ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!!
ጥር 18/2016 ዓ.ም
የባለልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር/ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኢትዮጵያ ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ተፈረመው በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር እንዲሁም በአሊያንስ ፎር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ መካከል ነው፡፡
ስምምነቱን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በኩል የፈረሙት ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ሁሴን አምቦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር ቦርድ ፕሬዝደንት እንዲሁም በአሊያንስ ፎር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኩል ደግሞ ሚ/ር አርዊን ናቸው፡፡
ውድድሩ በአገራችን ከ2012-2014 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ጊዜያት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በርካታ የቡና አርሶ አደሮችን በአፍታ ሚሊየነር ያደረገ እንደነበር አይዘነጋም፡፤ በተለያዩ ምክንያቶች ውድድሩ በባለፈው አመት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በዘንድሮ አመት ግን ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገልጸው፤ አርሶ አደሩ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ቡናውን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መሰብሰብ እና ማዘጋጀት እንደሚገባው እና ራሱንም ለዚህ ከፍተኛ ውድድር እንዲያዘጋጅ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡

Forwarded from Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
የቡና ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከ800 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የቡና ኮንፍረንስና ኤግዚቪሽን እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።
የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ከ800 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶ የሚሳተፉበት የመጀመሪያው "የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ" እና 20ኛው የአፍሪካ ኮፊ አሶሴሽን ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ከጥር 28 እስከ የካቲት 2 /2016 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን የ25 ቡና ላኪ አፍሪካ ሀገራትና የቡና ገዢ ሀገራት የግብርና ሚኒስትሮች ተጋብዘዋል።
በኮንፍረንስና ኤግዚብሽኑ ድርጅቶች ምርታቸውን እንደሚያስተዋውቁ፤ ዝርዝር ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው እና በጅማና ሃዋሳ የጉብኝት መርሃግብር እንደሚኖር ተገልጿል።
በተስፋ ፈሩ
ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ል

ጥር 22/2016 ዓ.ም
ክቡር የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ የመንግስት እና የግል ሚዲያዎች በተገኙበት በመጪው ሳምንት አለማቀፍ የቡና ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን መካሄዱን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለፁት፤ ከ800 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የመጀመሪያው "የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ" እና 20ኛው የአፍሪካ ኮፊ አሶሴሽን ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ከጥር 28 እስከ የካቲት 2 /2016 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ላይ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አለማቀፍ ቡና ገዢዎች እንዲሁም መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የተለያዩ አገራት ኤምባሲ ተወካዮች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ የ25 ቡና ላኪ አፍሪካ ሀገራትና የቡና ገዢ ሀገራት የግብርና ሚኒስትሮች መጋበዛቸውን አስረድተዋል።
በኮንፍረንስና ኤግዚብሽኑ ድርጅቶች ምርታቸውን እንደሚያስተዋውቁ፤ ዝርዝር ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው እና በጅማና ሃዋሳ የጉብኝት መርሃ ግብር እንደሚኖር ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገልጸዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ82 ሺህ ቶን በላይ የቡና እሸት ተሰብስቧል
***
(ኢ.ፕ.ድ)
👉67 ሺህ ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዷል
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በዘንድሮው የምርት ዘመን ከ82 ሺህ 400 ቶን በላይ የቡና እሸት መሰብሰቡን የክልሉ ቡና፤ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ገለጸ።
67 ሺህ 348 ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እቅድ መያዙም ተገልጿል።
በክልሉ የቡና፤ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አሥራት መኩሪያ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2016 የምርት ዘመን ከ82 ሺህ 400 ቶን በላይ የቡና እሸት ተሰብስቦ ወደ ቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪዎች ገብቷል።
በምርት ዘመኑ 106 ሺህ ቶን የቡና እሸት ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን እስካሁን ድረስ ባለው የመሰብሰብ ሂደት ከ82 ሺህ 400 ቶን በላይ የቡና እሸት....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=119308
(ፎቶ ፋይል)