EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
31.9K photos
323 videos
79 files
12.3K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ከፈቱ
************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎትን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሰራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ሰዋል።

ለዚህም ማሳያ የሆነውን የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ዛሬ መመረቁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ይኽን አዲስ ማዕከል የሚገልጡ ሶስት ቁልፍ አላባውያን አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የቆየ እና የተጎዳ ህንፃን ወደ ዘመናዊ እና ሥነውበታዊ ደረጃው ለሥራ ከባቢ አስደሳች ወደ ሆነ ህንፃ መለወጡ አንዱ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከልን መረቁ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
12ቱ ተቋማት በአንድ ጣሪያ ሥር
*************

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር ምርጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው።

የአሰራር ስረአቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል። ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያሰቀር ነው፡፡

አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት አስራ ሁለት የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን አርባ አንድ የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችንም አቅርበዋል፡፡

አገልግሎቶቹም ከፈቃድ አሰጣጥ ጀምሮ ፋይዳ ድጅታል የመታወቂያ ምዝገባ እና ሌሎችንም አካትተዋል። በአጠቃላይ በፓይለት ፕሮግራም በአንድ ስፍራ የ12 ተቋማት 41 አገልግሎቶች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ።

እነዚህም ፡
1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምሀርት ምዘና እና ፍተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም
ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡም ይገኛሉ።
#PMOEthiopia


ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ክሪስታል ፓላስ ለኤፍ ኤ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰ
**************

በእንግሊዝ የኤፍ ኤ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ አስቶንቪላን 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ፍፃሜው ማለፍ ችሏል።

የክሪስታል ፓላስን ቀዳሚ ግብ ኤዜ በ31ኛ ደቂቃ ሲያስቆጥር፤ ቀሪዎቹን 2 ግቦች ሳር በ58ኛ እና በ90ኛ ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

በታሪካቸው የኤፍ ኤ ዋንጫን አሳክተው የማያውቁት ፓላሶች በፍፃሜው ጨዋታ አዲስ ታሪክ ለማፃፍ የሚያደርጉት ግጥሚያ ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።

ክሪስታል ፓላስ ነገ ማንቸስተር ሲቲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ከሚያደርጉት ጨዋታ በኋላ በፍፃሜው የሚገጥመውን ቡድን የሚያውቅ ይሆናል።

በሴራን ታደሰ

የስፖርት ፌስቡክ ገፅን ይወዳጁ

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
ሩሲያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ዝግጁ ናት - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን
**************

ሩሲያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከዩክሬን ጋር የሰላም ድርድር ለማድረግ ዝግጁ ናት ሲሉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለፁ፡፡

ፑቲን ይህን የገለፁት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ አራተኛውን የሞስኮ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ነው።

ቭላድሚር ፑቲን ከስቲቭ ዊትኮፍ ጋር ባደረጉት ውይይት የሩስያ ወገን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከዩክሬን ጋር የሚያደርገውን ድርድር ለመቀጠል ዝግጁ መሆኑን መግለፃቸውን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

የሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድር

ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ

ኢቢሲ ድረ ገፅ

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ