Ethiopian Coffee and Tea Authority
6.03K subscribers
5.9K photos
30 videos
67 files
372 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
ለልማት መሬት ከተሰጣቸው ባለሀብቶች ጋር ሰፊ ውይይት ተካሄደ!!
ሚያዝያ 24/2018፡ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ቡና ለማልማት ከ101 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከተሰጣቸው 110 ባለሀብቶች እና ድርጅቶች ጋር በዛሬው እለት በባለስልጣን መ/ቤቱ አዳራሽ ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ክቡር ዋና ዳ/ር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በውይይቱ መክፈቻ ላይ ተገኝው እንደተናገሩት አገሪቱ ያላትን ከፍተኛ የቡና ማልማት አቅም በአግባቡ መጠቀም እንድትችል መንግስት ልዩ ትኩረት በመስጠት አልሚ ባለሀብቶች መሬት ወስደው ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሜካናይዝድ እርሻን ማስፋፋት እንዲችሉ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እጅግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ101 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መሰጠት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል ለልማት ተብሎ መሬት ለመስጠት የነበረውን እጅግ ውስብስብ እና ተስፋ አስቆራጭ አሰራር መቅረፍ የተቻለበት መሆኑን ጠቁመው፤ ይህን ወርቃማ እድል ተጠቅሞ በፍጥነት ወደ ስራ መግባት ደግሞ የሁሉም ግዴታ መሆኑን አስምረውበታል፡፤
የልማት ዘርፍ ምክ/ዋና ዳ/ሩ ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ በበኩላቸው ለዘመናት በሄክታር መሬት ላይ ይመረት የነበረውን እና በባለፈው በጀት አመት 9.5 ኩንታል በሄክታር የተደረሰበትን ሁኔታ በአገራችን በአንድ አልሚ ባለሀብት ሜካናይዝድ እርሻን በመጠቀም 54 ኩንታል በሄክተር መሬት ማልማት መቻሉ በዘርፉ ያልተጠቀምንበት እምቅ አቅም ያለን መሆኑን አመላካች እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ይህ አይነት አሰራር ተጠቅመው የአለማችን ቁንጮ ቡና አምራች አገራት የሆኑት ብራዚል እና ቪየትናም ይህን አሰራር በመከተላቸው ለዚህ ደረጃ እንዳበቃቸው ያስረዱ ሲሆን የእኛም ባለሀብቶች የተመቻቸውን አጋጣሚ በአግባቡ በመጠቀም አርሶ አደሩን፣ አገራችንን በአጠቃላይ የዘርፉን ተዋናይ ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል እድል የቀረበላቸው በመሆኑ በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በአጠቃላይ እያንዳንዳቸው ተሳታፊዎችም የተረከቡትን መሬት በተመለከተ የርክክብ ሂደቱን፣ የተረከቡባቸውን አካባቢዎች፣ አሁን የደረሱበትን ደረጃ እንዲሁም ገጥመውናል ባሏቸው ተግዳሮች ዙሪያ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ክቡር የግብይት ዘርፍ ምክ/ዋና ዳ/ሩ አቶ ሻፊ ኡመር በማጠቃለያው ላይ በሰጡት ሀሳብ በአገሪቱ ታሪክ እንዲህ ባለ አጭር ጊዜ እና ከቢሮክራሲ በጸዳ ሁኔታ የተሰጠው መሬት የአገር ሀብት በመሆኑ በታቀደው ጊዜ ለታሰበው ዓላማ መዋሉን እንደመንግስት የተጠናከረ ክትትል እንደሚደረግበት የተናገሩ ሲሆን አልፎ አልፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ቢኖሩ እንኳ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር በመቀናጀት በሚመለከተው አካል በኩል ችግሩ እንዲፈታ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል፡፡
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

በኮንፈረሱ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የተጋበዙ እንግዶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በአለም አቀፍ የቡና ኮንፈረንሱ የተለያዩ የቡና ተመራማሪዎች ጥናታዊ ጽሁፋቸውን እንደሚያቀርቡ እና ኮንፈረንሱ ሚያዝያ 24 እና 25/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ የወጣው መርሃ-ግብር ያመለክታል።

ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን
የቡና መጽሀፍ ተዘጋጅቶ ለንባብ በቃ!!
ሚያዝያ 29/2018
አዲስ አበባ
በዘርፉ ላይ ግማሽ ምዕተ አመት የሚጠጋ የካበተ ልምድ ባላቸው እና ከረዳት የቡና ልማት ሰራተኝነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት የበቁት አቶ ሬድዋን ከድር አማካኝነት "ኢትዮጵያዊው ወርቅ" በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ የቀረበው መጽሀፍ በዛሬው እለት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ የግል ድርጅቶች የተውጣጡ የቡና ቤተሰቦች በተገኙበት ተመርቆ ለንባብ በቅቷል፡፡ ይህ መጽሀፍ በሀያ የተለያዩ ምእራፎች ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ሲሆን ቡናን ከማሳ ዝግጅት አንስቶ እስከ ኤክስፖርት ድረስ ሊደረግባቸው የሚገቡ ተግባራትን፣ ቡናን በሜካናይዝድ ማልማት ስለሚቻልበት ዘዴ፣ የጠብታ መስኖ አጠቃቀም፣ ቡናና የሰው ልጅ ያላቸውን ተፈጥሯዊ መስተጋብር እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ ጉዳዮች አካቶ የያዘ መሆኑ ፀሀፈው አብራርተዋል፡፡
ክቡር አቶ ሻፊ የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳ/ር በምረቃ ስነ ስርአቶ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ቡና የአገሪቱ አንጡራ ሀብት እና የአገሪቱ ሩብ ህዝብ ቁጥር የኑሮ መሰረት በመሆኑ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ትርጉም ያለው በመሆኑ ልንጠብቅ እና ልንንከባከበው ይገባል ያሉት አቶ ሻፊ በዘርፉ ካለው የሰለጠነ ብቁ ባለሙያ እጥረት እና ቡናን በተመለከተ የተዘጋጁ ሳይንሳዊ መረጃዎች አናሳነት አንጻር ይህ መጽሀፍ ብዙ ክፍተቶችን ሊሞላ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
አቶ ታጋይ ኑሩ የባለስልጣን መ/ቤቱ ልማት ዘርፍ ኃላፊና ምክ/ዋና ዳ/ር በበኩላቸው ግለሰቡ ካላቸው በርካታ የካበተ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት አንጻር ይህን ሙያዊ መጽሀፍ ማበርከታቸው የሚደነቅ ተግባር መሆኑን ጠቁመው ሌሎችም የእሳቸውን ፈለግ በመከተል ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችሉ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ሊያበረክቱ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በእለቱ በክብር እንግድንት የተገኙት ክቡት አቶ ኡሰማን ሱሩር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊም እንደተናገሩት አገራችን በበርካታ የተፈጥሮ ፀጋ የታደለች እንደመሆኗ ቡና ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ ያበረከትነው ድንቅ ስጦታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ቡናን በዘመናዊ መንገድ ለማልማት እና በሜካናይዜሽን እና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ አልምቶ ለመጠቀም እንዲቻል በዘርፉ ልምድ ያካበቱ ባለሙያዎች አስተዋጽዖ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመው ይህ ዛሬ ለምርቃት የበቃው መጽሀፍ በዚህ በኩል ለአርሶ አደሩ ማህበረሰብም ሆነ በዘርፉ ለተሰማራ ዜጋ ትልቅ ሚና ስለሚኖረው ታች ህብረተሰቡ ዘንድ እንዲደርስ በክልልላቸው በኩል ያላሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡