Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.96K subscribers
5.8K photos
30 videos
67 files
370 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
ቡና ስልጠና ማዕከሉ ውጤታማነትና ያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ላይ ጥናት ቀረበ

መጋቢት 01/2018 ዓ.ም
ኢቡሻባ፤

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በቡና ስልጠና ማዕከሉ ውጤታማነትና ያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ላይ አበራ ፈይሳ የማማከር አገልግሎት በተባለ የግል ድርጅት ያስጠናውን ጥናት ለሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት እዲቀርብ አድርጓል፡፡

ጥናቱ በማዕከሉ በማሰልጠኛ ሞጁሎች ይዘት፣ የስልጠና አሰጣጥ፣ አቃፊነት፣ የስልጠና ክለጊዜያት በቂነትን ተመልክቷል፡፡

ከሞጁሎች ይዘት አንጻር 90 በመቶ አሰልጣኞች በጣም ጥሩ እንደሆነ፣ ዓለማቀፍ ስታንዳርድ የጠበቁ እንደሆኑና ኢንዱስትሪው የሚጠይቀውን ፍላጎት የሚያሟሉ ናቸው እንደሆኑ ጥናቱ አሳይቷል፡፡

ከስልጠና አሰጣጥ ጥራት አንጻር በተዳሰሰው ክፍል ደግሞ 76 በመቶ የሚሆኑ አሰልጣኞችና 70 በመቶ የሚሆኑ ሰልጣኞች መልካምና ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና ሂደት እንዳለ ተናግረዋል፡፡ ከስልጠና ክፍለጊዜ አንጻር ግን የንድፈ ሃሳቡንም የተግባር ስልጠናዎችንም በበቂ ሁኔታ ለመስጠት በቂ ጊዜ እንዳልተሰጠ ጥናቱ አስቀምጧል፡፡

ጥናቱ የማዕከሉን ውጤታማነትና ተጽእኖ በተመለከተ ስልጠና በሚሰጥባቸው የቡና ዘርፎች ያለው የቡና ሴክተር የአፈጻጸም ትክክለኝነት፣ ዓላም አቀፍ የቡና ገዢዎች ጋር ያለው ተግባቦት፣ የሰለጠነው የሰው ሃይል በራስ መተማመንና ውሳኔ ሰጪነት እንጨመረ አሳይቷል፡፡

እነዚህንም በመካን 22 በመቶ የሚሆኑት ሰልጣኞች የራሳቸውን የንግድ ስራ እንደከፈቱ እና 10 በመቶ የሚሆኑ ሴት ሰልጣኞች ኢንተርፕረኑር ወደ መሆን ደረጃ እንደደረሱ የተወሳ ሲሆን 13 በመቶ ነባር የቡና ንግድ ስራዎች ማስፋፋት እንደታየባቸው የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡

በአጠቃላይ እሴት ጭመራ ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የገቢ መሻሻል፣ በገበያ ተወዳዳሪነትን በማስፈን ረገድ የማዕከሉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነና እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡

መሻሻል እና መታከል ያለባቸውንም ጎኖችንም ጥናቱ ተመልክቷል፡፡ በዚህም መሠረት የስልጠና ፍላጎትና የማዕከሉ አቅም አለመመጣጠን፣ የስልጠና ማቴሪያሎች በበቂ ሁኔታ አለመኖር፣ የአሰልጣኞች የተግባቦት ክህሎት ውሱንነት፣ ውስን የሆኑት ስልጠናዎች ላይ ብቻ የሰልጣኝ ብዛት መኖር፣ የማዕከሉ የቦታ ስፋት ጥበት፣ የጥራት ሰርቲፊኬት ሰጪነት ማንዴት አለመለየት የመሳሰሉትን ጥናቱ ለይቷል፡፡

በቀጣይ መደረግ ያለባቸውንም ሲያወሳ የአየር ንብረት ለውጥ እና ኢንተርፕሬነር የመሳሰሉ ስልጠናዎች ቢካተቱ፣ ስልጠና አሰጣጡ ዲጂታላይዝ ቢሆን፣ ማዕከሉ ወደቡና አብቃይ አካባቢዎች ቢስፋፋ፣ ከሚመለከታቸው የክልልና ዓለም አቀፍ የግልና የመንግስት ድርጅቶች ጋር በቅንጅት መስራት የሚሉትን ጥናቱ እንደመፍትሄ ሃሳብ አቅርቧል፡፡

ጥናቱ ሲቀርብ በቦታው የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ ባለሰልጣኑ ጥናቱን ያስጠናው የማዕከሉን ጥራት ለማሻሻል ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ጠንካራዎቹን በማጠናከር ደካማ ጎኖችን በመቅረፍ የተሻለ ማሰልጠኛ ተቋም ለማድረግ በማለም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉን ወደቡና አብቃይ ክልሎች ከማስፋት አንጻር ስራው እንደተጀመረና በጅማ ዞን አንድ ማዕከል እንደተከፈ ተናግረዋል፡፡

በማቴሪያል ከማሟላት አንጻር የሀገር ውስጥም የውጪም አጋርና ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር በርካታ የቁሳቁስ እገዛዎችን ማግኘት እንደተቻለና በዚህም በቅንጅት የመስራቱን ተግባር ባለስልጣኑ አስቀድሞም የሄደበት ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አሸናፊ ጌታሁን እንደዘገበው
የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣንን ጎበኙ!!
መጋቢት 02/2018
የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በመገኘት የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸው ወቅት የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በመሥሪያ ቤቱ እየተከናወኑ ያሉ አበይት ተግባራትን ለባንኩ አመራሮች አስረድተዋል።
በተለይም በዘመናዊ መልክ የተገነባውን የባለሥልጣኑን አዲስ ሕንፃ፣ የቡና ማሰልጠኛ ማዕከልንና የኦንላይን የግብይት ቁጥጥር ሥርዓትን ለጉብኝቱ ቡድን በዝርዝር አስጎብኝተዋል። ይህ ጉብኝት በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን የሥራ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የቴክኖሎጂ ለውጦችን ለማስገንዘብ ያለመ ነው።
Higher level officials of Bunna International Bank Visits Ethiopian Coffee and Tea Authority!!
Mr. Mulugeta Alemayehu, President of Bunna International Bank, accompanied by the bank’s senior executive team, conducted an official working visit to the Ethiopian Coffee and Tea Authority. During the visit, the Director General of the Authority, H.E Dr. Adugna Debella, provided a comprehensive briefing on the institution's key strategic initiatives and ongoing projects.
The delegation visited several milestone developments, including the Authority's state-of-the-art headquarters, the modern Coffee Training Center, and the newly implemented online market regulatory system. This visit highlights the growing synergy between the financial sector and the coffee industry, showcasing the technological advancements driving Ethiopia's coffee value chain forward. Reported By Sahlemariam G/medhin