ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የምርጫ ማኒፌስቶውን ይፋ አደረገ
***************
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት በ2018 ዓ.ም በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደርበትንና ስትራቴጂካዊ የፖሊሲ አቅጣጫዎቹን የያዘውን ማኒፌስቶ ይፋ አድርጓል።
ጥምረቱ በማኒፌስቶው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች የሚከበሩበት፣ የሕግ የበላይነት የሰፈነበትና በኢኮኖሚ የበለፀገች ሀገር የመገንባት ራዕይ ይዟል።
በሕዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ...https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0HUg4iHPLXr9cyHVMv8Qg5sxPYWkUuegm3z46XEHrmLTynH9qQt71wEH7oLhxmRXkl

❤6
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚዲያ አጠቃቀም እና የድልድል ቀመር ይፋ ሆነ
**************************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚውለውን የነፃ የሚዲያ አጠቃቀምና የድልድል ቀመር ይፋ አድርጓል። ድልድሉ ፍትሐዊነትንና አካታችነትን መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ያካትታል፦
✅ የድልድል መመዘኛዎች፦
ድልድሉ 40% ለሁሉም እኩል፣ 25% እንደ እጩዎች ብዛት፣ 15% ለሴት እጩዎች፣ 15% ለአካል ጉዳተኛ እጩዎች እንዲሁም 5% ለሴት አካል ጉዳተኛ እጩዎች ትኩረት ሰጥቶ ተዘጋጅቷል።
✅ የተመደበ የሚዲያ መጠን፦
ለ47 የፖለቲካ ፓርቲዎችና የግል እጩዎች በድምሩ፦
• 782.5 ሰዓታት በሬዲዮ፤
• 513 ሰዓታት በቴሌቪዥን፤
• 576 አምዶች በጋዜጣ ተመድቧል።
✅ የሚሳተፉ ተቋማት፦
በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት 24 የሬዲዮ ጣቢያዎች፣ 20 የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና 6 የሕዝብ ጋዜጦች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ሆነዋል።
ይህ አሠራር ሁሉም ተፎካካሪዎች አማራጭ ሐሳባቸውን ለሕዝብ የሚያቀርቡበት የዴሞክራሲያዊ ምኅዳር ማሳያ ነው።

❤12
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
*******************
አንጋፋውና የታሪክ ባለቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የገጠመውን የመፍረስ አደጋ ለመታደግ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አካላትን በማስተባበር የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
ክለቡ ላለፉት ስድስት ወራት ደመወዝ መክፈል የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ አስተዳደሩ ከከተማዋ በጀት ከወሰነው በተጨማሪ ለባለሀብቶች ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ቢጂአይ ኢትዮጵያ በሰጡት ፈጣን ምላሽ የገንዘብ ድጋፉ ለተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚቴ ተበርክቷል።
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግርኳስ ክለብ የተጫዋቾችና የማኅበሩ ብቻ ሳይሆን የሀገርና የከተማችን ኩራት በመሆኑ፣ ይህንን ታሪካዊ ክለብ ከውድቀት የመታደግ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።
ድጋፍ ላደረጉት ተቋማትና ለስፖርቱ ቤተሰብ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ከንቲባ አዳነች፣ ይህ እርምጃ አስተዳደሩ ለስፖርት ወዳዱ ሕዝብ የሰጠው ክብር ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
ክለቡ ሁሉንም ባሳተፈና በግልጽነት አዲስ ቦርድ መርጦ፣ ከገጠመው ጊዜያዊ ችግር ተላቆ ወደ ቀድሞ ጥንካሬውና ዝናው እንዲመለስም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
#Ethiopia #SaintGeorgeSA #AddisAbaba #KidusGiorgis #SportSupport #mayoradanechabiebie

👍20❤17🥰4
እስካሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ ወስደዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
*******************
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በድምሩ 28 ሚሊዮን 365 ሺህ 310 መራጮች መመዝገባቸውን ገልጿል።
ከተመዝጋቢዎቹ መካከል 15 ሚሊዮን 317 ሺህ 567ቱ ወንዶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 13 ሚሊዮን 47 ሺህ 743ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።
በሌላ በኩል፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳቸውን ለሕዝብ እንዲያስተዋውቁ ለማስቻል በሕዝብና በንግድ መገናኛ ብዙኃን ላይ የነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ ዓምድ ድልድል መደረጉን ቦርዱ አስታውቋል።
በላሉ ኢታላ
#EthiopianBroadcastingCorporation #EBCDOTSTREAM #Ethiopia #GeneralElection

❤12🔥10👏10👍1🙏1
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ50 ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን በታላላቅ የምረቃና የዐውደ ርዕይ ኩነቶች አከበረ
**************************
ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረውን የስኬት ጉዞ በተለያዩ ተግባራት እያከበረ የሚገኘው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ዛሬ ሶስት አበይት ኩነቶችን በይፋ አከናውኗል፦
✅ ልዩ የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ፦ የኮርፖሬሽኑን የ50 ዓመት የልማትና የዕድገት ታሪክ የሚያሳይ የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ ተከፍቷል።
✅ ዘመናዊው "ጎልድ ሞል" ምረቃ፦ በፒያሳ መሀል ለወርቅ ንግድ ሱቆች አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የተገነባው ዘመናዊ የንግድ ሕንፃ ተመርቋል።
✅ የ27 ወለል ሁለገብ ሕንፃ ምረቃ፦ በሱማሊ ተራ አካባቢ ያስገነባው፣ 3 ቤዝመንት፣ ምድር ቤት እና 23 ወለሎች (3B+G+23) ያሉት እጅግ ዘመናዊ ሁለገብ ሕንፃ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
እነዚህ ስኬቶች የኮርፖሬሽኑን ለሀገር ልማትና ለከተማ ውበት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳያሉ። እነዚህ ሁነቶች በምስል ይመልከቱ፦
#FHC50Years #GoldJubilee #Ethiopia #AddisAbaba #Inauguration

❤12👍1
የኢትዮጵያ የትንሳኤ ጉዞ፦ ከመጋቢት እስከ መጋቢት የከፍታና የብርሃን ስምንት ዓመታት
************
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የታሪክ አውድ ውስጥ መጋቢት ወር የድልና የነፃነት ተምሳሌት ነው። ጥንት በየካቲት ወር መጨረሻ ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት የታወጀበት ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም አዲስ የለውጥ ማዕበል ይዞ ብቅ ማለቱ ይታወሳል።
ከመጋቢት 2010 እስከ መጋቢት 2018 ዓ.ም ባሉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ኢትዮጵያ ውስብስብ ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር፣ የማይታመኑ አሻራዎችን ያሳረፈችበትና ሁለንተናዊ ገጽታዋን የቀየረችበትን አዲስ ምዕራፍ እውን አድርጋለች።
ይህ የለውጥ ጉዞ በፖለቲካው መስክ መሠረታዊ የሆነ የትርክት ሽግግር ያመጣ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የነበረውን በዜጎች መካከል የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ዜግነት ስሜት የፈጠረ፣ የተወሰኑ የፖለቲካ ኃይሎችን ብቻ የበላይና ባለቤት ያደረገውን በመቀየር ሁሉንም ህዝቦች እኩል ባለቤት ያደረገ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን አንግሷል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02zKsqojhw9aQ8GeKedvmaR5uNvqd3M38TcxXw8Jo3bBrXxHyJPA3BEV4CdxYwwcfhl

❤33👏3🙏3
ኢራን የፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ 20 ተጨማሪ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲያልፉ ፈቀደች
***************************
ኢራን በፓኪስታን ስም የተመዘገቡ 20 ተጨማሪ መርከቦች ለሳምንታት ተዘግቶ በቆየው የሆርሙዝ ሰርጥ በኩል እንዲያልፉ መስማማቷን ፓኪስታን አረጋገጠች።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር ይህንኑ ውሳኔ በ‘ኤክስ’ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ያረጋገጡ ሲሆን፣ “እርምጃው የሚደነቅ እና ገንቢ ነው” ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም "ይህ የኢራን እርምጃ የሰላም አብሳሪ እና በቀጣናው መረጋጋትን ለማምጣት የሚረዳ ነው፤ ውይይት፣ ዲፕሎማሲ እና መሰል መተማመንን የሚፈጥሩ እርምጃዎች ለጦርነት ብቸኛ መፍትሔዎች ናቸው" ብለዋል።
ፓኪስታን በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ዙሪያ ዛሬ (እሑድ) የሚካሄደውን የአራትዮሽ ስብሰባ ለማስተናግድ መርሐ-ግብር ይዛለች።
በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት አንድ ወር በደፈነበት በዚህ ወቅት፣ የቱርክ፣ የፓኪስታን፣ የግብፅ እና የሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በኢስላማባድ በመገኘት፣ ውጥረቱን ለማርገብ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ይመክራሉ።
የሆርሙዝ ሰርጥ የዛሬ ወር ገደማ በተቀሰቀሰው የአሜሪካ-እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ምክንያት ከፈረንጆቹ መጋቢት ወር መጀመሪያ አንሥቶ በተግባር ተዘግቶ ቆይቷል።
ግጭቱ ከመከሰቱ በፊት በቀን በአማካይ 138 መርከቦች በወሽመጡ በኩል ያልፉ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።
በዮናስ በድሉ
#EBC #MiddleEast #Iran #USA #Israel #worldaffairs

❤33🙏13