☕️⚽️
የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ፕሬዝደንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ እስከዛሬ ለነበራቸው አበርክቶ ምስጋና የተቸራቸው ሲሆን ለአዲሱ ፕሬዝደንት ዶ/ር እስራኤል ደገፋ ደግሞ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንም የቀደሙትን ከልብ በማመስገን፣ ለአዲሱ አመራር መልካም የስራ ዘመን ይመኛል።

ቻይና በአውሮፓ ገበያ የቡናውን ዘርፍ በዝቅተኛ ዋጋ እና በከፍተኛ ቅልጥፍና እየተቀላቀለች ነው!!
• አውሮፓ ከአለም አቀፍ የቡና ፍጆታ ከ32% በላይ የሚሆነውን ድርሻ በመያዝ ለገበያ ምቹ የሆነች ቀጠና ናት።
• የቻይና የንግድ ምልክቶች የቡና አጠቃቀም ባህልን እስከ ምን ድረስ ሊቀይሩት እንደሚችሉ ገደብ ቢኖርም፣ ገበያውን ግን ወደ ተለያዩ ዘርፎች (Segmentation) እንደሚከፍሉት ይጠበቃል።
ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ፣ የቡና ችርቻሮ ንግድ በታወቁ አሰራሮች አማካኝነት ዓለም አቀፋዊ ሆኗል፤ ይህም "ቡና ቤት" ምቾትንና ድባብን (Atmosphere) ከአገልግሎት ቅልጥፍና ጋር አቀናጅቶ የያዘ "ሦስተኛው ስፍራ" (Third place) ተብሎ ይጠራ ነበር። አሁን ግን አዲስ ሞዴል ብቅ ብሏል፤ ይህ ሞዴል በልምድ ወይም በድባብ ላይ ሳይሆን በፍጥነት፣ በስፋት እና በዝቅተኛ ዋጋ ላይ የተገነባ ነው።
የቻይና የቡና ብራንዶች በፍጥነት ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እየገቡ ነው። ይዘውት የመጡት የሥራ ሥርዓትም በሞባይል መተግበሪያ (App) ትዕዛዝን መቀበል፣ ጥቅጥቅ ያሉ የመሸጫ ቅርንጫፎች እና አስገራሚ የዋጋ ቅናሽ ላይ ያተኮረ ነው። እነዚህ ተቋማት የቡናን ባህል ሳይሆን፣ የአሰራር ቅልጥፍናን ወደ ውጭ እየላኩ (Export እያደረጉ) ነው።
አውሮፓ በከፍተኛ የቡና ፍጆታዋና እየጨመረ በመጣው ዋጋ ምክንያት ቀጣዩ ተመራጭ መዳረሻቸው ሆኗል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ፣ ዝቅተኛ ዋጋና ከፍተኛ ቅልጥፍና ያላቸው ኦፕሬተሮች ወደ ገበያው ከመግባት ባለፈ፣ የገበያ ድርሻን ለመቆጣጠርና ቡና በከፍተኛ ደረጃ የሚሸጥበትን መንገድ ለመቀየር አመቺ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።
የተለየ ዓይነት ፉክክር
የቻይና የቡና ሰንሰለቶች መስፋፋት ከአዳዲስ የገበያ ተወዳዳሪዎች መምጣት በላይ ትርጉም አለው። ይህ በአውሮፓ የቡና ችርቻሮ ንግድ ውስጥ መሰረታዊ የሆነ የተለየ አቀራረብን ያስተዋውቃል።
ከቻይና ግዙፍ የቡና ብራንዶች አንዱ የሆነው ኮቲ ኮፊ (Cotti Coffee)፣ በ28 አገራት ውስጥ ከ10,000 በላይ መሸጫዎች አሉት። እ.ኤ.አ. በ2026 መጀመሪያ ላይ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ስፔን ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን፣ በቅርቡ ወደ ጣሊያን፣ ቤልጂየም፣ ፖርቱጋል እና ኔዘርላንድስ ለመስፋፋት ማቀዱ ተገልጿል።
ምንም እንኳን በአካል በአውሮፓ ገበያ ገና ባይታይም፣ ሉኪን ኮፊ (Luckin Coffee) ከ30,000 በላይ ሱቆችና 450 ሚሊዮን ደንበኞች ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ በእስያና በአሜሪካ መስፋፋቱን ቀጥሏል። ወደ አውሮፓ ገበያ ለማምራት ባለው እቅድ ውስጥ የአውሮፓ ትልቁን የቡና ሰንሰለት የሆነውን ኮስታ ኮፊን (Costa Coffee) የመግዛት ፍላጎት እንዳለውም ተዘግቧል።
የ"ኮፊ ኮንሱሌት" (Coffee Consulate) መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶ/ር ስቴፈን ሽዋርዝ እንዲህ ይላሉ፡-
“ይህ እጅግ ትልቅ ለውጥ ነው፤ ምክንያቱም ወደ ውጭ እየተላከ ያለው ብራንድ ብቻ ሳይሆን ሙሉ ‘የአሰራር አመክንዮ’ (Operating logic) ነው። ይህ ከአሁን በኋላ የቻይና የሀገር ውስጥ የንግድ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ በአለም አቀፍ የቡና ችርቻሮ ዘርፍ አዲስ የፉክክር ሞዴል መከሰቱን የሚያሳይ ነው።”
ይህ "የአሰራር ሞዴል" ከልምድ ይልቅ ለውጤት (Output) ቅድሚያ ይሰጣል። አነስተኛ የመሸጫ ስፍራዎች፣ በመተግበሪያ የሚመራ ትዕዛዝ እና ፈጣን ርክክብ ባህላዊውን የቡና ቤት ድባብ ይተካሉ። ዋጋውም በተመሳሳይ ገበያውን የሚረብሽ ነው፤ ለምሳሌ በጀርመን የሚገኘው ኮቲ ኮፊ የአንድ ኤስፕሬሶ ዋጋ €0.99 እና የካፑቺኖ ዋጋ ከ**€3** በታች እንዲሆን አድርጓል፤ ይህም ከአካባቢው ነባር ዋጋዎች እጅግ ያነሰ ነው።
አውሮፓ ለምን ተመረጠች? እድሉስ የት ጋር ነው?
ይህ አዲስ ሞዴል፣ የቡና ጥራትን ደንበኛው በቦታው ቆይቶ ከሚያሳልፈው ምቹ ጊዜ ጋር አጣምሮ ከቆየው ከአውሮፓ የቡና ገበያ ጋር በእጅጉ ይቃረናል።
ውጤቱም ነባሩን ሞዴል በቀጥታ መተካት ሳይሆን፣ ጎን ለጎን በማራመድ ነው። የቻይና የቡና እሴት ሰንሰለቶች የአውሮፓን የቡና ባህል ለመድገም እየሞከሩ አይደለም፤ እነሱ እየተወዳደሩ ያሉት ሙሉ በሙሉ በሌላ መስክ ነው።
ወቅቱ ለዚህ ሽግግር ወሳኝ ነው። የአውሮፓ የቡና ገበያ በጥሬ ቡና ዋጋ መናር፣ በጉልበት (Labor)፣ በቤት ኪራይና በኢነርጂ ወጪ መጨመር ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ነው።
አውሮፓ እ.ኤ.አ በ2025 የዓለምን 32% ፍጆታ በመሸፈንና በነፍስ ወከፍ ከፍተኛ የቡና ተጠቃሚ አገራትን በመያዝ ቀዳሚነቷን ቀጥላለች። ይህ ከፍተኛ ፍጆታና እየጨመረ የመጣው ዋጋ ዝቅተኛ ወጪ ለሚጠይቁት ተዋናዮች ግልጽ የሆነ የመግቢያ በር ከፍቷል። ቢሆንም ግን፣ ዶ/ር ስቴፈን ርካሽ አማራጮች ቢመጡም ደንበኞች ጥራት ያለውን (Specialty) ቡና ግን በፍጹም እንደማይተዉ ያምናሉ።
እንደ እሳቸው ገለጻ፣ የዋጋ መጨመር ደንበኞች በልዩ ሁኔታ የሚዘጋጅ ቡናን እንዲተዉ አያደርጋቸውም። ይልቁንም፣ የዋጋ ጫናው በሁለት የተለያየ የፍጆታ አይነቶች መካከል ያለውን ልዩነት ያሰፋዋል፡-
1. ቡና እንደ ልምድ (Coffee-as-experience): ለጣዕም፣ ለባህልና ለጥራት የሚጠጣ።
2. ቡና እንደ የዕለት ተዕለት ልማድ (Coffee-as-functional habit): ለስራ ወይም ለመንገድ በፈጣንና በዝቅተኛ ዋጋ የሚፈለግ።
“ያ የፍጆታ ክፍተት ነው እጅግ ቀልጣፋ ተወዳዳሪዎች ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉበት ቦታ፣” ሲሉ ስቴፈን ያጠቃልላሉ።
ይህ የገበያ ፉክክር የዘርፉን የገበያ ዑደት ይቀይረው ይሆን?
ሳህለማርያም ገ/መድህን
ምንጭ ያደረኩት Coffee Intellegence ነው:
https://intelligence.coffee/.../chinese-coffee-brands.../...

Coffee Intelligence
Chinese coffee brands have European consumers in their sights - Coffee Intelligence
Chinese coffee chains are expanding into Europe with their low-price, high-efficiency model, causing market segmentation.
Jordanian Ambassador Explores Collaboration with Ethiopian Coffee and Tea Authority
ADDIS ABABA — The Jordanian Ambassador to Ethiopia, His Excellency Amjad Al-Moumani, paid an official visit to the headquarters of the Ethiopian Coffee and Tea Authority (ECTA) today, April 16, 2026. Upon his arrival, the Ambassador was welcomed by the Director General of the Authority, Dr. Adugna Debela, for high-level discussions aimed at strengthening agricultural trade ties between the two nations.
During the meeting, Ambassador Al-Moumani emphasized that Jordan has a profound interest in Ethiopian coffee, noting that it is a widely consumed beverage in his country. He expressed a strong desire to collaborate on coffee import and export ventures, citing Ethiopia's reputation for producing high-quality agricultural goods. However, the Ambassador pointed out that to fully realize this trade potential, Jordan requires more comprehensive data regarding Ethiopia’s specific coffee grading standards and the formal procedures governing the marketing and procurement process.
In response, Dr. Adugna Debela provided an extensive briefing on the Authority’s strategic mission to modernize the coffee, tea, and spice sectors. He explained that the ECTA is dedicated to boosting productivity and ensuring that all exports are of premium quality and fully traceable for the global market. Dr. Adugna underscored the vital role coffee plays in the Ethiopian economy and its deep-rooted significance in the country’s cultural heritage. He further noted that following recent national reforms, the sector has seen a major breakthrough in terms of quality control and production efficiency.
To facilitate Jordan's future trade activities, the Director General elaborated on the legal framework for exporters, the logistics of product transportation, and the rigorous monitoring systems currently in place. The visit concluded with Ambassador Al-Moumani touring the Authority’s specialized Coffee Training Center to see the quality-control process firsthand. The event was documented by the ECTA’s Public Relations and Communications team. By Tesfu Alemayehu

📉 የአለማችን ቡና ገበያ ወቅታዊ ሁኔታ በአጭሩ ምን ይመስል ይሆን?/ ያነበብኩትን!
በሳህለማርያም ገ/መድህን
(ሚያዝያ 13/2018)፦ አሁንም የዋጋ መቀነስ ይታያል፣ በአንፃሩ ደግሞ የአቅርቦት ጫና ማደግ ይታይበታል።
በያዝነው ሳምንት የዓለም የቡና ገበያ ግልጽ የሆነ ምልክት እያሳየ ይገኛል፤ ዋጋ እየቀነሰ ነው። ይህ ደግሞ እንዲሁ በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን ተጨባጭ ምክንያቶች ያሉት ክስተት ነው።
☕
🌍 የዓለም አቀፍ ገበያ (ሁለንተናዊ ቅናሽ)
የሮቡስታ እና አረቢካ የቡና አይነቶች በሁሉም ዋና ዋና የንግድ ማዕከላት በቀይ መስመር ውስጥ/በቅናሽ) ይገኛሉ፦
⚠️ ለዋጋ መቀነሱ ምክንያቶቹ ምንድን ናቸው?
ይቀጥላል ..

1. ከፍተኛ የአቅርቦት ሞገድ እያስገመገመ መምጣት
ብራዚል ወደ ዋናው የመከር ወቅት እየገባች ሲሆን፣ የደቡብ ምስራቅ እስያ አገራት (ቬትናም እና ኢንዶኔዥያ) አዲስ ምርታቸውን በገፍ ለማቅረብ እየተዘጋጁ ነው። ገበያው ወደፊት የሚመጣውን የተትረፈረፈ ምርት ግምት ውስጥ በማስገባት ይመስላል ዋጋውን Adjust እያደረገ የሚገኘው።
2. ጠንካራ የምርት ትንበያ
እንደ Safras & Mercado ያሉ ተቋማት የብራዚል የ2026/27 ምርት ወደ 75.65 ሚሊዮን ከረጢት/Bag ሊጠጋ እንደሚችል ገምተዋል። ይህም በተለይ በአረቢካ ቡና ላይ የ29% እድገት ያሳያል ተብሏል። እንዲህ ዓይነቱ የአቅርቦት መተማመን ደግሞ በዋጋው ላይ የሌለ ጫናን ፈጥሯል በቀጣይም ይፈጥራል።
3. ደካማ የንግድ እንቅስቃሴ
በቪየትናም ገበሬዎች ምርት ይዘው ተቀምጠዋል፤ በኢንዶኔዥያ ደግሞ የዋጋ ልዩነቶች (Premiums) እየጠበቡ መጥተዋል። ገዥዎችም ሆኑ ሻጮች ነገሮችን በትዕግስት እየተጠባበቁ በመሆናቸው ገበያው ተቀዛቅዟል።
📊 የአሁኑ የገበያ መዋቅር
👉 የአቅርቦት ግምት፦ ከፍተኛ
👉 የገበያ እንቅስቃሴ፦ ዝቅተኛ
👉 የዋጋ አቅጣጫ፦ ወደ ታች
➡️ ይህ ሁኔታ በድንገተኛ ድንጋጤ (Panic selling) የመጣ ሳይሆን፣ ገበያው ራሱን እያስተካከለ ያለበት (Structural adjustment) ሂደት ነው።
💡 ቀጥሎ ምን ይጠበቃል?
በሚቀጥለው ወር የሚጠበቀው የብራዚል አረቢካ ምርት
የገበሬዎች የመሸጥ ፍላጎት ከገዥዎች ፍላጎት ጋር ያለው ፍጥጫ
እነዚህ ነጥቦች የገበያውን ቀጣይ ጉዞ የሚወስኑ ወሳኝ ጉዳዮች ይሆናሉ።
እኛስ ቀጣይ ሁኔታችንን እንዴት እያስተካከልነው እንሄዳለን? የእኔም፣ የእናንተም፣ የሁላችንም የቤት ስራ ይሆናል!!!

ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ የቻይና ልዑካንን ተቀብለው አነጋገሩ!!
ሚያዝያ 14/2018፡ አዲስ አበባ
ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በዛሬው እለት ከቻይና HONGQIAO አለማቀፍ ኢኮኖሚክ ፎረም የመጡ እንግዶችን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በቅርቡ በቻይና በሚካሄደው ኢንተርናሽናል ኢምፖርት ኤክስፖርት ኤክስፖ የዘርፉ ተዋናዮች ተሳታፊ በሚሆኑበት እና ምርቶቻቸውን ማስተዋወቅ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ አገራችን ወደ ቻይና እየላከችው ካለው የቡና ምርት ጋር ተያይዞ ከአመት ወደ አመት እያታየ ያለውን ከፍተኛ እድገት እንዲሁም ቀጣይ በሚጠበቁ ሁኔታዎች ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡ መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች እንዲሳተፉ የሰጠውን እድል ለመጠቀም የተለያዩ የቻይና ኩባንያዎች በዘርፉ ለመሳተፍ ወደ አገራችን እየመጡ መሆናቸውን የጠቆሙት ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ወደፊት ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በቡናው ዘርፍ ጋር ያላትን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ለሚደረገው ጥረት በመንግስት አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

#በኦሮሚያ ክልል የሻይ ቅጠል ምርት!
👉በክልሉ የሻይ ቅጠል ልማት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል። በዚህም፡-
-በ2013 ዓ.ም በሻይ ቅጠል የተሸፈነው መሬት 1,183 ሄክታር ነበር። በአሁኑ ወቅት ይህ አሃዝ ወደ 2,697 ሄክታር አድጓል።
👉መንግስት ምርቱን ለማስፋፋት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፦ ይሄውም:-
-ገበሬዎችን በክላስተር እንዲያለሙ ማበረታታት።
-ምርጥ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን፣ የሙያ ስልጠናና ቴክኒካዊ ድጋፎችን ማቅረብ።
-የገበያ ትስስርን ማጠናከርና የምርት ጥራትን ማሳደግ።
👉ቀደም ሲል ልማቱ በአንድ የግል ድርጅት ላይ ብቻ የተወሰነ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ሌሎች የግል ባለሃብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል። ይህም የዘርፉን ዘላቂነትና ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
#ባጭሩ፦ የሻይ ቅጠል ልማት በኦሮሚያ ክልል አዲስ የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ እየፈጠረ ያለ ስኬታማ የግብርና ኢኒሽየቲቭ ነው።
👉https://t.me/agriworld19
#ECTA #agriculturepostethiopia #agriculture #tealeaf #Oromia_Ethiopia