Ethiopian Coffee and Tea Authority
5.76K subscribers
5.52K photos
30 videos
66 files
358 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
ከኢኮኖሚው ባለፈ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ምቹ የሆነው የኢትዮጵያ ቡና
*******
የቱሪዝም ሚኒስቴር ያዘጋጀው የቡና ቱሪዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የትውውቅ ጉዞ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።
መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያውያን ከቡና ጋር ያላቸውን ጥልቅ የባህል ቁርኝት በማሳየት፣ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ግንባር ቀደም ተመራጭነት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ቡና በሁሉም የዓለም ክፍሎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው በመሆኑ፣ ከምርት እስከ ግብይት ያለውን ሂደት ለዓለም ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የቡና መገኛ በመሆኗ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ለዓለም ለማስተዋወቅ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ቡናን መሰረት ያደረገው የትውውቅ ጉዞ እንደ ጅማ፣ ከፋ፣ ሲዳማ እና ይርጋጨፌ ያሉ ዋና ዋና የቡና አምራች አካባቢዎችን ያካተተ ሲሆን፤ በጉዞው ላይ የሚሳተፉ ጋዜጠኞችም ከቡና ለቀማ እና ዝግጅት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በመመልከት ስለ ቡና ቱሪዝም ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል።
መርሐ ግብሩ እስከ ታኅሣሥ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን፤ ዛሬ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የቡና ማሳ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።
ቡና የኢትዮጵያውያን መገለጫ ከመሆኑ ባለፈ፣ ማኅበራዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድ ዘመናትን የተሻገረ እሴት በመሆኑ፤ ይህን ትልቅ የሀገር ሀብት ለዓለም ገልጦ ማሳየትና ማስተዋወቅ እንደሚገባም ተገልጿል
የቡና አምራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው - አቶ አዲሱ አረጋ

ኦቢኤን ሣይበር ሚዲያ ታህሳስ 21/ 2018
የቡና አምራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት የሚያረጋገጡ የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ ነው አሉ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፡፡

በሚኒስትሩ የተመራ ቡድን በሲዳማ ክልል ተገኝቶ የቡና ልማት እንቅስቃሴን ጎብኝቷል።
በዚህ ወቅት አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት፤ በተያዘው በጀት ዓመት 600 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዷል።

በአርሶ አደሩ እና በህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት እየለማ ያለው ቡና ዕቅዱን ለማሳካት እንደሚያስችል ጠቅሰው፤ በሲዳማ ክልል የታየው የቡና ልማት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ቡና አምራች አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የተለያዩ የማሻሻያ ርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ ገልጸው፤ ለአብነትም አርሶ አደሮች በቀጥታ ለውጭ ገበያ ምርት እንዲልኩ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል።

አርሶ አደሮቹ በቡና ስፔሻሊቲ ላይ ግንዛቤያቸው እንዲያድግ መደረጉን እና በቀላሉ ፈቃድ የሚያገኙበት አሰራር መዘርጋቱን አብራርተዋል፡፡
በዓለም ገበያ በጣዕሙ ልዩ የሆነ ቡና የምታቀርበው ኢትዮጵያ በሚገባት ልክ እንድትጠቀም ተጨማሪ ስራዎች ያስፈልጋሉ ነው ያሉት።

የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው÷ በክልሉ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ ክላስተር በማደራጀት አርሶ አደሩ በህብረት እንዲሰራ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ቃሬ÷ ክልሉ በበጀት ዓመቱ 40 ሺህ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ እንደሚያቀርብ ገልፀዋል፡ ኤፍ.ኤም.ሲ
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የተያዙ ትልሞች የቡናውን ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ የሚያደርጉ ናቸው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018፦ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የተያዙ ትልሞች የቡናውን ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ የሚያደርጉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ የግብርናውን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ የተሻሻሉ ዝርያዎችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች።

የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ዋነኛ ምንጭ የሆነው ቡናም የዚህ አካል ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቡና ምርትና ምርታማነት ላይ በተከናወኑ ስራዎች ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከለውጡ ዓመታት በፊት ከ500ሺህ ቶን ጥቂት ከፍ ያለ ቡና እንደሚመረትና ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ ብቻ ለውጭ ገበያ ይቀርብ እንደነበር አስታውሰዋል።

የለውጡ መንግስት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብርን ጨምሮ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማገዝ በወሰዳቸው እርምጃዎች በቡና ምርትና ምርታማነት ላይ የሶስት እጥፍ እንዲሁም በውጭ ምንዛሬ ግኝት አራት እጥፍ እድገት መመዝገቡ የዘርፉን ሁለንተናዊ ስኬት ያሳያል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ቴክኖሎጂ የላቀ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፣ በቡና እሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ አሰራሮችንም በቴክኖሎጂ የማገዝ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የተለያዩ ዘርፎችን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት የመጠቀም እቅድ ይዞ መምጣቱን ነው የገለጹት።

በተለይም የአርሶ አደሩን የገበያ መረጃ እጥረት ለመፍታትና አዳዲስ ዝርያዎችን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ አኳያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የተያዙ ትልሞች ዘርፉን የበለጠ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማህበር ፕሬዝዳንት ሁሴን አምቦ(ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ቡናን በጥራትና በብዛት ለማምረት ከባህላዊ አሰራር መውጣትና ዘርፉን ማዘመን ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል።

የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የእያንዳንዱ ቡና አምራች አርሶ አደር ማንነት እንዲለይ በማድረግ የቡና ምርትንና ንግድን ህጋዊና ዘመናዊ ለማድረግ ያግዛል ነው ያሉት።

ለዚህ ማህበሩ በቡና ዘርፍ እሴት ሰንሰለት ውስጥ ለሚገኙ አካላት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ጠቁመው የተወሰኑ ቡና አምራቾቸ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በጀመሩት ጥረት የሚታይ ውጤት መገኘቱን አመልክተዋል።

በዲጂታል 2030 ስትራቴጂ በመታገዝ ተሞክሮውን የበለጠ ማስፋት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።

በአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ቁጥጥር ደንብ መሰረት እያንዳንዱ የቡና ምርት ያለበትን ቦታ በሳተላይት ማሳየት የሚያስችል ሥርዓት እንዲዘረጋ ይጠይቃል ነው ያሉት።

ከዚህ አኳያ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አርሶ አደሩ የተለያዩ ሀገራት የሚያወጧቸውን ህጎች ተረድቶ በዚያ መሰረት እንዲያመርት ዕድል የሚሰጥ መሆኑንም ነው የተናገሩት።