Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.74K subscribers
5.49K photos
30 videos
66 files
358 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!!
ጥር 14/2018
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ እና የባንኩ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ሲሆኑ በሁለቱም ተቋማት በኩል ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተውበታል፡፡
በስምምነቱ ወቅት ክቡር ዶ/ር አዱኛ እንደተናገሩት ቡና አለማቀፍ ሰብል እና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ከመሆኑ አንጻር በልዩ ትኩረት እየተሰራበት የሚገኝ መሆኑን እና ባለስልጣን መ/ቤቱ የተቋቋመበትን ዝርዝር ዓላማ አብራርተዋል፡፡ ዘርፉ በተለይም ከባለፉት አምስት አመታት ወዲህ በልማቱም ሆነ በግብይቱ በኩል እያስመዘገበ ያለውን ውጤት፣ ገበያ መዳረሻ ከማስፋት አንጻርም የተሰራውን ስራ ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው ኣመትም በግማሽ አመት ብቻ ከ1.35 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቁመው በበጀት ዓመቱ ማብቂያም የታቀደው 3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማስገነት በስፋት እየተሰራበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር የተፈረመው ይህ ስምምነትም የዚሁ አካል ሊሆን እንደሚችል እና በተለይ አርሶ አደሩ ያሉበትን የግብኣት ችግሮች ለመፍታት፣ እሴት ሰንሰለቱም ላይ የሚታዩ አንዳንድ ጉድለቶችን ለመሙላት ትልቅ አስተዋጽዖ ሊኖረው እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ክቡር አቶ ሙሉጌታ በበኩላቸው ይህ ስትራቴጂካዊ ስምምነት መፈረሙ በባንኩ በኩል እንደትልቅ ስኬት የሚታይ እና ወደፊትም ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማምጣት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Researcher proposes renaming “Coffee Arabica” to “Ethiopian Coffee”
ኮፊ አረቢካ ከሚባል ምንጩ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ 'የኢትዮጵያ ቡና' መባል አለበት። አራት ነጥብ።
እኔ በደስታ እላለሁ። እናንተስ?

+++++++++++++++++++++++++
The name “Coffee Arabica” should be renamed “Ethiopian coffee” to honor Ethiopia’s historical and scientific contributions as coffee’s birthplace, said a researcher in the area.

Speaking to Gazette Plus, coffee researcher Solomon Tekle emphasized that despite Ethiopia being widely documented as the origin of coffee, it has not received the recognition or equitable benefits it deserves.

He pointed out that “Coffee Arabica,” native to Ethiopia, is marketed under a name that does not reflect its true source. Solomon criticized other countries for making unsubstantiated claims about being the origin of coffee.

The researcher further urged Ethiopian authorities and stakeholders to leverage the scientifically proven data supporting Ethiopia’s status as the cradle of coffee to secure UNESCO recognition for its coffee heritage.

“Available historical and scientific sources clearly show that coffee originated in Ethiopia,” Solomon stated, underscoring the importance of acknowledging this heritage globally.

#gazette_plus_english
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ሠራተኞች ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ አደረጉ!
                                                                                                                                                                                  (ጥር15/2018 ዓ.ም)
አ/አበባ
                                                                                                                                                                                            ከባለስልጣኑ በጎ ፈቃደኞች የተሰባሰቡትን ወደ አራት(4) ጆንያ አልባሳቶችን እና ጫማዎችን በዛሬው ዕለት በማዕከሉ በመገኘት ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በባለስልጣን መ/ቤቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ስራ አስፈፃሚ በኩል የተሰባሰበ ድጋፍ መሆኑን የስራ አስፈፃሚው ኃላፊ አቶ ፍፁም መንገሻ የገለጹ ሲሆን በቀጣይም ይህን መሰሉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡ ለማዕከሉ ድጋፉ በተሰጠበት ወቅት አቶ ሰፊሳ አባቡ የባለስልጣን መ/ቤቱ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ በቦታው በመገኘት ከማዕከሉ አስተባባሪዎች ጋር አጭር ውይይት አድርገዋል፡፡
                                                                                                                                                                                         ወ/ሮ የአብስራ ኃይሌ የማዕከሉ እንግዳ ተቀባይ እና አስተባባሪ እንደገለፁት በማዕከሉ ወደ 420 ወንዶች እና 250 ሴቶች በድምሩ 670 የሚደርሱ የአዕምሮ ህሙማን ያሉ ሲሆን ከአሁን በፊት ወደ 450 የሚደርሱት ህሙማን ሙሉ ለሙሉ ጤንነታቸው ተመልሶ ወጥተዋል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ወደ 425 ህሙማን ድነው ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው እንደሚኖሩ በውይይቱ ወቅት አብራርተዋል፡፡ በማዕከሉ በቋሚነት አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና ዶክተሮች እና የስነ-ልቦና ህክምና ባለሙያዎች እንዳሉ የገለፁት አስተባባሪዋ በስተመጨረሻ ስለተደረገላቸው ድጋፍ በማዕከሉ ስም ከልብ አመስግነዋል፡፡