በአማራ ክልል 1 ሺህ 224 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው
****************
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በእርምት ቆይታቸው የባሕርይ ለውጥ ላመጡና መስፈርቱን ላሟሉ 1 ሺህ 224 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን አስታወቀ።
የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፤ በአጠቃላይ የ1 ሺህ 463 ታራሚዎች የይቅርታ ጥያቄ ለክልሉ የይቅርታ ቦርድ ቀርቦ ነበር።
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በቀረቡት የይቅርታ ጥያቄዎች ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ፣ 1 ሺህ 224 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ገልጸዋል።
ታራሚዎቹ ለዚህ ይቅርታ ሊበቁ የቻሉት በእርምት ቆይታቸው ባሳዩት መልካም የባሕርይ ለውጥ እና የይቅርታ መመሪያው የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች በሙሉ በማሟላታቸው መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል 139 የሚሆኑት የሕግ ታራሚዎች አስፈላጊውን መስፈርት ባለማሟላታቸው ይቅርታቸው ተቀባይነት ሳይታገኝ ቀርቷል።
ይህ የይቅርታ ውሳኔ ታራሚዎቹ ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለው ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሩ ዕድል የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።
በሳሙኤል ወርቅአየሁ
#EthiopianBroadcastingCorporation #EBC #AmharaRegion #Justice #Amnesty #Ethiopia #EBCDOTSTREAM

❤19👍2👏2🙏1
በአዳማ ከተማ የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ ተመረቀ
********
ኢትዮ ቴሌኮም በአዳማ ከተማ ያስገነባውን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ በይፋ አስመርቋል።
በአዲስ አበባ ሥራ የጀመሩትን ሦስት ጣቢያዎች ተከትሎ በአዳማ የተገነባው ይህ ጣቢያ የተቋሙ አራተኛው ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ 12 መኪኖችን ቻርጅ የማድረግ አቅም አለው።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በምረቃው ወቅት፣ ተቋሙ ለአካባቢ ጥበቃና ለዘመናዊ ትራንስፖርት ትኩረት በመስጠት የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን እያስፋፋ ይገኛል ብለዋል።
እስከ አሁንም ከ284 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ካሉት ጣቢያዎች 7.1 ሚሊዮን ኪሎ ዋት ኃይል መጠቀም መቻላቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ አዳማ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለባት ከተማ በመሆኗ ይህ ጣቢያ ለከተማዋና በመስመሩ ለሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች ትልቅ እፎይታ እንደሚፈጥር አብራርተዋል።
በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም በዘርፉ ለሚሰማሩ አካላት ምቹ አሠራር የሚፈጥር "National EV charging platform" ወደ ሥራ ማስገባቱንና መሰል ማዕከላትን በሌሎች ከተሞችም ለማስፋት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ በበኩላቸው፣ ጣቢያው "ስማርት አዳማን" እውን ለማድረግ ለሚከናወነው ሥራ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል።
በዕለቱ ኢትዮ ቴሌኮም የመጨረሻውን የ"ኢትዮ_130 ሜጋ" ፕሮሞሽንና የ"ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት" ባለዕድለኞችን በመለየት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽልማቶችን አስረክቧል።
ይህ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊና ለአካባቢ ተስማሚ ወደሆነ የትራንስፖርት ሥርዓት የምታደርገውን ሽግግር የሚያፋጥን መሆኑ ተጠቁሟል።
በአባዲ ወይናይ

❤17👍4🤣3
የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርት በኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊሰጥ ነው
********************
የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ትምህርትን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስፋፋትና የትምህርቱን ጥራት ለማረጋገጥ ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮዎች ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
ስምምነቱ በዋናነት የመምህራንን የማስተማር ብቃት በማሳደግና የሙያ ማረጋገጫ (Professional Certificate) አሰጣጥ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ትምህርት ቢሮዎች ለሥልጠናው ብቁ የሆኑ መምህራንን የመለየት፣ አስተባባሪዎችን የመመደብና አስፈላጊውን የሎጂስቲክስ ድጋፍ የማመቻቸት ኃላፊነት እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል።
#EBC #Ethiopia #China #Education #AAU #LanguageLearning #Partnership

❤30👍5🤣3👏1
እስካሁን ከ36 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
****************
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ36 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በድምሩ 36,971,981 መራጮች መመዝገባቸውን ገልጿል።
ከተመዝጋቢዎቹ ውስጥ 20,122,327 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 16,849,654 ደግሞ ሴት መራጮች መሆናቸው ተመልክቷል።
ቦርዱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ በተመለከተም 76,609 ወንድ እና 72,451 ሴት የአካል ጉዳተኛ መራጮች ለምርጫው መመዝገባቸው ታውቋል።
#EthiopianBroadcastingCorporation #EBCDOTSTREAM #Ethiopia #GeneralElection

❤27🤣5👍4🤩1
የመደመር አንቀፅ
አምራች ኢንዱስትሪው ለአንድ ሀገር አጠቃላይ የውስጥ ምርት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል ሲባል በቀጥታ ከሚኖረው አስተዋጽዖ በላይ ነው፡፡
በሌሎች ዘርፎች ላይ በሚኖረው ተጽዕኖ የሚያበረክተውም አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው። የተሻለ ገቢ ያለው ማኅበረሰብ ለመፍጠር ለሚደረገው ርብርብም ዋነኛው የትኩረት ዘርፍ የአምራች ዘርፍ ነው፡፡
አምራች ኢንዱስትሪውን ወደ ከፍታ የማምጣትና የማበልጸግ ጉዳይ፣ ከኢኮኖሚና ከማኅበራዊ ጥቅሙ ባለፈ፣ ደኅንነትንና ሉዓላዊነትን ከማስከበር አንጻርም ሚናው ከፍተኛ ነው። በሌሎች ሀገራት አምራች ኢንዱስትሪ ላይ ጥገኛ ሆኖ፣ ራስን ሳይችሉ፣ ሉዓላዊ ሀገርነን ማለት ቀልድ ነው፡፡
የመደመር መንግሥት
ገፅ 197
Ethiopian Broadcasting Corporation #IPDC #Ethiopia #industry #Medemer

❤13👏3
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኅብረተሰቡ ከሐሰተኛ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ አሳሰበ
********************
ኅብረተሰቡ ከሐሰተኛ ዜናዎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭት ራሱን እንዲጠብቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አሳስቧል።
ጽ/ቤቱ ቤቱ ባስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክት፣ “ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተብሎ የሚደርስዎትን ማንኛውም ይፋዊ መልዕክት ከማጋራትዎ በፊት ሁልጊዜም በጽሕፈት ቤቱ ይፋዊ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች እና ድረ-ገጽ በመግባት፣ ትክክለኛነቱን እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን” ብሏል።
https://www.facebook.com/share/1DbRTPiYUF/?mibextid=wwXIfr
X: https://x.com/pmethiopia?s=21
Website: https://pmo.gov.et
#Ethiopia #PMOEthiopia

❤8🙏7👍3🔥1🥰1
ምዝገባው ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል!!!!
*****************
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ ቀርተዋል። እርስዎም ጊዜው ሳይረፍድ ዛሬውኑ ካርድዎን ይውሰዱ፤ በምርጫ ብቻ ለውጥ ያምጡ።
ምርጫ ካርድ አለመውሰድ የራስዎን እና የቤተሰብዎን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሌላ አካል እንዲወስን በራስዎ ፈቃድ ዕድሉን አሳልፎ መስጠት ነው።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ የመራጮች ምዝገባ ሰኞ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
የምዝገባው ሂደት ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ስለቀሩት፣ እስካሁን የምርጫ ካርድ ያልወሰዳችሁ ዜጎች ቀሪዎቹን ቀናት እንድትጠቀሙ እናስታውሳለን።
በሀገርዎ የዴሞክራሲ ልምምድ ውስጥ ለመወሰን እና የዜግነት ግዴታዎን ለመወጣት የድምፅ መስጫ ካርድዎን ይያዙ።
ድምፅ መስጠት መብትዎ ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ተሳትፎዎ መገለጫ ነው።
በሚቀርብዎ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት ወይም በምርጫዬ መተግበሪያ በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ ይችላሉ።
ምርጫዬ መተግበሪያን፦
ለአንድሮይድ (Play Store): https://play.google.com/store/apps/details..
ለአይፎን /iOS/ (App Store):
https://apps.apple.com/us/app/mirchaye/id6756587049
በድረ-ገጽ https://mirchaye.portal.nebe.org.et/
Ethiopian Broadcasting Corporation #Ethiopia #Election2026 #VoterRegistration #Registration #VoteEthiopia

❤11
ኢራን ከአሜሪካ ጋር ያላትን ቅራኔ በዘላቂነት የምትፈታበት አዲስ የዲፕሎማሲ መፍትሄ ተመላከተ
****************
የ2015ቱን የኑክሌር ስምምነት በማርቀቅ ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት የቀድሞው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዘሪፍ፣ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ያላትን ቅራኔ በዘላቂነት የምትፈታበትን አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ አመላክተዋል።
ቴህራን ያላትን ጂኦ-ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ ለጦርነት ሳይሆን ለድርድር ልትጠቀምበት ይገባል ብለዋል።
ኢራን የዓለምን የነዳጅ መስመር የምትቆጣጠርበትን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ የመዝጋት አቅምና የኑክሌር መርሐ ግብሯን እንደ ትልቅ የድርድር ካርድ ልትጠቀምባቸው ይገባል ይላሉ።
ዘሪፍ እንደሚሉት፣ ኢራን እነዚህን ወሳኝ ተፅዕኖዎች ለዋሽንግተን እንደ ማባበያ በማቅረብ፣ በምላሹ በሀገሪቱ ላይ የተጣሉ ከባድ የኢኮኖሚ ማዕቀቦች እንዲነሱ ማድረግ ትችላለች።
ይህ "በበላይነት የመደራደር ስልት" ቀደም ሲል አሜሪካ ያልተቀበለቻቸውን ጥቅሞች አሁን እንድትቀበል የሚያስገድድና ለሁለቱም ሀገራት የሚበጅ አዲስ ስምምነት ለመፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ፍጥጫ የንጹሃን ዜጎችን ሕይወት ከመቅጠፍና መሠረተ ልማትን ከማውደም ባለፈ ፋይዳ እንደሌለው የገለጹት ዘሪፍ፣ የኢራን መሪዎች ከስሜታዊነት በፀዳ መልኩ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ሊያስከብሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጦርነቱን መቀጠል ዘላቂ ሰላምን አያመጣም፤ ስለሆነም ሁለቱ ሀገራት የማይጠቃቁበት እና ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚፈጥሩበት ስምምነት ላይ መድረስ፣ ኢራንን ከጥፋት ከመታደግ ባለፈ በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል ነው ያሉት።
የዘሪፍ ጥሪ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ስምምነት ላይ ካልደረሰች "ወደ ድንጋይ ዘመን ትመለሳለች" የሚል ማስፈራሪያ በሰነዘሩበትና በቴህራን በኩል የጦርነት ነጋሪት በሚጎሰምበት ወቅት መቅረቡ፣ ለዲፕሎማሲው መስክ አዲስ ተስፋን የፈነጠቀ ሆኗል።
በኢንቲሀድ አብራር
#middleeast #peace #Iran #USA #EBC

❤16👍3🔥2