Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.74K subscribers
5.49K photos
30 videos
66 files
358 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት መሠረት ዕሴት የታከለበት ቡናን መላክ ተጀምሯል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018

በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት መሠረት ዕሴት የታከለበት የኢትዮጵያ ቡናን ለአፍሪካ ሀገራት ገበያ መላክ መጀመሩን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

የአፍሪካ ሕብረት መረጃ እንደሚያሳየው የአፍሪካ ሀገራት 85 በመቶ ምርታቸውን ለአውሮፓ፣ እስያ፣ ሰሜንና ላቲን አሜሪካ ገበያ የሚልኩ ሲሆን በአንፃሩ የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጣቸው ከ15 በመቶ ያልበለጠ ነው።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራም የሀገራቱን የእርስ በእርስ የንግድ ትስስር በማሳለጥ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን እንደሚያሳደግ ታምኖበታል።

አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቱም የአፍሪካ ሀገራትን የንግድ ታሪፍና መሰናክል በማስወገድ ወጥ በሆነ የአሰራር ሥርዓት የእርስ በእርስ የገበያ ትስስርን ማሳለጥ ዋና ዓላማው ያደረገ ነው።

ይህም የአህጉሪቱን አባል ሀገራት የንግድ ልውውጥ በማሳደግ፣ የኢንዱስትሪ ዕድገትን በማፋጠንና ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የአፍሪካን ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ አለው።

በዚህም ኢትዮጵያ በአህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቱ መሰረት ከመስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ገበያ ምርቶችን መላክ ጀምራለች።

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር ለኢዜአ እንዳሉት፤ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ሥምምነት መሰረት የኢትዮጵያ ቡና ገበያ መዳረሻን ለማስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የአፍሪካን ሰፊ የገበያ ዕድል ለመጠቀም የኢትዮጵያን ጥሬ ቡና ከመላክ ይልቅ ዕሴት ጨምሮ ለማቅረብ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚህም በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት ዕሴት የተጨመረበትን ቡና የመላክ ጅማሮን የበለጠ ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አዳዲስ የቡና ገበያ መዳረሻዎችን እያሰፋች ነው ያሉት አቶ ሻፊ፤ ለአብነትም በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያን የቡና ገበያ መዳረሻ ከ64 ሀገራት በ2017 ዓ.ም ወደ 84 ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

የኢትጵያን ነባር የቡና ገበያ መዳረሻን በማጠናከርና አዳዲስ ገበያን ለማስፋት በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

ቻይናን ጨምሮ አስር የእስያ ሀገራት የኢትዮጵያን ቡና እየገዙ እንደሚገኝ ጠቁመው በቀጣይም ቡና ላይ ዕሴት በመጨመር የአፍሪካ እና እስያ ገበያን ለመጠቀም ከኢትዮጵያ ቡና ላኪዎችና የአውሮፓ ባለሃብቶች ጋር በመቀናጀት ዕሴት ጨምሮ መላክ ላይ እንዲሳተፉ ይሰራል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርና በተለይም በቡና ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እያሳደጉ ነው
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 30/2018
ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርና በተለይም በቡና ዘርፍ ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነትና ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እያሳደጉ መሆኑን የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ።
ቻይና የኢትዮጵያ ቡና መዳረሻ በመሆን ባለፉት አምስት ዓመታት ከ33ኛ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ ማለቷ ታውቋል።
የኢትዮጵያን ቡና በቻይና እና በዓለም ገበያ የማስተዋወቅ ዓላማ ያለው የንግድና የኢኮኖሚ ትብብር በቻይና ጁጆ ከተማ ተካሂዷል።
የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና በግብርናው ዘርፍ ያላቸው ትብብር ከንግድ ባለፈ ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
ለዚህ ትብብር መጠናከርና ለቡና ወጪ ንግድ ዕድገት መነሻ ከሆኑት መካከልም የቻይና የቡና መዳረሻነት ማደግ፣ የነፃ ታሪፍ ዕድል፣ የቴክኖሎጂ እና የዕውቀት ሽግግር፣ የኢ-ኮሜርስ ትስስር እንዲሁም የሁናን ግዛት የንግድ ማዕከልነት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ መንግሥት የግብርና ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ለዚህም የምርት ጥራትንና መጠንን ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን፣ አዳዲስ ኢኖቬሽኖችንና የግብርና ግብዓቶችን በስፋት ጥቅም ላይ ማዋል ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቻይና የተካሄደው ኮንፍረንስም የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ገቢ ለማሳደግ ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል አንዱ ነው ብለዋል።
ከቡና ምርት ባለፈ የእንስሳት ተዋጽኦን፣ የዓሳ ምርቶችንና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን በስፋት ቻይናን ጨምሮ ወደ ሌሎችም ሀገራት ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህም በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ጠቁመው፤ ለኢትዮጵያ ላኪዎች አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለቡና ምርታማነትና ጥራት የሰጠችው ትኩረት በዘርፉ የወጪ ንግድ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ቡና በበርካታ ሀገራት ተመራጭነቱ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው፤ በተለይም ቻይና ዋነኛ የቡና መዳረሻ እየሆነች ነው ብለዋል።
ለአብነትም ቻይና ከአምስት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ቡና የወጪ ንግድ መዳረሻ ከሆኑ ሀገራት መካከል ከነበረችበት 33ኛ ደረጃ ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ማለቷንም ተናግረዋል፡፡
ይህ ውጤት የተመዘገበው በአንድ በኩል የቻይናውያን የቡና ፍላጎት መጨመር በሌላ በኩል የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ ሀገራት በሰጠው የነፃ ታሪፍ ዕድል የተነሳ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና በቻይናውያን ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈ መምጣቱንም ጨምረው ጠቅሰዋል።
የሁለቱ ሀገራት የቡና ንግድ ትስስር እያደገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በቅርቡ በጁጆ ከተማ በተካሄደው ኮንፍረንስ በርካታ ገዥ ኩባንያዎች መሳተፋቸውንና አዳዲስ የገበያ ትስስር ስምምነቶች መፈረማቸውን ገልጸዋል፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፤ በቻይና የተካሄደው ኮንፍረንስ የኢትዮጵያን ቡና በስፋት ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።
ቻይና ያላት ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እና በየጊዜው እያደገ የመጣው የቡና ፍላጎት ለኢትዮጵያ ቡና ወደፊትም ሰፊና አስተማማኝ የገበያ መዳረሻ እንድትሆን ያደርጋታል ነው ያሉት።
በመድረኩ ከቡና አፈላል ጀምሮ ያለውን ኢትዮጵያዊ ሥርዓት ለቻይናውያን ማስተዋወቅ መቻሉን ጠቅሰው፤ ቡና በሀገር ገጽታ ግንባታ በኩል ያለውን ትልቅ አቅም ለመጠቀም እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቡና ንግድ ትብብር ይበልጥ ለማስፋት አዲስ ምዕራፍ መከፈቱንም አቶ ተስፋሁን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እሴት የተጨመረበት ቡና ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ገቢዋን ለማሳደግ እየሠራች ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 1/2018: ኢትዮጵያ ቡናን በጥሬው ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ ለዓለም ገበያ በማቅረብ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገለጸ።
ኢትዮጵያ የቡና መገኛና ከአፍሪካ ቀዳሚዋ አምራች ሀገር ስትሆን ቡናን እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ በመላክ የተጀመረው ጥረት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው፡፡
ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ 470 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት የ15 ዓመት የቡና ስትራቴጂ ፍኖተ ካርታ ተቀርጾ ወደ ሥራ ተገብቷል።
በዚህም በዘርፉ የነበሩ መዋቅራዊ ችግሮችን በመለየት በምርትና ምርታማነት እንዲሁም በገበያ አድማስ ማስፋት ላይ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡
ምርታማነታቸው ዝቅተኛ የነበሩ ያረጁ የቡና ተክሎችን በመጎንደል የማሳ ላይ ምርታማነትን የማሳደግ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
በሀገር አቀፉ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ታግዞ አዳዲስ የቡና ተክሎች በስፋት መተከላቸውን ጠቁመዋል።
በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን የምርት መጠን ብቻ ሳይሆን ጥራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ቡናው በከፍተኛ ጥራት እንዲመረት ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ምርታማነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን የግብይት ሰንሰለቱን ማሳጠር ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም ለውጥ እየመጣ ይገኛል ብለዋል፡፡
ቀደም ሲል የነበረውን የተንዛዛ የገበያ ሥርዓት በፖሊሲ ማሳጠር በመቻሉ ይባክን የነበረውን የምርት መጠን መቀነስና በጥራት ላይ ይፈጠሩ የነበሩ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ማስቀረት መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ ካላት የቡና አቅም አንጻር የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ እሴት ጨምሮ ለገበያ የማቅረብ ሥራ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ቀደም ሲል እሴት የተጨመረበት ቡና በምን ዓይነት የጥራት ደረጃና ሁኔታ ወደ ውጭ መላክ እንዳለበት የሚወስኑ ግልጽ መመሪያዎች ባለመኖራቸው ዘርፉ ሳይነቃቃ መቆየቱን አስረድተዋል።
ይህንን ክፍተት በመሙላት ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥር አዲስ መመሪያ ጸድቆ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመው አዲሱ መመሪያ በሀገር ውስጥ የተቆላና የተፈጨ ቡናን በውጭ ምንዛሬ የመሸጥ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በርካታ የቡና ቆይ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትላልቅ ሆቴሎችና በቱሪስት መዳረሻዎች በውጭ ምንዛሬ መሸጥ መጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡
በቡና ገበያው ተወዳዳሪ ለመሆን ...

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቆየት በምርት ጥራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው አሉ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር፡፡

በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የቻይና-ኢትዮጵያ የቡና ኢኮኖሚ እና ንግድ ትብብር ኮንፈረንስ በቻይና ሁናን ግዛት ጁጆ ከተማ በታሕሣሥ ወር ውስጥ መካሄዱ ይታወሳል።

በቻይና ውስጥ የኢትዮጵያ የቡና ምርት ተፈላጊነት እየጨመረ መምጣት የሁለቱን ሀገራት ትስስር በማጠናከር ረገድ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።

የቻይና ገበያ ለኢትዮጵያ ቡና ያለው ፍላጎት እያደገ መምጣቱ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዕድል በመሆኑ የምርት ጥራትና ብዛትን ማስጠበቅ እንደሚገባ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ቡናን ቻይናን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ፣ ገበያ ለመፈለግና ወጪ ንግዱን ለማሳደግ ታልሞ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ሻፊ ኡመር፤ ለዚህም ሁለት ስትራቴጂዎች ተነድፈው እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የመጀመሪያው ስትራቴጂ ወደ አዳዲስ ገበያ መግባት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በነባሩ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ መቆየት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የቡና ጥራት ላይ ትኩረት ማድረግ የኢትዮጵያ ቡና ተፈላጊ እንዲሆን ያስችለዋል በማለት ገልጸው፤ ይህም አዳዲስ ገበያዎች ውስጥ ለመግባት እና ነባር ገበያ ውስጥ ደግሞ ጠንካራ እና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቆየት ያግዛል ብለዋል፡፡

እስካሁን የቡና ጥራትን ለማስጠበቅ በተከናወኑ ተግባራት የቡና ምርት መዳረሻ ሀገራትን ማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

በ2016 ዓ.ም ኢትዮጵያ 64 ለሚሆኑ ሀገራት የቡና ምርቷን ትልክ እንደነበር ጠቅሰው፤ አሁን ላይ የቡና ምርታችን መዳረሻ ሀገራትን ቁጥር ወደ 84 ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በሁለት ዓመታት ውስጥ የተፈጠሩት 20 አዳዲስ የቡና ገበያ መዳረሻዎች ከተለመደው አካሂድ በመውጣት ቡናን በአዲስ መልክ ለመላክ የተደረገው ጥረት ውጤት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
በሲዳማ ክልል ከአንድ ሄክታር በአማካይ ከ10 ኩንታል በላይ የቡና ምርት እየተሰበሰበ ነው
++++++++++++++++++++

በሲዳማ ክልል በ2018 የምርት ዘመን ከአንድ ሄክታር መሬት በአማካይ ከ10 ኩንታል በላይ የቡና ምርት እየተሰበሰበ መሆኑን የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬ እና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መስፍን ቃሬ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በክልሉ በምርት ዘመኑ ለመሰብሰብ ከታቀደው 239 ሺህ ቶን የቡና ምርት ውስጥ እስካሁን 80 ሺህ ቶኑ ተሰብስቧል።

በክልሉ 176 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና የተሸፈነ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 146 ሺህ ሄክታር የሚሆነው ምርት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

በደጋ እና ወይናደጋ አካባቢዎች የምርት አሰባሰብ ሂደቱ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መስፍን፤ አማካይ ምርታማነቱም በአንድ ሄክታር ከ10 ኩንታል በላይ መድረሱን ገልጸዋል።

የቡና ጥራትንና ምርታማነትን ለማሳደግ አርሶ አደሮችን በክላስተር የማደራጀት ሥራ እየተሠራ ሲሆን፤ በዘንድሮው ዓመትም በ239 ክላስተሮች የማደራጀት ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

ያረጁ የቡና ዛፎችን በመጎንደል፣ አዳዲስ ዝርያዎችን በመተካትና የተፈጥሮ ማዳበሪያን በመጠቀም ምርታማነትን የመጨመር ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ሁለት ሄክታርና ከዚያ በላይ የቡና ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች ምርታቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ እንዲልኩ በተፈቀደው መሠረት፤ በዘንድሮው ዓመት 495 አርሶ አደሮች አዲስ የኤክስፖርት ፈቃድ መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።


+++++++++++++++++
@ጋዜጣ_ፕላስ
የስልጤ ሮዝመሪ ተፈላጊነቱ ጨምሯል!
.......
የታይላንድ ቡናና ሻይ ማህበር ፕሬዚዳንት እና የኤስያ ቡና ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ትርዋት ዎግቮራታት በስልጤ ዞን የሮዝመሪ ምርትን ጎብኝተዋል፡፡

ጉብኝቱ የሮዝመሪ ምርት የገበያ ትስስር ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈላጋነቱ እየጨመረ የመጣው የሮዝምሪ ምርት ወደ ውጭ ሀገራት እየተላከ ፥ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እያስገኘ ነው።

#agriculturepostethiopia #agriculture Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና Silte Zone Government Communication Affairs Department
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እሴት የተጨመረበት ቡና …
ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ በዛሬው ዕለት ከStarbucks ኩባንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሮቤርቶ ቬጋ አሎንሶ ጋር የቡና ልማት እና ግብይትን በተመለከተ በኢትዮጵያ እና በStarbucks ኩባንያ መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸው ወቅት አስተማማኝ የስፔሻሊቲ ቡና አቅርቦት በማረጋገጥ የኢትዮጵያ ቡና በStarbucks የቡና Recipe ውስጥ መጠኑን ትርጉም ባለው ደረጃ ማሳደግ የሚያስችል መግባባት እንደተፈጠረ እንዲሁም የአነስተኛ አርሶ አደሮች ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ ኩባንያው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጡን ክቡር ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።
Starbucks በዓለም ትልቁ የስፔሻለቲ ቡናገዢ ኩባንያ ነው።
በ741ሺህ 165 ሔክታር ላይ የነበረ የቅመማቅመም ሰብል ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፤ ጥር 5/2018፡- በ741 ሺህ 165 ሔክታር ላይ የነበረ የቅመማቅመም ሰብል ተሰብስቦ 1 ሚሊየን 385 ሺህ 150 ቶን ምርት መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገለጸ።
በበጀት ዓመቱ በቅመማቅመም ሰብል የተሸፈነው 775ሺህ 439 ሔክታር መሆኑን በባለሥልጣኑ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፍቃዱ ደፈረስ ገልጸዋል።
ከዚህ ውስጥ እስካሁን ምርት የሚሰጠው በ741 ሺህ 165 ሔክታር ላይ የነበረው የቅመማቅመም ሰብል መሆኑን ገልጸው፤ ምርት ስብሰባውም እንደተጠናቀቀ አመላክተዋል።
የቅመማቅመሙ ዐይነትም፤ በርበሬ፣ ዝንጅብል፣ ኮረሪማ፣ እርድ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ነጭ አዝሙድ፣ አብሽ፣ ድንብላል፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ሚጥሚጣ፣ ሮዝመሪ፣ጥምዝ እና ሌሎች መሆናቸውን አብራርተዋል።
አሁን ላይ የቅመማቅመም ሰብል የምርታማነት ሁኔታ በሔክታር 18 ነጥብ 4 ኩንታል መሆኑንም ለኢዜአ አስረድተዋል።
የቅመማቅመም ዘር ከአርሶ አደር ለአርሶ አደር አቅርቦትን በተመለከተ 1 ሺህ 513 ነጥብ 75 ኩንታል በርበሬ፣ 32 ኩንታል ሚጥሚጣ፣ 2 ሺህ 444 ነጥብ 4 ኩንታል ጥቁር አዝሙድ፣ 406 ኩንታል ነጭ አዝሙድ፣ 1ሺህ 300 ኩንታል አብሽ፣ 868 ሺህ 153 ኩንታል ዝንጅብል፣ 90 ሺህ 597 ኩንታል እርድ ለተጠቃሚዎች መቅረቡን ገልጸዋል።
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግም የኤክስቴንሽን አገልግሎትን፣ የኩታ ገጠም ልማትን፣ የሙሉ ፓኬጅ አተገባበርን ማጠናከርና አዳዲስ ቴክኖሎጂን መጠቀም ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል።