Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.75K subscribers
5.52K photos
30 videos
66 files
358 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
የአካል ጉዳተኞች የቡና ልማት ስራ ተጎበኘ
የቡና እሴት ጭመራ ቴክኖሎጂ ርክክብም ተካሄደ
የካፌ ፓይለት ፕሮክት መዝጊያ ስነስርዓትም ተፈጽሟል
ታኅሳስ /2018 ዓ.ም
ጅማ ዞን፣ ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ
Life for the World የተሰኘ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ያስጀመረውን Cafe Project የተሰኘ ፓይለት ፕሮጀክት አፈጻጸም የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ፤ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሠፊሳ አባቡ፤ የChesheir Foundation Action for Inclussion ዳይሬክተር ክቡር አቶ ከድር መሐመድ፤ የ Light for the World ዳይሬክተር አቶ ስዋዲቅ ሐሰን፣ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ መሐመድ ቡሪ፣ የሰቃ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ሙክታር አባ ዝናብ በተገኙበት ተጎብኝቷል።
ፖይለት ፕሮጀክቱ በጅማ ዞን ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳና ጅማ ከተማ ያሉ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት በቡናው ልማትና ግብይት እንዲሰማሩ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም በሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አስተዳደር ድጋፍ የወረዳው አካ ጉዳተኞች ማኅበሩ 3 ካሬ የቡና እርሻ ቦታ እና 5000 የቡና ችግኞች ተበርከተውለት የቡና ልማት ስራውን በመስራት ላይ ይገኛል። ማኅበሩ ያመረተውን ቡና እሴት ጨምሮ ለመሸጥ እንዲያስችለው የቡና መቁያ፣ መፍጫና ማሸጊያ ቴክኖሎጂዎች በLight for the World ፈንድ ጠያቂነት፣ በGIZ የገንዘብ ድጋፍ አድራጊነት፣ በChiesheir ግዥ ፈጻሚነት ተበርክቶላቸዋል። ማሽኖቹ እሚያርፉበት 200 ካሬ ቦታ የተሰጣቸው ሲሆን ለማሽኖቹ ከለላ 35 ካሬ ሼድ ተገንብቷል። መቁያ ማሽኑ በሀገር ውስጥ የተሰራ መሆኑና ይህም አገር ውስጥ ሊጠገን የሚችል መሆኑ፣ በ25 ደቂቃ 25 ኪሎ በሰዓት 50 ኪሎ የሚቆላ፣ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት ያለው በመሆኑም የአካባቢ ብክለትን የሚከላከል መሆኑ፣ ዋጋው ተመጣጣኝ እንደሆነና በ1.3 ሚሊዮን ብር ወጭ እንደተገዛ ተነግሯል፡፡ የመፍጫ ማሽኑ ደግሞ አገር ውስጥ የተሰራና በሰዓት 41 ኪ.ግ ቡና የሚፈጭ አንደሆነ፣ የድቀት መጠንን ለማመጣጠን የሚያስችል ስክሪን ያለው፣ ብናኝ መሰበሰቢያ የተገጠመለት እንደሆነና በኤሌክትሪክ የሚሰራ መሆኑ የአየር ንብረት ብክለትን በማያስከትል መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል መሆኑን ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል፡፡
ስለማሽኖቹ አጠቃቀም ክህሎት ላይ ከአዲስ አበባ ጅማ ባለሞያ በማስመጣት መሠረታዊ ስልጠና ለተመለመሉ የማኅበሩ አባላት ተሰጥቷቸዋል።
የሰቃ ጨቆርሳ የአካል ዳተኞች ቡና እርሻና እሴት የተጨመረበት የቡና ምርት አንደሚሰማራ፤ በጅማ ከተማ ያለው ማኅበር ደግሞ በንግድ ስራ እንደሚሰማራ ተገልጸዋል፡፡ ለዚህም እውናዊነት የሰቃ ጨቆርሳው ማኅበር ራሱም በመንግድ ስራ መሰማራቱ እነዳለ ሆኖ ለጅማው ማኅበር ያመረተውን ቡና በሽያጭ እንደሚያስረክብና ጅማ ያለው ማህበርም በቡና ንግድ ስራእንደሚሰማራ በዚህ መልክም ሁለቱ ማኅበራት ቅንጅትን እንደሚፈጥሩ ተወስቷል፡፡
ከጉብኝቱና ርክክቡ በኋላ በነበረው መርሀግብር የየተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ንግግር አሰምተዋል። የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ የተለገሱትን የቡና ማሽኖችን ለመጠቀም የሚያስችል የጠለቀ ዕውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ሠፋ ያለ ስልጠና ባለስልጣን መስሪያቤቱ እንደሚያመቻች ተናግረዋል። የተደረጉትና ቀጣይ የሚደረጉ ድጋፎችን በመጠቀም ማኅበሩ ቡናን ለውጭ ገበያ እስከማቅረብ ድረስ ራዕይ የሰነቀ የስራ እንቅስቃሴ እንዲኖረው አሳስበዋል። ለማኅበሩ ድጋፍ ያደረጉትን የወረዳው መስተዳድር አካላትን ጨምሮ የግል ድርጅቶችን አመስግነዋል።
እንደምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ሁሉ ፓይለት ፕሮጀክቱን የቀረጸው የLight for the World ዳይሬክተር ክቡር አቶ ስዋዲቅ ሐሰን ንግግር አድርገዋል፡፡ በመንደርደሪያቸው የተቋማቸው ሙሉ ተልዕኮ፣ ተግባርና ኃላፊነት ከገለጹ በኋላ ባለስልጣን መስሪያቤቱን፣ ሺሼይርንና የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አስተዳደር አካላትን አመስግነው ጂ አይ ዜድ የገንዘብ ድጋፍ እንዳደረገ ጠቅሰው በአካል ተገኝተው እንደተመለከቱት ፕሮጀክቱ ውጤታማ መሆኑን እንዳጤኑ ተናግረዋል፡፡ ስራው ምሳሊያዊ የሆነ ጅማሮ እንደሆነ ያወሱት ዳይሬክተሩ ከዚህም ባሻገር ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር የተሰሩ በርካታ ስራዎችን ዘርዝረዋል፡፡ ስራዎቹን ሲገልጹም በባለስልጣኑ የስልጠና ማዕከል አካል ጉዳተኞች ስልጠናዎች እንዲወስዱ መደረግ፣ የድረገጽ አጠቃቀም አካል ጉዳተኞችን ያማከለ እንዲሆን ማድረግ፣ የአካል ጉዳተኞች ያማከለ ስትራቴጂ መቅረጽ ስራዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡
የሺሼይር ዳይሬክተርም በበኩላቸው ፕሮጀክቱ የስድስት ወራት ፕሮጀክት እንደሆነ ሆኖም ግን የታቀዱት ስራዎች በዚህ ጊዜያት ያልቃሉ ተብለው የሚታሰቡ እንዳለነበረና በባለስልጣኑ፣ በLight for the World፣ በወረዳው መስተዳድር አካላትና የማኅበሩ አባላት ርብርብ ከዳር መድረሱን አድንቀው እነዚህን አካላትን አመስግነዋል፡፡ ስራውም ‹‹ቅን ልቦች የተሰባሰቡበት እንደነበር ያሳይል›› ብለዋል፡፡ ስራው አሁንም ቀጣይነት እንዲኖረው የቅንጅት ስራው መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ይህም እውን ሆኖ ስራው ሌላ ፕሮጀከት መውለድ አለበት ብለዋል፡፡ በወረዳው ያሉ አካል ጉዳተኞች በቡናው ዘርፍ እንዲሳተፉ እየተደረገ እንዳለው ሁሉ በሌሎችም የልማት ስራዎች ውስጥ ማሳተፍ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከርክክቡና የልማት ቅኝቱ ቀደም ባሉት ቀናት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሠፊሳ አባቡ በወረዳው ተገኝተው የቡና ልማት ስራውንና የቡና ማሽኖቹን ተመልክተዋል፡፡ በቅኝታቸውም ወቅት የተሠራውን ስራ አድንቀው መደረግ ስላለባቸቀው ነገሮች ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ ከቡና ልማቱ አንጻር የአረም ማረሙ ስራ ሊታሰብበት እንደሚገባና የአካል ጉዳተኞች ማኅበር አባላት በርብርብ መስራ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ የተሰጠው የእርሻ መሬት፣ የተገኙት ችግኞች፣ የተበረከቱት የቡና ማሽኖች በቀላሉ የማይገኙ እንደሆኑና ሀብቶቹ እንዳይባክኑ በዋናነት የማኅበሩ አባላት ከፍትኛ ኃላፊበነት ሊሰማቸውና ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
በመርሀ ግብሩም ወቅት ለስድስት ወራት የቆየውና የልማት ስራውን ያሳካው የLight for the world ፓይለት ፕሮጀክት የመዝጊያ ስነስርዓትም ተፈጽሟል።
ዘገባ አሸናፊ ጌታሁን
ከሲዳማ ክልል ከ6 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ
ሐዋሳ ታኅሣስ 24/2018
በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት ከ6 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የሲዳማ ክልል ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ቃሬ ተናገሩ።
ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበውን የቡና መጠን ለማሳደግም ቡናን በክላስተር የማልማት፣ ያረጁ ቡናዎችን የመጎንደልና በአዲስ የመተካት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሥነ-ምኅዳርን መሠረት ያደረጉ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለማስፋት ከምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
የቡና ጥራትና ምርታማነትን ለማሳደግም ከቡና አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም ከ232 በላይ ቡና አምራች ኢንዱስትሪዎች ቨርሚ ኮምፖስት አዘጋጅተው ለአርሶአደሩ እያሰራጩ ነው ብለዋል።
ዘንድሮ ከተዘጋጀው ከ5 ነጥብ 2 ሚሊየን ቶን በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ቶኑ ጥቅም ላይ መዋሉን እንዲሁም ቀሪው ለመጋቢት ተከላ መቀመጡን አስረድተዋል።
በክልሉ በቡና ልማት ከተሸፈነው 176 ሺህ ሔክታር መሬት 148 ሺህ ሔክታሩ ምርት እየሰጠ መሆኑም ተጠቁሟል።
በክልሉ የበንሳ ወረዳ ቡናና ፍራፍሬ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ታምራት ቱንሲሳ በበኩላቸው፤ በወረዳው ካለው ከፍተኛ የቡና ልማት የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ውጤት እያመጡ ነው ብለዋል፡፡
ምርታማነቱን ለማሳደግም በወረዳው ባሉ ከ19 በላይ ቡናን የሚያዘጋጁ ኢንዱስትሪዎችና አርሶ አደሮች ማሳ ከ365 ሺህ ቶን በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት መቻሉን አንስተዋል።

ምንጭ፡ ኢዜአ
የቡና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ችግኞችን በማፍላት አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 23/2018

የቡና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ችግኞችን በማፍላት አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑን የጅማ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

ቱሪዝም ሚኒስቴር "የቡና ቱሪዝም" የመገናኛ ብዙኅን ሙያተኞች የትውውቅና የግንዛቤ ማስጨበጫ የጉብኝት መርሃ ግብር እያካሄደ አንደሚገኝ ይታወቃል።

በዛሬው ውሎም የቡና ቱሪዝምን ማነቃቃት ዓላማ ያደረገ የመገናኛ ብዙኅን ሙያተኞች የቡና አብቃይ አካባቢዎች የመስክ ምልከታ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ጎማ ወረዳ በሻሻ ቀበሌ ቀጥሏል።

በዚሁ ወቅት የጅማ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አብዲ መሐመድኑር፤ የጅማ ሕዝብ ከቡና ምርታማነት ጋር ጥብቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቁርኝት እንዳለው ገልጸዋል።

በዞኑ በቡና ምርታማነት ላይ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያሻሽሉ ውጤታማ የቡና ልማት ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል ብለዋል።

በዞኑ የቡና ጥራትና ምርታማነትን በማሳደግ ከለቀማ እስከ ውጭ ገበያ የሚቀርብበት ሥርዓት በጥንቃቄ እየተመራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም የአርሶ አደሩን የቡና ምርታማነት ለማሳደግ ምርታማነታቸው የተረጋገጠ የችግኝ ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ባለሙያ የሆኑት መሐመድሰፋ ከድር በበኩላቸው፣ የአርሶ አደሮችን የቡና ምርታማነት በማሳደግ በተለያዩ የደረጃ መለኪያዎች በውጭ ገበያ ጭምር ቀጥታ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ለኢዜአ ገልጸዋል።