EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
31.8K photos
323 videos
79 files
12.3K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
አርሰናል በሜዳው ነጥብ ጣለ
****************

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 34ኛ ሳምንት መርኃ ግብር በሜዳው ኢምሬትስ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው አርሰናል 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።

ለአርሰናል ግቦቹን ኪቪዮር እና ትሮሳርድ ሲያስቆጥሩ ኤዜ እና ማቴታ የክሪስታል ፓላስን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

በጨዋታው ላይ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት የነበራቸው መድፈኞቹ ሁለት ጊዜ መምራት ቢችሉም ውጤታቸውን ማስጠበቅ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
ሪያል ማድሪድ ሄታፌን በማሸነፍ ወሳኝ ድል አሳክቷል

በስፔን ላሊጋ 33ኛ ሳምንት ከሜዳው ውጪ ከሄታፌ የተጫወተው ሪያል ማድሪድ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል::

የሪያል ማድሪድን የአሸናፊነት ግብ አርዳ ጉለር ማስቆጠር ችሏል::

ውጤቱን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ በ 72 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በሪያል ማድሪድ በኩል መጥፎው ዜና ወሳኙ አማካኝ ካማቪንጋ ጉዳት ማስተናገዱ ሆኖል::

ጉዳቱ ከቅዳሜው የኮፓ ዴላሬ የፍፃሜ ጨዋታ ውጪ ሊያደርገው እንደሚችል አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ተናግረዋል።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ
ማስታወቂያ
**********

የሲንቄ ባንክ የዲጅታል ባንኪንግ መተግበሪያን ከplay store በማውረድ አሁኑኑ ይመዝገቡ፣ አገልግሎቱን ያስጀምሩ!

Appilikeeshinii Dijiitaal Baankiingii Baankii Siinqee 'Play Store' irraa  buufachuun ammuma galmaa'aa, tajaajila isaa jalqabsisaa.

#Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan
#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER
ማስታወቂያ
****
ሬስ ማይክሮ ፋይናንስ እና ሁድ ሁድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመተባበር የተመቻቸ ብድር
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በካዛንቺስ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ የተሳተፉ አካላትን አመሰገኑ
********

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በካዛንቺስ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ በመሳተፉ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትላንት ማምሻውን በካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ ሃገር የማበልፀግ ራዕያችንን በመጋራት በርካታ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን፣ እረፍት አልባ የስራ መርሃግብር በማሳለፍ አብረውን ለሰሩ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ተቋማትን አመስግነናል ብለዋል።

ከእነዚህም መካከል ማሽኖቻቸውን በነጻ ለዚህ ስራ ያዋሱ ባለሃብቶችን፣ ስራ ወስደው በፍጥነትና በጥራት ፕሮጀክቶችን በጊዜ በማጠናቀቅ ያስረከቡ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን አመስግነዋል።

አክለውም ይህን ስራ ከጅማሮ እስከ ፍጻሜ በፍጹም ታታሪነት እና ቅንነት ያስተባበሩ የከተማችን አመራሮችን፣ የግል የመንግስትና የፌደራል ተቋማትን እንዲሁም የህንጻ ባለንብረቶችን ራዕያችንን በመጋራት ሃገር በመገንባት ስራችን ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅዖ ሁሉ በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

በካዛንቺስ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ
ቻይና በባሕር ላይ ማረፍ እና መነሳት ለሚችለው አውሮፕላን የገበያ ፈቃድ ሰጠች
***************

በባሕር ላይ ማረፍ እና መነሳት የሚችለውየቻይናው AG600 አምፊቢየስ አውሮፕላን በሀገሪቱ ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር የገበያ ፍቃድ ሰርተፊኬት በይፋ ተሰጥቶታል።

‘የውሃ ድራጎን’ የሚል ስያሜ የተሰጠው አውሮፕላኑ ግዝፈቱ እና ክብደቱ የዓለማችን ትልቁ አምፊቢየስ አውሮፕላን እንዲሆን አስችሎታል፡፡

AG600 አምፊቢየስ አውሮፕላኑ በውኃ እና በመሬት ላይ ማረፍ እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ነው።

አንድ ጊዜ በተሞላ ነዳጅ 4 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የመሸፈን አቅም ያለው ይህ አውሮፕላን፣ ከባድ እሳት አደጋን ለማጥፋት፣ የባሕር ላይ ፍለጋ ለማካሄድ እና ለነብስ አድን ተልዕኮዎች እንደሚውል ተጠቁሟል።

አውሮፕላኑ 12 ቶን ውኃ እና 50 ሰዎችን የመጫን አቅምን እንዳለውም ተጠቅሷል።

ይህ የአውሮፕላን ስሪት ቻይና በአቪዬሽን ኢንደስትሪ የበላይነት እንድትቀዳጅ ከማስቻሉ ባሻገር፣ ለሚከሰቱ አደጋዎች ፈጣን እና አመርቂ እርምጃ ለመውሰድ የሚስችላት ነው ሲል ሲጂቲኤን በዘገባው አመላክቷል።

በአፎሚያ ክበበው
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የካዛንቺስ የመልሶ ማልማት አካል የሆነው ኡራኤል የሚገኘው የሕዝብ መናፈሻ
ዳዊት አስፋው የአፍሪካ ቴክዋንዶ ህብረት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጡ

የአፍሪካ ቴክዋንዶ ኅብረት በአዲስ አበባ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ ሲያካሂድ ተቋሙን በቀጣይ አራት አመታት የሚመሩትን የፕሬዝደንት እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።

የኢትዮጵያ ወርልድ ቴክዋንዶ ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ዳዊት አስፋው የአህጉሩ ቴክዋንዶ ኅብረት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል።

ተቋሙን በፕሬዝደንትነት የመሩት የኒጀሩ ኢዴ ኢሳቅ በድጋሜ ለቀጣይ አራት አመታት በፕሬዝዳንት ለመምራት ተመርጠዋል።

በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በተደረገው ጉባዔ 52 ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚንስተር ዴኤታ መኪዩ ሙሀመድም ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት የአፍሪካ ቴክዋንዶ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ እና የፕሬዝዳንሻል ዋንጫን የምታዘጋጅበት መሆኑን መኪዩ ሙሀመድ አስታውቀዋል።

ቴክዋንዶ አንድነትን በማምጣትና ከምንም በላይ ለወጣቶች ተስፋ የሆነ ስፖርት መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

በጉባዔው በአፍሪካ ቴክዋንዶ ህብረት ከ2021 ጀምሮ እስከ 2025 የተከወኑ ስራዎች ቀርበዋል።

ባለፉት 5 አመታት የታዳጊዎች ስልጠና እና ውድድሮች ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው በሪፖርት ቀርቧል።

ነገ የወርልድ ቴክዋንዶ የአፍሪካ ፕሬዝዳንሻል ዋንጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ይጀመራል።

ለ3 ቀን በሚቆው ውድድር ከ35 ሀገራት በላይ የሚሳተፉበትም ይሆናል።

ዳዊት አስፋው ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጡ

በአንተነህ ሲሳይ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር ጋኦ ዩንሎንግ ጋር ተወያዩ
******************

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለጋኦ ዩንሎንግ እና ለልዑክ ቡድናቸው ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጡ ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፡፡

በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሊቀ መንበሩ ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለው ትብብር