Ethiopian Coffee and Tea Authority
6.03K subscribers
5.9K photos
30 videos
67 files
372 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ስር የሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
(ጥር 25/2016 ዓ ም፡ ኢ/ቡ/ሻ/ባ)፡
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ስር የሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት ስልጠና በቢሾፍቱ ፒራሚድ ሆቴል በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
መድረኩን በይፋ የከፈቱት በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ ናቸው፡፡ አቶ ሰፊሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት በባለስልጣን መ/ቤቱ በጀት ብቻ ስራዎችን ማከናወን አስቸጋሪ በመሆኑ በአጋርነት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ መጠቀም የሚያስፈልግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም የዛሬው መድረክ ማተኮር ያለበት የፕሮጀክት ስራዎችን አፈፃፀም መገምገምና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መለየት ዋነኛው ጉዳይ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም የስልጠና እና የግምገማ መድረኩን በአግባቡ ተከታትሎ ለቀጣይ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ግብዓት ሊገኝ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡
በዚህ መድረክ የክልል ኃላፊዎች፣ የምርምር ማዕከላት፣ የባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዴስክና የቡድን መሪ ባለሙያዎች እና ሌሎች አጋር አካላት የተገኙ ሲሆን የEU-CAFE፣ የEU YAHU DESIRA ፕሮጀክት፣ የFSRP ፕሮጀክት፣ የ ፕሮጀክት እና የ Spanish cooperation Desira እንዲሁም GI ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ሪፖርቶች በተከታታይ በአስተባባሪዎቹ አማካኝነት በዝርዝር የቀረበ መሆኑን የባለስልጣን መ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳየች ቡድን በቦታው በመገኘት ዘግቧል፡፡
The 1st African Coffee week was launched at Sheraton Addis.
የአፍሪካ የቡና ሳምንት በታላቅ ድምቀት በይፋ ተከፈተ!!
20ኛው የአፍካ ጉባኤም እየተካሄደ ነው::

አዲስ አበባ፤ ጥር 29/2016
የመጀመሪያው የአፍሪካ ቡና ሳምንት እና 20ኛው የአፍሪካ ባለልዩ ጣዕም የቡናዎች ማህበር ጉባኤና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል::

ጉባኤውና ኤግዚቢሽኑን በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ የአፍሪካ ባለልዩ ጣዕም ቡናዎች ማህበር/AFCA እንዲሁም ኢንተር አፍሪካ ኮፊ ኦርጋናይዜሽን/IACO ናቸው ።

ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ እና ኤግዚቢሽን ላይ ዓለም አቀፍ ቡና ገዥዎች፣ ቆዪዎች፣ ቡና አምራቾች፣ አልሚዎች, ላኪዎች, የዘርፉ ባለሙያዎች, የክልልና ፌዴራል መ/ቤቶች የስራ ሃላፊዎች, የምርምር ተቋማት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከ1000 በላይ እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የግብርና ሚኒስትሩ ክቡር ዶክተር ግርማ አመንቴ በመክፈቻው ላይ እንዳሉት በአፍሪካ የቡና ኢንዱስትሪ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም አንዳንድ ችግሮች መስተዋላቸውን ተናግረዋል።

ከነዚህ መካከል የተለያዩ የቡና በሽታዎች፣ የበቂ ዝናብ እጥረት፣ የዓለም የቡና ገበያ በየጊዜው መለዋወጥ ተጠቃሽ መሆናቸውን አስረድተዋል:: እነዚህን ችግሮች በጋራ ለማለፍ በትብብር መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያም በአፍሪካ በቡናው ኢንዱስትሪ መስክ የሚገጥሙ ችግሮችን በትብብር ለማስወገድ በሚደረገው አህጉራዊ ጥረት የድርሻዋን ለመወጣት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶክተር አዱኛ ደበላ በበኩላቸው ጉባኤና ኤግዚቢሽኑ በዘርፉ ያሉ ተዋንያንን ቅንጅት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አስረድተው: ምርትና ምርታማነት ለመጨመር እንዲሁም በጥራት ለማምረት ከአርሶ አደሩ፣ በዘርፉ ካሉ ተዋንያን ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህን መሰል አህጉራዊ ሁነት በኢትዮጵያ መካሄዱ ኢትዮጵያ በመስኩ ያላትን አቅም ለማስተዋወቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸው በአፍሪካ የቡና ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ተዋንያንን የበለጠ የሚያቀራርብ የልምድ ልውውጥ መድረክ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢንተር አፍሪካ ኮፊ ኦርጋናይዜሽን ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ሶሎሞን ሩቴጋ በበኩላቸው የአፍሪካ ቡና ኢንዱስትሪ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈ መሆኑን አብራርተዋል።

የቡና ምርት ላይ እሴት አለመጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም ቡናን በሚፈለገው ደረጃ ያለማምረት ችግሮች ከፈተናዎች መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በቡናው ኢንዱስትሪ መስክ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት አህጉራዊ ቅንጅቶች ሊጠናከሩ ይገባል ሲሉም አመልክተዋል።
በርካታ የቡና ድርጅቶችም ምርቶቻቸውን አቅርበው በተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ እንግዶች እየተጎበኘ ሲሆን በከሰአት በኇላ በነበረው መድረክም የፓናል ውይይቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ::
የፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ አበረታች እንደሆነ ተገለፀⵑⵑ
ጥር 2016 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ስራ አስፈጻሚ ትኩረቱን በሴቶች ላይ ያደረገው Women, Coffee and Climate ፕሮጀክት አጠቃላይ ሲያከናውናቸው በቆዩ ተግባራት ዙሪያ ክብርት የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ∕ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ∕ር አዱኛ ደበላ፣ የስፓኒሽ ኮኦፐሬሽን ሀላፊ እንዲሁም በስፓኒሽ ኮኦፐሬሽን የአፍሪካና ኢስያ ፕሬዝደንት በተገኙበት ሰፊ ገለጻ ተደርጓል∶∶ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚገኘው የቡና ማሰልጠኛ ማእከልም ተጎብኝቷል∶∶
ፕሮጀክቱ በስፓኒሽ ኮኦፐሬሽን ድጋፍ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያ ደን ልማት፣ የምስራቅ አፍሪካ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እንዲሁም ውመን ኢን ኮፊ በቅንጅት የሚያከናውኑት እንደሆነ አቶ ፍጹም መንገሻ በባለስልጣን መ∕ቤቱ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ስራ አስፈጻሚ ተናግረዋል∶∶
በኢሉባቦር ዞን ቡና አምራች በሆኑ 5 ወረዳዎች ትኩረቱን ያደረገው ይህ ፕሮጀክት ሴቶች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊደርስባቸው የሚችለውን ጉዳት ከመቀነስ አንጻር በግብአት አቅርቦት፣ በስልጠናና አቅም ግንባታ፣ ማህበረሰብ አቀፍ ውይይት፣ የእውቀት ሽግግር፣ እንዲሁም ሴቶችን በማብቃት በኩል የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱ ተብራርቷል∶∶ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች የታዩ ግኝቶችም ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል∶∶
ይህ በስፓኒሽ ኮኦፐሬሽን በአገራችን ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኝ ፕሮጀክት በሌሎች አገራት ከሚከናወኑ መሰል በርካታ ፕሮጀክቶች አንጻር 12ኝነት ደረጃ ማግኘቱ አበረታች እንደሆነም በውይይቱ ተነስቷል∶∶