ሪያል ማድሪድ ዛሬ ነጥብ ከጣለ ባርሴሎና ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል
******************
በስፔን ላሊጋ 36ኛ ሳምንት መርኃ ግብር ሪያል ማድሪድ በሜዳው ዛሬ ምሽት 4:30 ማዮርካን ያስተናግዳል።
የካርሎ አንቾሎቲው ሪያል ማድሪድ በዚህ ዓመት በላሊጋው በባርሴሎና በ 7 ነጥቦች ተበልጦ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ጨዋታ ከተሸነፈ ባርሴሎና ሻምፒዮንነቱን ሳይጫወት ያረጋግጣል።
ወደ ብራዚል ብሄራዊ ቡድን ማምራታቸው የተረጋገጠው ካርሎ አንቾሎቲ በጨዋታው በቂ የመጫወቻ ጊዜ ላላገኙ ተጨዋቾች ዕድል እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
በሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች ዲፖርቲቮ አላቬስ ከ ቫሌንሽያ፤ ቪያሪያል ከ ሌጋኔስ በተመሳሳይ ምሽት 2 ሰዓት ይጫወታሉ።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
ኢቢሲ የስፖርት ገፅ
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ

👍9🤬3😭3❤2
የአውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ
****************
የአውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ከስምምነት ላይ መድረሱን የሕብረቱ የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጃዳ ካላስ ተናግረዋል።
አዲሱ ማዕቀብ የሩሲያ የንግድ መርከቦችና የነዳጅ ዘይት ንግድ ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል።
ማዕቀቡ የሩሲያ ጦር ዩክሬን ላይ የሚፈፅመውን ጥቃት ለማስቆም ያለመ ነው ሲሉ ካጃ ካላስ ተናግረዋል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።
የአውሮፓ ሕብረት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ በሩሲያ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን ሲጥል እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
****************
የአውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል ከስምምነት ላይ መድረሱን የሕብረቱ የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጃዳ ካላስ ተናግረዋል።
አዲሱ ማዕቀብ የሩሲያ የንግድ መርከቦችና የነዳጅ ዘይት ንግድ ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል።
ማዕቀቡ የሩሲያ ጦር ዩክሬን ላይ የሚፈፅመውን ጥቃት ለማስቆም ያለመ ነው ሲሉ ካጃ ካላስ ተናግረዋል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።
የአውሮፓ ሕብረት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ በሩሲያ ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን ሲጥል እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
👎22👍16
"ፋይዳ እያንዳንዱ ሰው ሊኖረው የሚገባ ወሳኝ ነገር ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************
ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እያንዳንዱ ሰው ሊኖረው የሚገባ ወሳኝ ነገር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ፋይዳ በአሁኑ ሰዓት የዜጎችን ማንነት ከመለየት ባለፈ የተለያዩ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፓስፖርት ያላቸው በርካታ የውጭ ዜጎች አሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "በተለይ ጎረቤቶቻችን ከኛ ባህል ቋንቋ እና አኗኗር ጋር የሚመሳሰል ዘይቤ ይዘው እዚሁ ይኖራሉ ይህን ለመለየት ፉይዳ ያለው ጥቅም የጎላ ነው" ብለዋል፡፡
ፋይዳ ለአንድ ኢትዮጵያዊ የዜግነቱ ማረጋገጫ ጭምር ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፋይዳ በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ተቋማት አገልግሎቶችን ለማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀላሉ ማንነትን የሚለይ በመሆኑ ጌዜን በመቆጥብ አገልግሎትን ለማሳለጥ በእጅጉ ያግዛል ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ከ 15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡
እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ እስከ 20 ሚሊዮን ለመድረስ እቅድ እንደተያዘም ጠቅሰዋል፡፡
በሚቀጥለው ዓመት እስከ 67 ሚሊዮን የመድረስ ዕድል ይኖረናል ሲሉም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ

👍70👎9❤8🤬2🥰1👏1
የልጅነት ሕልሟን መኖር የጀመረችው ረዳት ፓይለት ኬርማይ እሸቱ
**********
የተወለደችው እና ያደገችው አዲስ አበባ ውስጥ ነው። ለወላጆቿ 5ኛ ልጅ የሆነችው ኬርማይ ከልጅነቷ ጀምሮ አውሮፕላን አብራሪ በመሆን ሀገሯን የማገልገል ሕልም ነበራት።
ይህንን ሕልሟን ለማሳካት የአባቷን፣ የእናቷን እና የእህቶቿን ጠንክሮ የመሥራት ፈለግ በመከተል በከፍተኛ ውጤት ረዳት አብራሪ በመሆን ዘንድሮ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ካስመረቃቸው 974 ባለሙያዎች መካከል አንዷ ነች ረዳት ፓይለት ኬርማይ እሸቱ (ዶ/ር)።
የወላጆቿ ቤት ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ በመሆኑ የአውሮፕላኖችን ድምፅ አዘውትሮ መስማት እና ከሩቁ የማየት ዕድል ነበራት።
ወደ ሰማይ የሚምዘገዘገው አውሮፕላን ታዲያ አንሶ ስለሚታያት “ይህ ትንሽ ነገር” እንዴት ሰው ጭኖ ከሀገር ወደ ሀገር መብረር እንደቻለ ያስገርማት ነበር።
ሕፃን እያለች አባቷ በትምህርት ምክንያት ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ ስለነበር የአውሮፕላን ድምፅ በሰማች ቁጥር ከቤት ወደ ውጭ እየወጣች “አባቴን ጣለው፤ አባቴን ጣለው” ብላ ትጮህ እንደነበር እናቷ ወ/ሮ ሳራ ስዩም ይናገራሉ።
የዛሬዋ ረዳት ፓይለት ኬርማይ እሸቱ (ዶ/ር) ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቷን በሊሴ ገብርማርያም ትምህርት ቤት በመከታተል የላቀ ውጤት አምጥታ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀላቀለች።
ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በነበራት ቆይታ ብቃት ባላቸው አሠልጣኞች ያገኘችው ሥልጠና ሀገሯን በኃላፊነት ለማገልገል ብቁ እንዳደረጋት ለኢቢሲ ዶትስትሪም ትናገራለች።
“በተለይም የአየር በረራ ልምምዱን ከአዲስ አበባ ውጭ ከቤተሰብ ተለይቶ እንደ ወታደር ሌሊት 11:30 እየተነሡ፣ አልጋ እያነጠፉ፣ ጫማ እየጠረጉ መሥራቱ ሀገርን ዝቅ ብሎ በትህትና እንዳገለግል ቀርፆኛል” ትላለች።
ሀገርን የማገልገል ትምህርት የቀሰመችው እርሻ እያረሰ ተምሮ ትልቅ ደረጃ ከደረሰው አባቷ ነው።
ወደፊትም ትጋቷን በመቀጠል በሙያዋ፣ በኃላፊነት፣ በሐቀኝነት፣ በትህትና ሀገሯን ለማገልገል እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች።
ትልቅ ሕልምን ይዞ በመትጋት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ማሳያ የሆነው የረዳት ፓይለት ኬርማይ እሸቱ (ዶ/ር) የህይወት ጉዞ ለብዙ አዳጊዎች ማነቃቂያ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በላሉ ኢታላ

👍29❤16
ቦሎኛ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ሻምፒዮን ሆነ
በኮፓ ኢጣሊያ የፍፃሜ ጨዋታ ቦሎኛ ኤሲ ሚላንን 1 ለ 0 በማሸነፍ ከ 51 ዓመት በኋላ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።
በሮም ኦሎምፒክ ስቴዲየም በተደረገው የዋንጫ ጨዋታ የቦሎኛን የማሸነፊያ ግብ ዳን ንዶይ አስቆጥሯል::
ቦሎኛ በታሪክ ሶስተኛ የኮፓ ኢጣሊያ ዋንጫውን አሳክቷል።
ኤሲ ሚላን በኮፓ ኢጣሊያ የፍፃሜ ጨዋታ ሲሸነፍ ለ 10ኛ ጊዜ ሲሆን ይህም የመጀመሪያው ቡድን ያደርገዋል።
ቦሎኛ ዋንጫውን ማንሳቱን ተከትሎ በቀጣይ አመት ዩሮፓ ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።
ከ2003 በኋላ የጣልያን ዋንጫን ማንሳት ያልቻለው ኤሲ ሚላን የከተማ ተቀናቃኙን ኢንተር ሚላንን አሸንፎ ለፍጻሜ ቢደርስም ዋንጫውን ማንሳት አልቻለም።
የጣሊያን ዋንጫን ለመጨረሻ ጊዜ በ1974 ያነሳው ቦሎኛ ይሄንን ክብር ለማሳካት ከ5 አስርት አመታት በላይን ጠብቋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
ኢቢሲ የስፖርት ገፅ
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
በኮፓ ኢጣሊያ የፍፃሜ ጨዋታ ቦሎኛ ኤሲ ሚላንን 1 ለ 0 በማሸነፍ ከ 51 ዓመት በኋላ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።
በሮም ኦሎምፒክ ስቴዲየም በተደረገው የዋንጫ ጨዋታ የቦሎኛን የማሸነፊያ ግብ ዳን ንዶይ አስቆጥሯል::
ቦሎኛ በታሪክ ሶስተኛ የኮፓ ኢጣሊያ ዋንጫውን አሳክቷል።
ኤሲ ሚላን በኮፓ ኢጣሊያ የፍፃሜ ጨዋታ ሲሸነፍ ለ 10ኛ ጊዜ ሲሆን ይህም የመጀመሪያው ቡድን ያደርገዋል።
ቦሎኛ ዋንጫውን ማንሳቱን ተከትሎ በቀጣይ አመት ዩሮፓ ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።
ከ2003 በኋላ የጣልያን ዋንጫን ማንሳት ያልቻለው ኤሲ ሚላን የከተማ ተቀናቃኙን ኢንተር ሚላንን አሸንፎ ለፍጻሜ ቢደርስም ዋንጫውን ማንሳት አልቻለም።
የጣሊያን ዋንጫን ለመጨረሻ ጊዜ በ1974 ያነሳው ቦሎኛ ይሄንን ክብር ለማሳካት ከ5 አስርት አመታት በላይን ጠብቋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
ኢቢሲ የስፖርት ገፅ
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ
👍23🤣1
ከለንደን ወደ ፓሪስ የሚመላለሱ የተደራራቢ ባቡሮች ውጥን
*************
አውሮፓውያኑ ለንደንን እና ፓሪስን በሚያገናኘው የባቡር መስመር ላይ ተደራራቢ የሕዝብ ማመላለሻ ባቡሮችን ስራ ለማስጀመር ዕቅድ ይዘዋል።
ታዲያ እነዚህ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ተደራራቢ ባቡሮች የተሳፋሪዎችን ቁጥር በእጅጉ እንደሚያሳድጉ እና ዝቅተኛ የትራንስፖርት ክፍያ ዋጋ ሊኖራቸው እንደሚችል ተገልጿል።
ዩሮስታር እና ቨርጂን ግሩፕ ኩባንያዎች እያደገ የመጣውን የሰው ልጅ የመጓጓዣ ፍላጎት ለማሟላት እና የፈረንሳይ ስሪት የሆኑትን ተደራራቢ ባቡሮች ለማሰራት ከባቡር አምራቾች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልፀዋል።
ተደራራቢ ባቡሮቹ መቼ ወደ አገልገሎት እንደሚገቡ የቴሌግራፍ ዘገባ ባያመላክትም፤ በዝቅተኛ ወጪ በቂ አገልግሎት እንደሚሰጡ የሚጠበቁት ባቡሮች በቀጣይ ዓመት ሙሉ በሙሉ ሊመረቱ እንደሚችል ተጠቁሟል።
በህንድ የተለያዩ ከተሞችን የሚያገናኙ ተደራራቢ ባቡሮች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።
በሴራን ታደሰ

👍23