Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.73K subscribers
5.48K photos
30 videos
66 files
358 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
አገራችን ራሷን በዘመናዊ ላቦራቶሪ ስላደራጀች እና የበርካታ ዝርያዎች ባለቤት በመሆኗ የውድድሩን ይዘት ከፍ ያደርገዋል!!!
ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ

ጥር 15/2018
አዲስ አበባ

በርካታ የውጭ እና የአገር ውስጥ እንግዶች የሚሳተፉበትን የAFCA/ የአፍሪካ ቡና አምች ሃገራት ማህበር ጉባኤ እና ኤግዚቢሽን ዘንድሮም ለማካሄድ አገራችን ዝግጅቷን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።
የዚሁ ጉባኤ እና ኤግዚቢሽን አካል የሆነው Taste of Harvest የተሰኘው ልብ አንጠልጥል እና ምርጥ ቡናዎች ተለይተው እውቅና የሚያገኙበት ውድድርም በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል ከኢትዮጵያና ከውጭ  በመጡ ከስምንት  በላይ  የላቀ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች አማካኝነት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ማዕከሉን ከውጥኑ ጀምረው እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በየቀኑ በመገኘት ያለመታከት የሚከታተሉት ክቡር ዋና ዳ/ር ዶ/ር አዱኛ የዚህን ውድድር ሁኔታ ለመታዘብ እና አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮችም በቅርብ ተገኝተው አቅጣጫ ለመስጠት ባሉበት በቦታው አግኝተናቸው ስለ ውድድሩ ጥቂት እንዲሉን ጠይቀናቸው እንዲህ አጫወቱን።

ኢትዮጵያ ይህንን የአፍካን ጉባኤ በተደጋጋሚ፣ የIACO እንዲሁም ሌሎች አለማቀፍ የቡና ኮንፍረንስ እና ኤግዚቢሽኖችን በተለመደው ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ በከፍተኛ ብቃት ስታዘጋጅ መቆየቷን እንደ መግቢያ አነሱልን። እንደ የIACO አባልነታችን ካሉ 25 አባል አገራት ኢትዮጵያ የመሪነቱን እና ወሳኙን ድርሻ ይዛለች ያሉን ሲሆን፤ የአሁን የዘንድሮውን ሁነት ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ፣ ድንቅ፣ ልዩ ሆና አሸብርቃ በተገኘችበት እንግዶቻችንን ለመቀበል መዘጋጀታችን ነው ብለዋል። የዚሁ ታላቅ ሁነት አካል የሆነው  ውድድርም በአፍሪካ ለ23ኛ ጊዜ ሲካሄድ 232 የኢትዮጵያ የቡና ሳምሎች/የቡና ናሙናዎች / ቀርበው ብቃታቸው በተመሰከረላቸው ባለሙያዎቻችን ውድድሩ በመካሄድ ላይ ይገኛል ብለውናል።
ክቡር ዋና ዳይሬክተር እንደተናገሩት ይህ ውድድር መዘጋጀቱ ተጨንቀን እና ጨምቀን ያወጣናቸውን እውቅ ባለሙያዎች አቅማችንንም ለመላው የውጭ ማህበረሰብ ለማሳየት፣ በላቀ ጥረት በዘመናዊ መሳሪያዎች እና የሰው ኃይል የተሟላውን የቅምሻና ልዩ የቡና ማሰልጠኛ ማዕከላችንን ለመመልከት እንዲችሉ፤ ከምንም በላይ ደግሞ የአገራችንን ገፅታ ለመገንባትና ያለችበትንም አስደናቂ የለውጥ ደረጃ ለማሳየት መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው ሲሉ አጫውተውናል። አገራችን ራሷን በዘመናዊ ላቦራቶሪ ስላደራጀች እና የበርካታ ዝርያዎች ባለቤት በመሆኗም የውድድሩን ይዘት ከፍ ያደርገዋል ሲሉ አስረድተውናል።

የቡና  ናሙናዎቹ  ከተለያዩ የኢትዮጵያ ቡና አምራች ክልሎች ወረዳዎችና ቀበሌዎች በቡና አምራቾች ላኪዎችና ኮኦፐረቲቭስ  የቀረቡ መሆናቸውን ደግሞ ወ/ሮ ባምላክ መለሰ በአፍካ  የቴሰት አቭ  ሃርቨስት  የፕግራም ሱፐርቪዥን አስተባበሪ  ባለሙያ ነግረውናል ፡፡  100  የቡና ናሙናዎች  ናሽናል ፕሮሰስድ የተደረጉ ፤43 የቡና ናሙናዎች የታጠቡ ፤ 37 የቡና ናሙናዎች ሃኒ ፕሮሰስድ  እና 46 የቡና ሳምፕሎች ደግሞ ኤክፐርመንታል ፕሮሰስድ   ናቸውም ብለዋል ፡፡
እንደ አስተባባሪዋ ገለጻ የቡና ደረጃ ውድድር በየአመቱ  በአፍካ  አባል ሃገራት የሚካሄድ ሲሆን  የዛሬው ውድድር    እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር  የ2026 ዓ/ም  ውድድር  የመጀመሪያው ምእራፍ ሲሆን  ሁለተኛው ምእራፍ ደግሞ  ፌብሩዋሪ 2026 ይካሄዳል ፡፡  በዚህ ውውድር ያለፉ ቡናዎች  በፌብዋሪ  በሚካሄደው የሁለተኛ ምእራፍ የቡና ውድድር ከአፍካ  ቡናዎች ጋር  ተወዳደረው  የላቀ ደረጃ ያገኙ ቡናዎች መለያ ቁጥር  ተሰጥቶ እውቅናና ሰርተፊኬት  በማግኘት በቀጥታ   በአፍካ በኩል ለጨረታ ይቀርባል ብለዋል ፡፡  እንደ አስተባባሪዋ  ማብሪያ  ከአሁን በፊት  የነበረው  ተሞክሮ  ቡናዎች ተወዳድረው  ውድድሩን ላለፉ ቡናዎች እውቅናና የምስክር ወረቀት ካገኙ በኋላ ለገበያ ይቀርቡ ነበር ብለዋል ፡፡ ይህ የደረጃ  አሸናፊነት  ደረጃ  እውቀና  ለአንድ አመት ብቻ እንደሚያገለግልም  ወ/ሮ ባምላክ ጠቁመውናል ፡፡

‎በደቡብ ቤንች ወረዳ የኮረሪማ ቅመም ልማት በከፊል (በምስል)


ምስል፡ የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን
ጥር 22/2018

ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሚላክ ቡና ደን ሳይመነጠር የተመረተ እንደሆነ አረጋግጦ የመላክ ስራ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጀመራል ተባለ።

ህብረቱ ወደ አባል ሀገራቱ የሚላክ የግብርና ምርት ከደን ምንጣሮ ነፃ መሆን እንዳለበት የሚያስገድደውን ህግ ከአንድ ዓመት በኋላ ስራ ላይ ማዋል እንደሚጀምር ማሳወቁ ይታወሳል።

የአውሮፓ ህብረት በተለይ በታዳጊ ሀገራት የተመረቱ ዘጠኝ የግብርና ምርቶች ወደ አባል ሀገራቱ መግባት የሚችሉት፤ ከደን ምንጣሮ ነፃ በሆነ መሬት ላይ ተዘርተው የበቀሉ ከሆነ እና ለዚህም ማረጋገጫ ሲያቀርቡ ብቻ እንደሚሆን በመጥቀስ ይህንኑ የተመለከተ የሚል ህግ አውጥቷል።

በዚህ ክልከላ ውስጥ ከተካተቱ የግብርና ምርቶች ኢትዮጵያን የሚመለከተቱት ቡና እና አኩሪ አተር መሆናቸውን ሠምተናል።

ህጉ ከባለፈው ወር አንስቶ ስራ ላይ ይውላል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ተግባራዊ የሚሆንበት ጊዜ በአንድ ዓመት ተራዝሟል።

ኢትዮጵያም በተሰጠው አንድ ዓመት ጊዜ ወደ ህብረቱ የምትልከው ቡና ደን ሳይመነጠር የተመረተ እንደሆነ እያረጋገጠች ምስክር ወረቀት ለማዘጋጀት እየሰራች እንደምትገኝ ተጠቅሷል።

አሁን ላይ እያንዳንዱ የቡና እርሻ መሬት ወደ መረጃ ቋት እየገባ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ቡና ፤ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ፤ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተጋይ ኑሩ ነግረውናል።

በኢትዮጵያ ከሚመረተው ቡና ከ90 በመቶ በላዩ ከአርሶ አደሮች የሚገኝ እንደሆነ አቶ ታጋይ ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ ቡናውን የሚያመረቱበት መሬት ስፋት እጅግ አነስተኛ እና የተበጣጠሰ በመሆኑ የመረጃ ማሰባሰቡን ስራ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል።

የተራዘመውን የአንድ ዓመት ጊዜ በመጠቀም ግን የሁሉንም አርሶ አደሮች መሬት ወደ መረጃ ቋት በማስገባት ቡናቸው ደን ሳይመነጠር የተመረተ እንደሆነ የሚያረጋግጠውን የምስክር ወረቀት መስጠት እንደሚጀመር ነግረውናል።

የአውሮፓ ህብረት ያወጣው ህግ የቡና አመራረት ከህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ነፃ ሊሆን ይገባዋል የሚል ድንጋጌንም ያካተተ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህንንም የማረጋገጥ ማስረጃ ለማቅረብ የኢትዮጵያ ቡና ፤ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እየሰራሁ ነው ብሏል።

ሸገር ኤፍ ኤም
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል occupational Standard ሰነድ በተዘጋጀበት ወቅት
ጥር 23/2018 ዓ.ም
አዳማ
የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም አቅም በመጠቀም ሀገሪቷን የዘርፉ የስበት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል

ሀዋሳ፤ ጥር 23/2018

የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም አቅም በመጠቀም ሀገሪቷን የዘርፉ የስበት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸው ተመላከተ።

የቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ቡና ለቱሪዝም መዳረሻነት ለማዋል የሚያስችሉ ስራዎችን ለማጠናከር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቡና ቱሪዝም ሴሚናርና የመስክ ምልከታ በሲዳማ ክልል ተካሄዷል።

በሚኒስቴሩ የቱሪዝም መስህብ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሳ ከድር እንደገለጹት የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም አቅም በመጠቀም ሀገሪቷን የዘርፉ የስበት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።

የተጀመሩ ትልልቅ የቱሪዝም ስራዎችን ለማጠናከር የፖሊሲ አቅጣጫ፣ የተቀናጀ ትብብርና ስልት ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አውስተው እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን ለማስቀጠል ያሉ ሀብቶችን የመለየትና የመጠቀም ስራ ይሰራል ብለዋል።

እንዲሁም አዳዲስ ያልተዳሰሱ ዘርፎችና ዕምቅ አቅሞች የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው ከዚህ ውስጥ አንዱ ቡናን በተለየ አቀራረብ ለቱሪዝም መዳረሻነት ለማዋል የሚያስችል ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።

የቡና መገኛ በመሆናችን ከባህልና ታሪክ ጋር ያለንን ማህበረሰባዊ ትስስር እንዲሁም የምርት ሂደቱ ከእርሻ እስከ ቅምሻ ድረስ ያለውን ሂደት በተቀናጀ መንገድ ለቱሪዝም መዳረሻነት ለማዋል በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የቱሪስት መስህብና መዳረሻ ልማት ዳይሬክተር አቶ ካሳ መንገሻ በበኩላቸው የክልሉ የቡና ልማት ለቱሪዝም መዳረሻነት አማራጭ አቅም መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ ኢዜአ