ሀገራት፣የምትመደብ ሲሆን፣ቡና አገርቱ የዉጭ ምንዛሬ ከሚታገኛቸው ምርቶች ቀዳሚ እንደሆነ ይታወቃል።

በሀገራችን ቡና ከሚመረትበት አከባቢዎች መካከል የጌዴኦ ዞን ቀዳሚ ሲትሆን፣መንግሥት የአርሶ አደሮች ተጠቃሚነት በማሻሻልና ጥራት ያለው ቡና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በወናጎ ወረዳ ዶቦታ ቀበሌ የሚገኙ ሞዴል አርሶ አደር የአቶ ተገኝ ኦቾሎ የቡና ማሳ እና ሥራዎች ድጋፍና ምልከታ አድርገዋል።

በዘኑ የሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች ቡና ከማምረት ባሻገር፣የቡና ጥራት ለማስጠበቅ መንግስት እያደረገ ያለውን ሙያዊ ድጋፍ እና ክትትል ተጠናከሮ እንደሚቀጥል የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም አምራች አርሶ አደሮች፣ጥራት ያሉውን ቡና በቀጥታ ለውጪ ለገበያ እንዲያቀርቡ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የወናጎ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት እና የዘርፉ ባለሙያዎች፣ምርትና ምርታማነትን በማሻሻል በወረዳው ከሚገኙ አርሶ አደሮች ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰጠ ያለው ትኩረት የሚደነቅ እንደሆነ ተጠቅሷል።

አሁን ላይ ጥሩ የሚባል የቡና ገበያ እንዳለ ተገለጹት ሞዴል አርሶ አደር አቶ ተገኝ፣መንግሥት እያደረገላቸው ባለው ድጋፍ ጥራቱ የጠበቀ ስፔሻል ቡና ለገበያ ለማቅረብ እየሰራ እንደምገኝ ተናግሯል።

የወናጎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው
የቸሃ ወረዳ የቡና ልማት ተሞክሮ

*****

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በቸሃ ወረዳ በዘመናዊ የግብርና አሰራር የቡና ልማት እየተስፋፋ ነው፡፡ የወረዳውን የቡና ኢኒሼቲቭ ለማሳካት አርሶአደሮች በ12 ክላስተሮች የተደራጁ ሲሆን አንዱ ክላስተር 120 አርሶአደሮችን በማቀፍ እያንዳንዱ አርሶአደር በየዓመቱ 250 የቡና ምርጥ ዘር ችግኞችን ተክሎ ያለማል፡፡

በችግኝ ጣቢያዎች፣ በቡድኖች እና በአርሶአደሮች ችግኞቹ እንደሚዘጋጁ የጠቀሱት የቸሃ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ጠቅልል አባድየ፣ በወረዳው እስከ አሁን የቡና ልማት ሽፋን ከ9 ሺህ ሄክታር በላይ መድረሱን እና በዘንድሮው መጪ ክረምትም የሚተክል 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የቡና ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተለይም የአቶርቸ እና የቡቻች ችግኝ ጣቢያያዎች በወረዳው እየተስፋፋ ላለው የምርጥ ዝሪያ ቡና ልማት የጎላ አስተዋፅዖ አላቸው፡፡ አምና ከሁለቱም ችግኝ ጣቢያዎች 400 ሺህ ችግኞች ለአርሶአደሮች ተሰራጭተው የተተከሉ ሲሆን ለዘንድሮ ክረምት ተከላ ደግሞ ከ400 ሺህ በላይ ችግኞች ፈልተው ጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

የቸሃ ወረዳ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ትዕግስቱ ናንሳነ ፕሮግራሙ በወረዳው የነበሩትን የግብዓት ቅርቦት እጥረት፣ የክህሎት ክፍተትና የአስተሳሰብ ችግሮችን በመፍታት በክልሉ የተጀመረውን የቡና ኢኒሼቲቭ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው እንደወረዳ በ12 ክላስተር በታቀፉት አርሶአደሮች ብቻ ዓምና 630 ሺህ የቡና ችግኞች መተከላቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕሮግራሙ ዘንድሮ ለሚተከለው የቡና ችግኞች ዝግጅት 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር መደገፉንና ለ2019 ዓ.ም ቡና ችግኝ ዝግጅት ደግሞ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በመመደብ ቅድመ-ዝግጅት መጀመሩን አቶ ትዕግስቱ ተናግረዋል፡፡

የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የቡና ችግኝ ጣቢያያዎችን አቅም በመገንባት የቡና ምርጥ ዘር በወረዳው እንዲስፋፋ የማይተካ አስተዋፅዖ እያበረከተ ነው፡፡

የቡና ምርጥ ዘር፣ ለችግኝ ተስማሚ የሆነ አፈር፣ ፖሊባግ እና ለችግኝ ጣቢያው የሚያስፈልጉ የግብርና መሳሪያዎችን ከማቅረብ ባሻገር ለአርሶአደሮችም የተግባር ስልጠና በመስጠት እየደገፈ ይገኛል፡፡

የሲሰና እማትየ ቀበሌ ነዋሪ አርሶአደር አየለ በርታ ከቡና አልሚዎች ግምባር ቀደም ናቸው፡፡ በፊትም ከጅማ በቀሰሙት ልምድ የቡና አምራች ሞዴል አርሶአደር ሲሆኑ በፕሮግራሙ ድጋፍ ዓምና የተከሉትን 250 ምርጥ ዝሪያ ቡና እያለሙ ለመጪው ክረምት ተከላም ዝግጅት ጀምረዋል፡፡ በምርጥ ዝሪያ ቡናም ሞዴል ለመሆን እየሰሩ ይገኛሉ ሲል የዘገበዉ የቸሀ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።
በጎፋ ዞን በመሎ ጋዳ ወረዳ በአሊዛ ጎይዶ ቀበሌ የኮረሪማ ምርት በፎቶ
ቡና አምራች አርሶ አደሮችን ከኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው

በሲዳማ ክልል ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑ ቡና አምራች አርሶ አደሮችን ከኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በክልሉ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።

በዚህም ከ200 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ቡና አጥበውና ፈልፍለው ከሚያዘጋጁ ኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር የቡና ጥራትንና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከኢንዱስትሪዎች ጋር የተፈጠረውን ትስስር ከቡና ጥራት ባሻገር አርሶ አደሩ ከምርቱ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ እያስቻለ መሆኑን ጠቁመው፥ ባለፈው ዓመት 10 ኢንዱስትሪዎች ትርፍ ክፍፍል ማድረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በንሳ ወረዳ ትስስር ከፈጠሩ አርሶ አደሮች ቡና የሚረከቡ ባለሃብቶች፤ ትስስሩ ጥራትንና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም አርሶ አደሩ ከችግኝ ተከላ እስከ ቡና ለቀማ የባለሙያ ድጋፍ እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ለኢንዱሰትሪዎች ቡና ከሚያቀርቡ አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር አስፋው ሆሼ፤ ከተከላ ጀምሮ እስከ ቡና ለቀማ የባለሙያዎችን ምክር ተቀብለው በመስራታቸው የተሻለ ምርት ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከደረሰ ማሳቸው የለቀሙትን ከ220 ኪሎ ግራም በላይ ቡና ትስስር ለፈጠሩት ኢንዱስትሪ በማቅረብ በተገቢው ዋጋ መሸጣቸውን ተናግረዋል፡፡