አስደሳች ዜና!! የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ለመጀመርያ ግዜ በአፍሪካ ፋይን ኮፊ አሶስዬሽን እና በኢንተር አፍሪካ ኮፊ ኦርጋናይዜሽን የጋራ ጥምረት የሚከበረውን የመጀመርያው "የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ" እና 20ኛው የአፍሪካ ፋይን ኮፊ አሶስዬሽን ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን ከጥር 28 እስከ የካቲት 2/2016 ዓ.ም በመዲናችን አዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ያካሄዳል፡፡
በዝግጅቱ ከ600 በላይ ታዳሚዎች ተሳታፊ ይሆናሉ። በመድረኩም ከፍተኛ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ በቡና ልማትና ግብይት ዘርፍ የታወቁ ተመራማሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ አለማቀፍ ቡና ገዢዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ይታደማሉ፡፡
የኢትዮጵያ ምድር ያበቀለቻቸው የተለያየ ዝርያ ያላቸው ቡናዎችም ቀርበው ታዋቂ ባለሙያዎች እና እንግዶች እንዲቀምሱት፣ እንዲያጣጥሙት ይደረጋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ይህንን አለማቀፍ ሁነት ለማከናወን የቅድመ ዝጅግት ስራውን ማጠናቀቁን ስንገልጽ በታላቅ ኩራት ነው፡፡
«የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ»
ቡናችን ወርቃችን፤ ቡናችን መለያ፣ ክብር እና አንድነታችን!!!

https://dailycoffeenews.com/2024/01/04/ethiopia-launches-20-8-million-coffee-land-use-program-folur/
Daily Coffee News by Roast Magazine
Ethiopia Launches $20.8 Million Coffee Land Use Program (FOLUR)
In partnership with the United Nations Development Programme (UNDP), the Government of Ethiopia has officially embarked on a long-term program to combat deforestation and integrate sustainability in the coffee sector.
በቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉ በዘመናዊ የቡና አቆላል ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ጥር 15/ 2016 ዓ.ም
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቡና ምርትና ግብይት ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት በተለያዩ ጊዜያት ሲያደርገው እንደቆየው ሁሉ በዛሬው ዕለትም ከዩኒዶ ጋር በመተባበር ከዚሁ ተቋም ጋር በጋራ ባቋቋመው የቡና ማስልጠኛ ማዕከል ዕሴት የተጨመረበት ቡና ጥራቱን ጠብቆ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በዩኒዶ በኩል ከጣሊያን የመጡና የካበተ ልምድ ያላቸው አሰልጣኘ ሲሆኑ ስልጠናውን የወሰዱት ደግሞ ከቡና ቆዬዎች ማኅበር ለመጡና ሌሎች አጋር አካላት ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞችም ስልጠናውን እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን 5 ሴቶችና 10 ወንዶች በድምሩ 15 ሰልጣኞች ስልጠናውን ወስደዋል፡፡ ይህ ለሶስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ዕሴት የተጨመረበት ቡና አዘጋገጃጀት ላይ ያለው የዕውቀትና የክህሎት ክፍተት ይዘጋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ ስልጠናው በንድፈሃሳብና በተግባር የተሰጠ ሲሆን በዋናነት በኤሌክትሪክና በጋዝ ማሽኖች እንዴት ጥራቱን ጠብቆ መቁላት ላይ ያለተኮረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከስልጠና ማዕከሉ እንደተገለጸው ስልጠናው በሶስት ዙር የተሰጠ ስልጠና አንዱ አካል ሆኖ ይህ ሶስተኛው ዙር ስልጠና እንደሆነና መሰል ስልጠና ለዚህ ቀደም በሁለት ዙር እንደተሰጠ አስተውሰዋል፡፡ ሁለቱን ስልጠናዎች አስመልክቶ የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ክፍል በዜና ማስነበቡ ይታወሳል፡፡

ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!!
ጥር 18/2016 ዓ.ም
የባለልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር/ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኢትዮጵያ ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ተፈረመው በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር እንዲሁም በአሊያንስ ፎር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ መካከል ነው፡፡
ስምምነቱን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በኩል የፈረሙት ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ሁሴን አምቦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር ቦርድ ፕሬዝደንት እንዲሁም በአሊያንስ ፎር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኩል ደግሞ ሚ/ር አርዊን ናቸው፡፡
ውድድሩ በአገራችን ከ2012-2014 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ጊዜያት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በርካታ የቡና አርሶ አደሮችን በአፍታ ሚሊየነር ያደረገ እንደነበር አይዘነጋም፡፤ በተለያዩ ምክንያቶች ውድድሩ በባለፈው አመት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በዘንድሮ አመት ግን ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገልጸው፤ አርሶ አደሩ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ቡናውን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መሰብሰብ እና ማዘጋጀት እንደሚገባው እና ራሱንም ለዚህ ከፍተኛ ውድድር እንዲያዘጋጅ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡