Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.96K subscribers
5.79K photos
30 videos
67 files
370 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
በቅርቡ በኮሎምቢያ የተካሄደ አዲስ ጥናት እንደጠቆመው፤ የታሸገ ኮንቴይነር እና መጠነኛ የካርቦን ዳይኦክሳይድ (CO2) ጋዝ አጠቃቀም ተራ የሆኑ “ናቹራል” ቡናዎችን ወደ ከፍተኛ የልዩ (Specialty) ቡና ሊያሸጋግራቸው ይችላል።
ጥናቱ ክፍት በሆነ አየር እና በካርቦን ዳይኦክሳይድ የታገዘ (Closed Fermentation) ዘዴዎችን በማነፃፀር በኮሎምቢያ የቴክኖሎጂ ተቋም (SENA) እና በቫሌ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተከናወነ ነው። ተመራማሪዎቹ ከአንድ ማሳ የተለቀሙ የቡና ፍሬዎችን ከመድረቃቸው በፊት አምስት አይነት አፕሮች በመጠቀም Ferment በማድረግ፤ ቡናው ደርቆና ተቆልቶ በዓለም አቀፉ የልዩ ቡና ማህበር (SCA) ከ100 ነጥብ መለኪያ ተመዝኗል።
በዚህም ለ24 ሰዓታት በካርቦን ዳይኦክሳይድ በታፈነ ስፍራ የቆየው ቡና 86.90 አማካኝ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ ሲወጣ፤ ምንም አይነት ሂደት ያልተደረገበት ቡና ደግሞ 82.15 ነጥብ ብቻ አግኝቷል።
በታህሳስ 2025 በታዋቂው Scientific World Journal ላይ የታተመው ይህ ጥናት፤ በልምድና በጥቃቅን ሙከራዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ ለሚሰራው የልዩ ቡና ገበያ፣ በሳይንሳዊ መንገድ የተረጋገጠ እና በሰፊው ሊተገበር የሚችል አዲስ አቅጣጫ እንደሚያመላክት ተገልጿል።
ተመራማሪዎቹ እንዲህ ብለዋል፦
“ምንም እንኳ በቡና Fermentation ሂደት ላይ በርካታ ምርምሮች ቢደረጉም፣ አብዛኞቹ በላቦራቶሪ ቁጥጥር ስር ወይም በታጠበ ቡና (Wet processing) ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው፤ በፀሐይ በሚደርቅ (Natural) ቡና ላይ ያላቸው ተፈጻሚነት ውስን ነበር። በተለይም በካርቦን ዳይኦክሳይድ የታገዘ የFermentation ዘዴ በተፈጥሯዊ የቡና አዘገጃጀትና በኬሚካላዊ ይዘት ላይ ያለውን ተፅዕኖ በተጨባጭ የምርት ቦታዎች ላይ የሚያሳይ ሳይንሳዊ መረጃ እጥረት ነበረው።”
ይህ አዲስ ግኝት ለቡና አምራቾች ጥራትን ለማሻሻል ቀላልና ውጤታማ መንገድ ይጠቁማል ይለናል አዲሱ ጥናት።
CO2 Fermentation Boosts Natural-Process Coffee Scores in Colombian Trial
Daily Coffee News March 17, 2026
https://dailycoffeenews.com/.../co2-fermentation.../...
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች: እንኳን ለ1447ኛው የዒድ-አልፈጥር በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!!
አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
የኢዩ ካፌ ፕሮጀክት የስድስት ወራት አፈጻጸሙን ገመገመ፤ የቀጣይ ሶስት ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀመጠ
አዲስ አበባ | መጋቢት 15/2018
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ስር የሚንቀሳቀሰው የኢዩ ካፌ (EU-CAFÉ) ፕሮጀክት ላለፉት ሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቀቀ። በመድረኩ ላይ የፕሮጀክቱ ስድስት ወራት ጉዞ የተገመገመ ሲሆን፣ በቀጣይ ሶስት ወራት መጠናቀቅ ባለባቸው ተግባራት ላይም የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።
በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የክልል የቡናና ሻይ ተወካዮች፣ የምርምር ተቋማት ተወካዮች፣ የፕሮጀክቱ Focal Persons እና የፌዴራል ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚደረግባቸው ወረዳዎች የቡናውን ዘርፍ ለማሳደግና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ስራዎች ተከናውነዋል።
በባለፉት ስድስት ወራት የታቀዱ ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብና በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ እና በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን በመቅረፍ ረገድ ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑም ተመላክቷል።
ምንም እንኳን አፈጻጸሙ መልካም ቢሆንም፣ በቀሪዎቹ ሶስት ወራት ስራዎች በዝግታ እንዳይሄዱ አቶ ሰፊሳ የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች ሰጥተዋል፡-
1.  ቅንጅታዊ አሰራር፦ ቀሪ ስራዎች ይበልጥ በተናበበ እና በተቀናጀ ሁኔታ መከናወን እንዳለባቸው።
2.  የመረጃ አያያዝ፦ እስከ ዛሬ የተከናወኑ ተግባራት በበቂ መረጃ ተጠናቅረው ለቀጣይ ስራዎች እንደ ግብዓት እንዲያገለግሉ ማድረግ።
3.  ውጤት ተኮር ስራ፦ በቀሩት ጥቂት ወራት ውስጥ በታቀዱት ግቦች ላይ በትኩረት በመስራት ፕሮጀክቱን በስኬት ማጠናቀቅ።

ማጠቃለያ፦ የኢዩ ካፌ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የቡና ጥራትና ምርታማነት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት እየሰራ ያለ ፕሮጀክት ሲሆን፣ የአሁኑ ግምገማም የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።