የጣልያን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቡድን የባለስልጣን መ/ቤቱን ጎበኙ!!
ጥር 12/2018
ኢ/ቡ/ሻ/ባለሰልጣን
ከጣልያን ውጭ ጉዳይ መ/ቤት፣ ጣልያን ሮም ከሚገኘው እና እዚህ አዲስ አበባ ከሚገኘው የጣልያን ልማት ትብብር ኤጀንሲ/Italian Agency for Development Cooperation እንዲሁም የጣልያን ኦዲተሮች ቦርድ የተሰኘው መቀመጫውን ሮም ያደረገ መ/ቤት የተወከሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት በባለስልጣን መ/ቤቱ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ያነጋገሩት ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክ/ዋና ዳ/ር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ የቡና ምርትን ለመጨመር በአገራችን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲሁም በተሰሩት የሪፎርም ስራዎች በኤክስፖርት ግኝት እየተመዘገቡ ያሉትን ከፍተኛ ውጤቶች በተመለከተ ሰፊ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት መንግስት ባከናወነው ከፍተኛ ስራዎች ለኢንቨስትመንት እና ንግድ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ተናግረዋል።
እንግዶቹ በባለስልጣን መ/ቤቱ የሚገኘውን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከልም ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት በሳይንሳዊ የቡና አቆላል፣ በባሬስታ እና በቅምሻ ዘርፎች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝና በቅርብ ጊዜ የቡና ኤክስፖርት አስተዳደር ስልጠና መስጠት እንደጀመረም ተገልጾላቸዋል፡፡ ስልጠናዎቹን ለሀገር ውስጥ ሰልጣኞች ብቻ ሳይሆን ከውጭ ሀገራት ለመጡ ሰልጣኞችም እየተሰጡ እንደሆነ የተብራራ ሲሆን የስልጠና አሰጣጥ ሂደቱም በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ፤ ከዚህም ባሻገር ሰልጣኞች ተመርቀው ከመውጣታቸው በፊት የቡና ኢንዱስትሪዎችን እንዲጎበኙ በማድረግ እውቀትና ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ የማድረግ ስራም እንደሚሰራ በስፋት ተብራርቷል፡፡

ደረቅ ቡናን ጥራቱን ጠብቆ በብዛት በማዘጋጀት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል፦አቶ አስራት መኩሪያ
የክልሉ ቡና ሻይ ቅ/ቅ/ባለስልጣን ከምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ጋር በመተባበር የደረቅ ቡና ምርት ዝግጅት ስልጠናና የ 6 ወራት አፈጻጸም ላይ ከዞንና ከወረዳ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎችጋር እያካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ ደረቅ ቡናን በጥራትና በብዛት አዘጋጅቶ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ሰፊ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸው አሁንም መታረም የሚገባቸው ክፍቶችን በመለየት ማረም ይገባል ብለዋል።
በዘንድሮው ዓመት እስካሁን 18 ሺህ ቶን ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የጠቀሱት አቶ አስራት ይኽም ከሚጠበቀው አንጻር አነስኛ በመሆኑ የምርት ክምችት እንዳይኖር ሁሉም መዋቅር በቅንጅት በማጣራት ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲገባ መሥራት እንደሚገባ በአጽንኦት አንስተዋል።
አቶ አስራት አክለውም በደረቅ ቡና ምርት ዝግጅት አኳያ ከጥራት አንጻር የሚታየውን ጉድለትና የተዘጋጁ ምርቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ እንዲገቡ የማድረግ ክፍተት መንስኤዎች በየአካባቢው በመለየት በስልጠናና በ6 ወራት የአፈጻጸም መድረክ በጥልቀት ውይይት ተደርጎባቸው የጋራ መፍትሔ እንዲቀመጥ አሳስበዋል።
በመድረኩ የዞንና ከተማ አስተዳደር የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የወረዳ የቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ምርት ዝግጅትና ገበያ ልማት ቡድን መሪዎች እየተሳተፉ ሲሆን የደረቅ ቡና ምርት ዝግጅትና ጥራት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ የስልጠና ሠነድ በባለስልጣኑ የቡና ሻይ ቅ/ ቅ ምርት ዝግጅት ባለሙያ በሆኑት አቶ ሽመልስ አራጋው እየቀረበ ይገኛል።
ደ/ምዕ/ ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው

በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!!
ጥር 14/2018
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ እና የባንኩ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ሲሆኑ በሁለቱም ተቋማት በኩል ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተውበታል፡፡
በስምምነቱ ወቅት ክቡር ዶ/ር አዱኛ እንደተናገሩት ቡና አለማቀፍ ሰብል እና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ከመሆኑ አንጻር በልዩ ትኩረት እየተሰራበት የሚገኝ መሆኑን እና ባለስልጣን መ/ቤቱ የተቋቋመበትን ዝርዝር ዓላማ አብራርተዋል፡፡ ዘርፉ በተለይም ከባለፉት አምስት አመታት ወዲህ በልማቱም ሆነ በግብይቱ በኩል እያስመዘገበ ያለውን ውጤት፣ ገበያ መዳረሻ ከማስፋት አንጻርም የተሰራውን ስራ ተናግረዋል፡፡ በዘንድሮው ኣመትም በግማሽ አመት ብቻ ከ1.35 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቁመው በበጀት ዓመቱ ማብቂያም የታቀደው 3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማስገነት በስፋት እየተሰራበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር የተፈረመው ይህ ስምምነትም የዚሁ አካል ሊሆን እንደሚችል እና በተለይ አርሶ አደሩ ያሉበትን የግብኣት ችግሮች ለመፍታት፣ እሴት ሰንሰለቱም ላይ የሚታዩ አንዳንድ ጉድለቶችን ለመሙላት ትልቅ አስተዋጽዖ ሊኖረው እንደሚችል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ክቡር አቶ ሙሉጌታ በበኩላቸው ይህ ስትራቴጂካዊ ስምምነት መፈረሙ በባንኩ በኩል እንደትልቅ ስኬት የሚታይ እና ወደፊትም ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመቅረፍ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማምጣት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Researcher proposes renaming “Coffee Arabica” to “Ethiopian Coffee”
ኮፊ አረቢካ ከሚባል ምንጩ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ 'የኢትዮጵያ ቡና' መባል አለበት። አራት ነጥብ።
እኔ በደስታ እላለሁ። እናንተስ?
+++++++++++++++++++++++++
The name “Coffee Arabica” should be renamed “Ethiopian coffee” to honor Ethiopia’s historical and scientific contributions as coffee’s birthplace, said a researcher in the area.
Speaking to Gazette Plus, coffee researcher Solomon Tekle emphasized that despite Ethiopia being widely documented as the origin of coffee, it has not received the recognition or equitable benefits it deserves.
He pointed out that “Coffee Arabica,” native to Ethiopia, is marketed under a name that does not reflect its true source. Solomon criticized other countries for making unsubstantiated claims about being the origin of coffee.
The researcher further urged Ethiopian authorities and stakeholders to leverage the scientifically proven data supporting Ethiopia’s status as the cradle of coffee to secure UNESCO recognition for its coffee heritage.
“Available historical and scientific sources clearly show that coffee originated in Ethiopia,” Solomon stated, underscoring the importance of acknowledging this heritage globally.
#gazette_plus_english