Ethiopian Coffee and Tea Authority
6.03K subscribers
5.9K photos
30 videos
67 files
372 links
Ethiopian Coffee and Tea Authority
Download Telegram
ስፔሻሊቲ ቡና ምንድነው? ስፔሻሊቲ ቡና ብለን ከምንጠራው ስያሜ በስተጀርባ ያለው እውነታ!! ለቅምሻ ያህል….
ሳህለማርያም ገ/መድህን
ስፔሻሊቲ ብለን ስንል የተለየ፣ የተመረጠ፣ ደረጃው ከፍ ያለ ወይም ባለ ዝና የሚል እሳቤ ወደ እዝነ ልቡናችን ይመጣልናል፡፡ ይህን ቃል ወደ ቡናችን ስናመጣውም ትርጉሙ ከዚህ እምብዛም የተለየ እንዳልሆነ እንመለከታለን፡፡ ነገር ግን የንግዱ/commercial የሆነውን ቡና ሳይሆን (ስፔሻሊቲ ቡና) በመባል የሚታወቀው ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡና ከአበቃቀል ጀምሮ እስከ መሰብሰብ፣ ማዘጋጀት፣ ማጓጓዝ፣ ማቀነባበር ብሎም እስከ መቁላት እና ቅምሻ ድረስ ያለውን ሂደት ለመግለጽ/ለማመልከት የሚያገለግል ቃል ነው።
ይህ ቡና በአሁኑ ሰዓት በአለማቀፍ ደረጃ ከሚቀርቡ ቡናዎች አንጻር ያለው ድርሻ 15 በመቶ ሲሆን በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኝ ገበያ ነው፡፡ ከዋጋም አንጻር አሁን ባለው የገበያ መረጃ መሰረት በፓውንድ ከ3-5 ዶላር እየተሸጠ የሚገኝ ቡና ነው፡፡
ልዩ ቡና ልዩ መሆኑ ከሚታወቅባቸው ባህርያት መካከል፤ እንደአለማቀፉ ልዩ ቡናዎች ማህበር Specialty Coffee Association (SCA) ስታንዳርድ «ምጥን በሆነ ሁኔታ በእጅጉን የተለየ ጥፍጥና/ቃና ወይም ጣዕም ያለው መሆኑ ፕሮፌሽናል የሙያው ባለቤት በሆኑት ቀማሾች መረጋገጡ ሲታመን እና ከመቶኛ የሚሰጡት ውጤትም ከሰማንያ አጋማሽ በላይ ያስመዘገቡ መሆን ሲችሉ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ስፔሻሊቲ ቡና ከሚለው በስተጀርባ ያለው ታሪክ…
"ልዩ ቡና" የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1974 ኤርና ክኑትሰን በተባለ ሰው "የሻይ እና ቡና ንግድ ጆርናል" እትም ላይ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ Knutsen ቃሉን የተጠቀመው በተወሰኑ/በታወቁ አካባቢዎች በቅለው፣ ልዩ ባህርይ እና ጣዕም ኖሯቸው ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የቡና ዛላ/ፍሬዎችን ለመግለጽ የተጠቀመበት ነው፡፡
ግብይቱ የተጀመረውም ስታር ባክስ በሚባል ኩባንያ አማካይነት እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በዚያ በኋላ ባሉ ቀጣዮቹ ዓመታት ደግሞ የቡና ኢንዱስትሪው በፍጥነት እያደገ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የልዩ ቡናዎች ገበያ ዕድገትም በዚያው ልክ እድገቱን አስመዝግቧል። በዚሁ መሰረት የሚከተሉት ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ለልዩ ቡና ስታንዳርድ ለማውጣት እና በዚያ መሰረትም ደረጃ ለመስጠት/ለመገምገም ደረጃዎች እንዲዘጋጁ ተደርገዋል፤

ሀ. የቡናው ጥራት፡- ልዩ ቡና ጥሩ ጣዕም ያለው እና ምንም አይነት/ የተጋነነ እንከን የለሽ መሆን አለበት።
ለ. እንዴት እንደሚመረት፡- ስፔሻሊቲ ቡና ብዙ ጊዜ አካባቢ ጥበቃን እና ሰራተኞችም ፍትሃዊ የስራ ሁኔታ አላቸው ወይ? የሚለውን ጥያቄ በሚመልስ ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጎ በዘላቂነት/ sustainably ይመረታል።
ሐ. ዱካው መታወቅ፡- ልዩ ቡና ብዙ ጊዜ የጠራ መነሻ አለው፣ እያንዳንዱ የቡና ክፍል ከየትኛው ማሳ ተመረተ፣ ምን አይነት እንክብካቤ እና ታሪክ አለው፣ የት/እንዴት ተለቀመ፣ የት/እንዴት ተዘጋጀ፣ የት/እንዴት ተጓጓዘ ወይም የት/እንዴት ደረሰ የሚለውን ጥያቄ በግልጽ ሊመልስ ይችላል።
መ. ደረጃ አሰጣጥ፤ የስፔሻሊቲ ቡና ማህበር (SCA): በልዩ የቡና ኢንዱስትሪ ውስጥ ግንባር ቀደም የሙያ ድርጅት በመሆኑ የSCA አጠቃላይ የቡና ደረጃ አሰጣጥ ስነ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ደረጃ አሰጣጡ ይከናወናል፡፡
ሠ. ማሸግ እና ነጥብ መስጠት፡- ቡና ደረጃውን/ስታንዳርድ በጠበቀ ሁኔታ መጠቅለያ ዘዴ/እሸጋ ተጭኖ ከ100 ነጥብ መለኪያ ሲመዘን ስፔሻሊቲ ቡና ነው ለመመባል 80 ነጥብ ከረገጠ እና ከዚያ በላይ ከሆነ እንደ ልዩ ቡና/ specialty ቡና ይቆጠራል።
አስደሳች ዜና!! የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን  ለመጀመርያ ግዜ በአፍሪካ ፋይን ኮፊ አሶስዬሽን እና በኢንተር አፍሪካ ኮፊ ኦርጋናይዜሽን የጋራ ጥምረት  የሚከበረውን የመጀመርያው "የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ" እና  20ኛው የአፍሪካ ፋይን ኮፊ አሶስዬሽን ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን  ከጥር 28 እስከ የካቲት 2/2016 ዓ.ም በመዲናችን አዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ያካሄዳል፡፡
በዝግጅቱ ከ600 በላይ ታዳሚዎች ተሳታፊ ይሆናሉ። በመድረኩም ከፍተኛ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣ በቡና ልማትና ግብይት ዘርፍ የታወቁ ተመራማሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ አለማቀፍ ቡና ገዢዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ይታደማሉ፡፡
የኢትዮጵያ ምድር ያበቀለቻቸው የተለያየ ዝርያ ያላቸው ቡናዎችም ቀርበው ታዋቂ ባለሙያዎች እና እንግዶች እንዲቀምሱት፣ እንዲያጣጥሙት ይደረጋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ይህንን  አለማቀፍ ሁነት ለማከናወን የቅድመ ዝጅግት ስራውን ማጠናቀቁን ስንገልጽ በታላቅ ኩራት ነው፡፡

«የአፍሪካ የቡና ሳምንት በኢትዮጵያ»
ቡናችን ወርቃችን፤ ቡናችን መለያ፣ ክብር እና አንድነታችን!!!
በቡና ማሰልጠኛ ማዕከሉ በዘመናዊ የቡና አቆላል ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ጥር 15/ 2016 ዓ.ም
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቡና ምርትና ግብይት ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት በተለያዩ ጊዜያት ሲያደርገው እንደቆየው ሁሉ በዛሬው ዕለትም ከዩኒዶ ጋር በመተባበር ከዚሁ ተቋም ጋር በጋራ ባቋቋመው የቡና ማስልጠኛ ማዕከል ዕሴት የተጨመረበት ቡና ጥራቱን ጠብቆ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በዩኒዶ በኩል ከጣሊያን የመጡና የካበተ ልምድ ያላቸው አሰልጣኘ ሲሆኑ ስልጠናውን የወሰዱት ደግሞ ከቡና ቆዬዎች ማኅበር ለመጡና ሌሎች አጋር አካላት ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞችም ስልጠናውን እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን 5 ሴቶችና 10 ወንዶች በድምሩ 15 ሰልጣኞች ስልጠናውን ወስደዋል፡፡ ይህ ለሶስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ዕሴት የተጨመረበት ቡና አዘጋገጃጀት ላይ ያለው የዕውቀትና የክህሎት ክፍተት ይዘጋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ ስልጠናው በንድፈሃሳብና በተግባር የተሰጠ ሲሆን በዋናነት በኤሌክትሪክና በጋዝ ማሽኖች እንዴት ጥራቱን ጠብቆ መቁላት ላይ ያለተኮረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከስልጠና ማዕከሉ እንደተገለጸው ስልጠናው በሶስት ዙር የተሰጠ ስልጠና አንዱ አካል ሆኖ ይህ ሶስተኛው ዙር ስልጠና እንደሆነና መሰል ስልጠና ለዚህ ቀደም በሁለት ዙር እንደተሰጠ አስተውሰዋል፡፡ ሁለቱን ስልጠናዎች አስመልክቶ የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ክፍል በዜና ማስነበቡ ይታወሳል፡፡
ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!!
ጥር 18/2016 ዓ.ም

የባለልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር/ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኢትዮጵያ ለማካሄድ የሚስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ተፈረመው በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን፣ በኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር እንዲሁም በአሊያንስ ፎር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ መካከል ነው፡፡
ስምምነቱን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በኩል የፈረሙት ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ ክቡር ዶ/ር ሁሴን አምቦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የቡና ማህበር ቦርድ ፕሬዝደንት እንዲሁም በአሊያንስ ፎር ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በኩል ደግሞ ሚ/ር አርዊን ናቸው፡፡
ውድድሩ በአገራችን ከ2012-2014 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ተከታታይ ጊዜያት መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በርካታ የቡና አርሶ አደሮችን በአፍታ ሚሊየነር ያደረገ እንደነበር አይዘነጋም፡፤ በተለያዩ ምክንያቶች ውድድሩ በባለፈው አመት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በዘንድሮ አመት ግን ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ገልጸው፤ አርሶ አደሩ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ቡናውን ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ መሰብሰብ እና ማዘጋጀት እንደሚገባው እና ራሱንም ለዚህ ከፍተኛ ውድድር እንዲያዘጋጅ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡