🍒☕️ The coffee picking season is almost coming to an end and our focus now shifts to nurturing the next crop......preparing the fields, caring for the trees and laying the foundation for another exceptional harvest.
In coffee, every ending is also a beginning and the quality of tomorrow’s cup is shaped by the work we do today.
#☕️

አለማቀፍ መስፈርቶችን አሟልቶ መገኘት እስከተቻለ ድረስ ጥሩ የሚባል/Premium ዋጋ ማግኘት እንደሚቻል ተገለጸ!!
ታህሳስ 25/2018
ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በሀንስ ኒውማን ፋውንዴሽን ከሚደገፈው EU YAYU DESIRA ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ ነው፡፡ የወርክሾፑ ዓላማ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የመጡ ምሁራን ኢትዮጵያ ቡናዎቿን ዓለማቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አውሮፓውያን በሚጠይቁት መስፈርት መሰረት GI ሰርቲፋይ መሆን ስለሚችሉበት መንገድ ገለጻ ለማድረግ እና አእምሯዊ ንብረቶች/ IP Based Strategy በመከተል ላመረትነው ምርት ጥሩ የሚባል/Premium ዋጋ ማግኘት ስለሚቻልበት ሁኔታ ከባለሙያዎች ጋር ለመምከር ነው፡፡
ምሁራኑ አጠቃላይ የንግድ ምልክት/Trade Mark ከ GI ጋር ያላቸውን አጠቃላይ አንድነት እና ልዩነት እንዲሁም ዘመኑን የተከተለውን GI በመጠቀም አገሪቱም ሆነ ቡና አብቃይ ማህበረሰብ የልፋቱ ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ያለውን ጠቀሜታ አስረድተዋል፡፡ EU YAYU DESIRA ፕሮጀክት ተግባራዊ በሚደረግባቸው ወረዳዎችም ከዚሁ ጋር በተያያዘ እስካሁን በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ኢኮኖሚያዊ እና ህጋዊ አንድምታውን ጠቋሚ አንድ ጠቃሚ ጥናታዊ ሰነድ እንደሚያቀርቡ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ሰነድ እንደአገር ወጥ የሆነ አካሄድ እንዲኖር ለማድረግ የሚረዳ ከመሆኑም ሌላ የሻይና ቅ/ቅመም ሰብሎችንም በዚሁ ቅኝት እንዲጓዙ የሚስችል እንደሆነም ተብራርቷል፡፡
ክቡር ዋና ዳይሬክተሩን ወክለው የተገኙት በባለስልጣን መ/ቤቱ የዋና ዳ/ር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ ሴክተሩ እንደአየር ንብረት ለውጥ፣ አለማቀፉ ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታ እና ሌሎች መሰል ችግሮች የሚፈትኑት ከመሆኑ አንጻር በእውቀት የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ ባለስልጣን መ/ቤቱ ከተለያዩ ምርምር ተቋማት እና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በያዩ በሚገኙ የጫካ ቡናዎች ዙሪያ የሚሰራው ይህ ሰነድ በብዙ መልኩ ጠቃሚ በመሆኑ ከመቱ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀንስኒውማን፣ ECF, PHE እንዲሁም ከባለስልጣን መ/ቤቱ የተገኙ አመራር እና ባለሙያዎች ሙያዊ ግብዓታቸውን ያለማሰለስ መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ ውይይቱ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ውሏል፡፡