EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
138K subscribers
31.8K photos
323 videos
79 files
12.3K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ስቅለት በቦሌ መድኃኔዓለም በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ሲከበር (በምስል)፦

📸 ኢቢሲ ዶትስትሪም
የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከስግደት ለሚመለሱ ክርስቲያን እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ አጋሩ
***********

በድሬዳዋ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከስግደት ለሚመለሱ ክርስቲያን እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ አጋሩ።
ሙስሊሞች ለክርስቲያን እህት ወንድሞቻቸው ማዕድ አጋሩ
በቦሌ መድኃኔዓለም የተካሄደው የጥብጣቦ ሥርዓት
*********************

በሰሙነ ህማማት ሃይማኖታዊ እና ትውፊታዊ ክንውኖች ይከናወናሉ፤ ከእነዚህም ውስጥ ጥብጣቦ አንዱ ነው።

በዕለተ አርብ ካህናት ስግደቱን ካበቁ በኋላ ምዕመናን አንገታቸውን ዝቅ አድርገው፣ ጀርባቸውን ሰጥተው በወይራ እየተጠበጠቡ (ቸብ ቸብ እየተደረጉ) ሐጢአታቸውን ለካህን ይናገራሉ።

ጥብጣቦ የሚደረግለት ሰው በህማማቱ ወቅት የፈፀመው በደል ወይም ሐጢአት ቢኖር ይህንኑ ተናግሮ ስግደት ይቀበላል፤ ካህኑም ይህን ያህል ስገዱ እያሉ ለእያንዳንዱ ምዕመን ይሰጣሉ።
ከኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የምንማረው ይቅርታ ማድረግን፣ ትህትናን እና መከባበርን ነው፦ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል
************

የሰው ልጆች ከኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የምንማረው እርስ በርስ ይቅርታ ማድረግን፣ ትህትናን እና መከባበርን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ገለጹ።

የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በስግደት፣ በፆምና በጸሎት ተከብሯል።
ከስቅለት የምንማረው ይቅርታ ማድረግን፣ ትህትናን እና መከባበርን ነው
የሰሙነ ሕማማት መጨረሻዋ ዕለት ቅዳሜ ነች፡፡ በዚህች ዕለት ምዕመናን በጠዋቱ ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ኪዳን አድርሰው ቄጠማ በራሳቸው አስረው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ በዚህ ዕለት የሚጾም ቢሆንም ስግደት አይሰገድም፤ መስቀልም መሳለም አይቻልም፡፡

የትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ከቀድሞው በተለየ መልኩ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል "ቀዳም ሥዑር" ወይም የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች።

የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋው በመቃብር የዋለበት በመሆኑ ምእመናንም እንደ ሐዋርያት የትንሣኤውን ብርሃን ሳናይ እህል አንቀምስም በማለት በጾም ያሳልፏታል።
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=10828
ማስታወቂያ
****
ሬስ ማይክሮ ፋይናንስ እና ሁድ ሁድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በመተባበር የተመቻቸ ብድር