Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.74K subscribers
5.5K photos
30 videos
66 files
358 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በታችኛው አርሾ ቀበሌ በለበቆ የመንግስት ችግኝ ጣቢያ ውስጥ ለያዝነው ዓመት ተከላ እንዲውል እየተዘጋጀ የሚገኝ የቡና ችግኝ አሁናዊ ገጽታ!

ታህሳስ 26/04/18 ዓ.ም
የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ መረጃ በትክክል መሰብሰብና መያዝ ወሳኝ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ገለፀ

‎ሆሳዕና 24/04/2018

‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ባላስልጣን ጋር በመተባበር በኢዩ-ካፌ በጀት ድጋፍ በEUDR ህጎችና የአርሶአደሮች ቡና ማሳ መረጃ አሰባሰብ ዙሪያ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሶምሶን ወ/ግዮርግስ በበኩላቸው ስልጠናው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ባላስልጣን ጋር በመተባበር በኢዩ-ካፌ በጀት ድጋፍ በEUDR ህጎችና የአርሶአደሮች ቡና ማሳ መረጃ አሰባሰብ ዙሪያ እየተሰጠ ነው ብለዋል ።

‎ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆነ እና የምርቱ መነሻና ወቅቱ የተረጋገጠ እንድሁም የተሻለ ግብይት እንድካሄድ የሚያስችል ስልጠና እንደሆነም ተናግረዋል ።

‌‎የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ መረጃ በትክክል መሰብሰብና መያዝ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል ።

‌‎የሁሉም አርሶአደሮች ከተከለ እስከ ምርት አሰባሰብ ድረስ ያለውን የቡና መረጃ ለመሰባሰብ የጋራ ግንዛቤ እንድኖር ነው ብለዋል ።

‌‎ በቡና ልማት በቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ በመያዝ የግብይት ሂደቱን በማሳለጥ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ የስልጣናው ፋይዳ የጎላ እንደሆነም አንስተዋል ።

የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ሀብታሙ ታደሰ በስልጠና ወቅት እንደገለፁት ስልጠናው በቡና ምርት ግብይት ፣በመረጃ አሰባሰብና በጥራትና በአመራረት ዘይቤ ትኩረት ያደርጋል ።

‎የቡና ምርት አያያዝን በቴክኖሎጂ ከማስደገፍ አንጻር የሚስተዋሉ ውስንናቶችን ለማስቀረት በሚል በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ዶክተር ሀብታሙ ተናግረዋል ።

‎በየአከባቢው የሚገኙ የቡና አምራቾችና የማሳ ሽፋን ተለይቶ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ልዩ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም አንስተዋል ።

ሰልጣኞች እየተሰጠ ያለውን ትምህርትና ስልጠና በአግባቡ በመከታተል በየአካባቢያቸው የአርሶአደሮችን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የድርሻቸውን እንድወጡም አስገንዝበዋል ።

‎የሀድያ ዞን ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም ስርጎታ እንደተናገሩት በዞኑ ከዚህ ቀደም የቡና ሽፋን 20 ሺህ ሄክተር ከነበረበት በተያየዘው በጀት ዓመት ወደ 42 ሺህ ሄክተር ማሳደግ ተችሏል ።

‎የጉራጌ ዞን ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት የኃላፊ ተወካይ አቶ ታሪኩ ወርቁ በዞኑ የቡና ሽፋን 55 ሺህ ሄክተር እንደሆነ ገልጸው ይህ ስልጣና ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል አምራቹ በቀጥታ ከገዥ ጋር እንድገነኝ እድል ይፈጥራልም ብለዋል ።

‎ከዚህ ቀደም የቡና ምርትን በተለምዶ በማምረት በአከባቢው ገበያ በማቅረብ የተጠቀሚነት ጉድለት እንደነበር ያነሱት ሀላፊዎቹ ከሽፋን ባለፈ ጥሩ ምርት የሚሰጥና በሽታን መቋቋም የሚችል የቡና ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ።

‎የአርሶአደሮችን ተጠቀምነት ለማረጋገጥ በገበያ ትስስር ዙርያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል ።

ምንጭ ሀድያ ቴሌቪዥን


Prime Minister Abiy Ahmed Ali "The tea development initiative, which is part of the Green Legacy program, is being implemented successfully. The promising start observed in planting, if followed through with full agro-processing and supported by private sector participation to add value, will benefit our country through exports in addition to meeting domestic consumption needs. "
የልዩ ጣዕም ቡናን በብዛትና በጥራት በማምረት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል
ዲላ ፤ታህሳስ 25/2018
በበጀት ዓመቱ የልዩ ጣዕም ቡናን በብዛትና በጥራት አምርቶ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የዘርፉን ገቢና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትኩረት መደረጉን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የልዩ ጣዕም ቡና ዝግጅት የመስክ ምልከታና በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የተለያዩ ጣዕም ቡና ማቀነባበሪያ ማሽን ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይም የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት በተያዘው ዓመት ቡናን በብዛትና በጥራት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ርብርብ እየተደረገ ነው።
በተለይ በቂ ምርት ከማዘጋጀት ባለፈ ጥራትና እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ ጣዕሞች ቡናን የሚያቀነባበር ማሽን ወደ ስራ መግባቱን ለአብነት አንስተዋል።
ይህም የኢትዮጵያን ቡና ተፈላጊነት ለመጨመር የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
በተያዘው ዓመት ከ600 ሺህ ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በጥራት የመሰብስብና የማዘጋጀት እንዲሁም ከስር ከስር የመላክ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በተለይ የውጭ ደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የልዩ ጣዕም ቡና ከ70 በመቶ በላይ በማቅረብ ከ800 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘትና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በክልሉ ከ131 ሺህ ቶን በላይ ቡና በመሰብሰብ ከ46 ሺህ ቶን የሚልቀውን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አማኑኤል ብሩ ናቸው።
በተለይ ከታጠበና ካልታጠበ ቡና በተጨማሪ የቡና ገዢ ደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቡና በተለያዩ ጣዕሞች በስፋት እየተዘጋጀ መሆኑን አንስተው ምልከታውም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመዋል።
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ብቻ ልዩ ጣዕምን ጨምሮ በ15 የተለያዩ ጣዕሞች ከ50 ሺህ ኩንታል በላይ ቡና ለውጭ ገበያ መቅረቡን አንስተው ይህም የዞኑን ቡና ጥራትና ተፈላጊነት በእጅጉ ማሳደጉን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅትም በማህበራትና በአርሶ አደሮች የቡና ግዢ ደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የልዩ ጣዕም ቡና በስፋት እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።
ከአካባቢው ማህበራት ጋር በመቀናጀት በውድድር የሚሸጥ ልዩ ጣዕም ቡና እያዘጋጁ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የቡና ላኪ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የሆኑት መሰረት ወርቅነህ ናቸው።
በዚህም በተያዘው ዓመት 5 ሺህ ቶን ልዩ ጣዕም ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብም ቡናን በተለያዩ ጣዕሞች የሚያዘጋጅ ማሽን ወደ ስራ ማስገባታቸውን ገልጸዋል።
መረጃውን ያገኘነው ከኢዜአ ነው
ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ጎበኙ!!
ታህሳስ 28/2018
አዲስ አበባ
የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት አጠቃላይ ያለውን የስራ እንቅሰቃሴ ጎብኝተዋል፡፡ ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ሚኒስትሩን ተቀብለው በዘመናዊ ሁኔታ የታደሰውን የህንጻውን አጠቃላይ ገጽታ እና በውስጡ የሚገኙትን ቢሮዎች ተዘዋውረው አስጎብኝተዋቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዘመናዊ ሁኔታ በኦንላይን እየተሰጠ የሚገኘው የሽኝት እና ኬላ ቁጥጥር አሰራር በተመለከተ በቂ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉም የጉብኝቱ አካል ነበር፡፡