Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.96K subscribers
5.79K photos
30 videos
67 files
370 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
የቡና ምርትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ 43 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል፡- የኦሮሚያ ቡና አምራች ገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን
**********
የኦሮሚያ ቡና አምራች ገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ውስጥ የቡና ምርት ለዓለም ገበያ በማቅረብ 43 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን ገለፀ፡፡
የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ የምሥረታውን 25ኛ ዓመት በተለያዩ ኩነቶች እያከበረ ይገኛል፡፡
ዩኒየኑ ባለፈው ዓመት ውስጥ 3 ሺህ 700 ሜትሪክ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ 27 ሚሊዮን ዶላር፤ባለፉት 6 ወራት 1 ሸህ 728 ሜትሪክ ቶን ቡና በመላክ 16 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ችሏል፡፡
የዩኒየኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ደዲ እንደገለጹት፣ ተቋሙ ባለፈው ዓመት ብቻ 824 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን ካፒታሉንም ወደ 1.34 ቢሊዮን ብር አሳድጓል፡፡
ባለፉት 25 ዓመታት የመሠረታዊ ማኅበራቱን ቁጥር ከ34 ወደ 413፣ የአባላቱን ቁጥር ደግሞ ከ22 ሺህ ወደ 557 ሺህ በላይ ያሳደገው ዩኒየኑ ምርታማነትን ለማሳደግ ለአርሶ አደሮች ምርጥ የቡና ዝርያዎችን በማቅረብና ቀጣይነት ያለው የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ረገድ ውጤት ማመዝገቡን ገልፀዋል።
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ምርቱን ወደ "ስፔሻሊቲ" እና "ፕሪሚየም" ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ዩኒየኑ ከቡና ተረፈ ምርት ላይ የካርቦን ፕሮጀክት በመቅረጽ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን ይህም ለአካባቢው ጥበቃ ከማገዝ ባለፈ ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መፍጠር አስችሎታል።
ዩኒየኑ በቀጣይም ከኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር፣ ጥራቱን የጠበቀ የቡና ምርት ለዓለም ገበያ በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩት እንደሚሰራ አስታውቋል።
ቴርሞፕላን እና ካሪታዝ የተሰኙ የስዊዘርላንድ ካምፓኒና ድርጅት ከባለሰልጣኑ አመራሮች ጋር ተወያዩ

መጋቢት 16/2018 ዓ.ም
ኢቡሻባ

ካሪታዝ ስዊዘርላንድ የተባለ ዓለማቀፍ የሰብአዊ እና የልማት ድርጅት እና ቴርሞፕላን የተሰኘ በዓለማቀፍ ደራጃ የታወቀ የስዊዘርላንድ ካምፓኒ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በቡና ልማት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በቅድሚያ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር የኢትዮያ የቡና አመራረትና የገበያ ስርዓትን በፓወር ፖይንት የታገዘ ሰነድ አቅርበዋል፡፡ በዚህም ከልማት አኳያ በኢትዮጵያ ያለውን ባህላዊና ዘመናዊ የአመራረት ሁኔታን አብራረርተው ዘመናዊ ያመራረት ስርዓት እምብዛም እንዳልተንሰራፋ፣ በአነስተኛ የተበታተነ እርሻ ያመራረት ስርዓት እንዳለና ይህም ለመካናይዝድ ያመራረት ስርዓትም ይሁን ለአውሮፓው ከደን ነጻ አመራረት ደንብ መረጃ ለመያዝ አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ግን ምርታማነት እየጨመረ እንደመጣና ቀደም ሲል ከነበረው በሄክታር 7.5 ኩንታል ምርታማነት ወደ 9.5 ኩንታል እድገት እንደታየ አስረድተዋል፡፡

ከግብይት አንጻር ያለውንም ሲያቀርቡ ከቅርብ አማታት ወዲህ ሲተገበር የመጣው ማሻሻያ የእሴት ሰንሰለቱን በማሳጠር በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሰገኘ እና ከእነዚህም ጠቀሜታዎች አንዱ አርሷደሮች በቀጥታ ወደውጪ ኤክስፖር የማድር እድል መስጡን አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል፡፡ በቀጣይም አቅራቢን ከሰንሰለቱ በማስወጣት አሁን ያለውንም የእሴት ሰንሰለት በረጅም ጊዜ ክንውን የማሳጠር ስራ እንደሚሰራ አውስተዋል፡፡

ቴርሞፕላን ካምፓኒ በበኩሉ በቡናው ዘርፍ አዳዲስ የፈጠራ ምርቶችን በማቅረብ እንደሚታወቅና በዋናነት በአውቶማቲክ የቡና ማሽኖች ምርትና የቡና ግብአቶችን ቀጣይነትን የማረጋገጥ ቁርጠኝነት ውስጥ ያለ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ከዚህም ባሻገር የቡና አምራች ማኅበረሰቦችን ቦታቸው ድረስ በመሄድ መዋእለነዋይ በማፍሰስ የተሰማራም እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ካሪታዝ ስዊዘርላንድ የተባለው ድርጅት በበኩሉ ድኅነትን በመቀነስና ችግሮችን ተቋቁሞ የማለፍ ጥንካሬን በማስፈን ዘርፍ የተሰማራ እንደሆነ ተወስቷል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው እንቅስቃሴያቸው ሲናገሩም በግብርና የግብይት ስርዓት፣ የአየር ንብረት ተቋቋሚነት፣ ማኅበረሰብን በማብቃት ቀጣይነት ያለው የኑሮ ሁኔታ መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የእነዚህ አካላት ትብብር ተፈጻሚ ለማድረግ በካሪታዝ ስዊዘርላንድ እየተተገበረ ያለ ‹‹ልዩ ቡና›› የተሰኘ ፕሮጀክት (uniqueBean Project) ተፈጻሚ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ፕሮጀክቱ በባሌ ዞን ሀሬና ደን ላይ የሚገኙ የቡና አርሷደሮችን አቅም የቡና ጥራን በማሻሻል፣ የገበያ ተደራሽነታቸውን በማጠናከር፣ ቀጣይነት ያለውና የአየር ንብረት ጥበቃን ያማከለ አሰራርን በማስተዋወቅ አቅማቸውን የማጎልበት ስራ እየሠራ ያለ መሆኑ ተገልቷል፡፡

ሁለቱ አካላት ባለስልጣኑን ማነጋር ያስፈለጋቸውም ተቋማዊ ትስስርን ለማጠናከር፣ በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ስራዎችን ለማካፈል፣ በቀጣይ በጋራ የመስራ እድሎችን ለማሰስ፣ በኢትዮጵያ የቡና አመራረት ስርዓት፣ በዓለም ገበያ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ገበያ እምቅ ሃብትና የውጭ ገበያ ስርዓት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አሸናፊ ጌታሁን ዘግቦታል
Ethiopia-China Coffee Diplomacy: High-Level Chinese Delegation Explores Strategic Partnerships
Addis Ababa | March 26, 2026
— In a significant move to bolster international trade, a high-level Chinese delegation consisting of 21 influential investors met today with H.E. Dr. Adugna Debela, Director General of the Ethiopian Coffee and Tea Authority (ECTA).
The delegation, led by Madam Betty, Chairperson of the Ethiopia-China Friendship and Cooperation Committee, visited the Authority’s headquarters to discuss strategic frameworks for expanding the reach of Ethiopian coffee within the vast Chinese market.
Key Highlights of the Discussion:
• Strategic Promotion: The delegation is recognized for its pivotal role in introducing Ethiopian coffee to the Chinese public through diverse and innovative marketing channels.
• Rapid Market Growth: Dr. Adugna highlighted China’s meteoric rise as a primary consumer. In just three years, China has jumped from being the 33rd largest buyer of Ethiopian coffee to the 3rd largest within the last eight months alone.
• Strong Investor Appetite: Multiple Chinese firms have expressed a burgeoning interest in sourcing premium coffee directly from its birthplace, signaling a new era of "Coffee Diplomacy."
"China’s transformation into a top-tier destination for our coffee is a remarkable achievement. We appreciate the delegation's commitment to promoting our heritage, and we stand ready to provide all necessary support to ensure this partnership flourishes." — Dr. Adugna said.
The Road Ahead
The meeting concluded with a mutual commitment to strengthening the Ethiopia-China friendship. By leveraging the expertise of this delegation, Ethiopia aims to solidify its brand identity in China, ensuring that every cup of coffee served in Beijing or Shanghai carries the authentic flavor of the Ethiopian highlands.