በጉጂ ዞን የቡና ልማትን ለማሳደግ የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት የሚያስችሉ የቡና ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
በጉጂ ዞን የቡና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ችግኞች መዘጋጀታቸውን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በጽህፈት ቤቱ የቡናና ሻይ ልማት ባለሙያ ብርሀኑ ፈይሳ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በዘንድሮው ዓመት የዞኑን የቡና ልማት ማሳደግ የሚያስችሉ ከ61 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለማዘጋጀት ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል።
ባለፉት ሰባት ወራትም ከ70 ሚሊየን በላይ የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን በማዘጋጀት ከእቅድ በላይ መፈፀም መቻሉን አብራርተዋል።
የተዘጋጁት ችግኞች በመጪው ክረምት የሚተከሉ ሲሆን የተሻሻሉና የቡና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በሲዳማ ክልል የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የቡና ችግኞች ለተከላ ተዘጋጅተዋል
በሲዳማ ክልል የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የቡና ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማቅመም ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መስፍን ቃሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከተለያዩ የግብርና ምርምር ማዕከላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
ለመጪው ክረምት የሚተከሉ ከ34 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የቡና ችግኞች መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል፡፡
ችግኞቹ የተዘጋጁት በክልሉ መንግስት፣ በማህበራት፣ በግል ባለሃብቶች እና 15ሺህ በሚጠጉ አርሶ አደሮች አማካኝነት መሆኑንም ገልጸዋል፡:

በኦሮሚያ ክልል የተሻሻሉና የአካባቢን ስነ-ምህዳር ታሳቢ ያደረጉ የቡና ችግኞች ይተከላሉ
በኦሮሚያ ክልል የተሻሻሉና የአካባቢን ስነ-ምህዳር ታሳቢ ያደረጉ የቡና ችግኞች እንደሚተከሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የቡናና ፍራፍሬ ዘርፍ አስተባባሪ መሐመድሳኒ አሚን ገለጹ።
አቶ መሐመድሳኒ አሚን በክልሉ ባለፉት ዓመታት የቡና ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች ሲናወኑ መቆየታቸውንና በተያዘው የበልግ የዝናብ ወቅት የተዘጋጁ የቡና ችግኞችን ከ300ሺህ በሄክታር በሚበልጥ አዲስ መሬት ላይ ይለማሉ ብለዋል።
የቡና ዝርያዎቹ ከግብርና ምርምር ተቋማት የተለቀቁ እንዲሁም የአካባቢን ስነ-ምህዳር ከግምት ያስገቡ እና የተሻለ ምርት የሚሰጡ መሆናቸውንም ለኢዜአ ገልጸዋል።
ስራውን ስኬታማ ለማድረግ በየደረጃው ከሚገኙ የግብርና ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
በክልሉ ባሌ ዞን የቡና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ያላቸው ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሙአዊያ ፉአድ ናቸው።
ከግብርና ምርምር ማዕከላት የወጡ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በስፋት መትከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
እነዚህን ዝርያዎች በመጠቀም ባለፉት ሰባት ወራት በወረዳዎቹ በተደረገው እንቅስቃሴ ከ41 ሚሊየን በላይ የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ያላቸው ችግኞች ማዘጋጀት መቻሉን አስረድተዋል።
በአሁኑ ወቅት በዞኑ እየጣለ ያለውን የበልግ ዝናብ በመጠቀም የቡና ችግኝ ተከላ መጀመሩን ገልጸው በዚህም 5ሺህ 700 ሔክታር አዲስ መሬት እንደሚለማ አስታውቀዋል።
በልማቱም ከ20 ሺህ በላይ አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑን ጠቁመው የቡና ችግኝ ተከላውም ከአዲስ መሬት በተጨማሪ ያረጁና ከምርት ውጭ የሆኑ የቡና ተክሎችን በመንቀል ጭምር በምትኩ ተከላው እንደሚካሄድ አመልክተዋል።