EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
133K subscribers
43K photos
483 videos
80 files
13.6K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
የጎዴ የመስኖ መሰረተ-ልማት ፕሮጀክት ለምግብ ሉዓላዊነት ትልማችን አይነተኛ ስንቅ ነው - አብርሃም በላይ (ዶ/ር)
*****************

የጎዴ የመስኖ መሰረተ-ልማት ፕሮጀክት ለምግብ ሉዓላዊነት ሰፊ ትልማችን አይነተኛ ስንቅ ነው ሲሉ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የጎዴ የመስኖ መሰረተ-ልማት ፕሮጀክት ምረቃ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል፡፡

የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት ፅሁፍ፤ ይህ የስኬት ጅምር ለምግብ ሉዓላዊነት ሰፊ ትልማችን አይነተኛ ስንቅ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎዴ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ምረቃት ላይ በመገኘታቸው እና ተግባር ወደ ዘላቂ ባህል እንዲያድግ ለሰጡት አመራርና ትኩረት ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።
👍238
ኢቢሲ በይዘቶቹ ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ችሏል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*******************

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባደረጋቸው የይዘት ለውጦች ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆን ችሏል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ይህን ያሉት ሸጎሌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና መስርያ ቤትን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡

ኢቢሲ ከዋና የስርጭት ጣቢያው በተጨማሪ ጊዜውን በዋጀው የማህበራዊ ሚዲያም ይበልጥ ተደራሽ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የተደረጉ የይዘት ለውጦች በርካቶች የቴሌቪዥን ጣቢያው ተከታታይ እንዲሆኑ አስችሏል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሁሉም የማህበራዊ ትስስር አማራጮች መገኘቱም ተደራሽነቱን እንደጨመረው ተናግረዋል፡፡

ባደረጉት ጉብኝት የቴክኒክ ለውጦች መመልከታቸውን የገለፁት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም አሁን ላለው የይዘት ለውጥ መሰረት መሆኑን አንስተዋል፡፡

በራስ አቅም ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶችን በማድነቅ ያንን ለማጎልበት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያድረግም ነው የተናገሩት፡፡

ኢቢሲ ውድድሩ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ሚዳያዎች ሳይሆን ከውጪ መገናኛ ብዙሃን ጋር ሊሆን እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ውይይት፣ የሃሳብ ነፃነት እና ሀገርን ማስተዋወቅ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

በአፎሚያ ክበበው
👍16👎53
በተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምክንያት ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ
***************

በአዲስ አበባ ከተማ በአንዳንድ መንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምክንያት ነዋሪዎች ለእንግልትና አላስፈላጊ ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን ለኢቲቪ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ አገልግሎት ፈልገው ወደሄዱባቸው አንዳንድ ተቋማት በቀጠሮ ብዛት እየተመላለሱ ለአላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት መዳረጋቸውን ነው በሰጡት አስተያየት የተናገሩት፡፡

ከ8 ወር በፊት የአገልግሎት ክፍያ ባለመፈጸማቸው የውኃ አቅርቦት እንደተቋረጠባቸው የገለጹት አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ምንም እንኳን የተጠየቁትን ክፍያ ቢፈጽሙም ቆጣሪው መልሶ እንዳልተገጠመላቸው ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢው በአዲስ አበባ ውኃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮልፌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ8 ወራት ያህል እየተመላለሱ መሆኑንና እስካሁንም ችግሩ እንዳልተፈታላቸው ነው የገለጹት፡፡

ሌላኛው ተገልጋይ ደግሞ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ለማግኘት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው በቀጠሯቸው መሰረት መታወቂያቸውን ከኢትዮጵያ ፖስታ በወቅቱ መረከብ አለመቻላቸውን እና ለእንግልት መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም አሰራሩን በማዘመን አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02EzvEetNBo7pY6A5v9CzWma8EL4yvwrAJ2rvWQuPRM7tRr41PeEJ2p7wAJMwSEXLrl
👍182
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተገኙበት የጎዴ የመስኖ መሰረተ-ልማት ፕሮጀክት የምረቃ ስነ ስርዓት
👍20
የውሃ ሀብቶቻችንን ለኢትዮጵያ ልማት በጥቅም ላይ ለማዋል እያደረግናቸው ያሉ ጥረቶች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስገኙ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
************

የውሃ ሀብቶቻችንን ለኢትዮጵያ ልማት በጥቅም ላይ ለማዋል እያደረግናቸው ያሉ ጥረቶች ተስፋ ሰጪ ውጤት እያስገኙ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መረጃ፥ በሶማሊ ክልል በእርሻ ይለማ የነበረውን 350 ሺህ ሄክታር መሬት ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በሦስት እጥፍ ማሳደግ መቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል።
21👍9
የገና በዓል የፀጥታ ማስከበር ተግባራትን አስመልክቶ ለጥምር የፀጥታ አካላት አመራር የሥራ መመሪያ ተሰጠ
*******

ጥምር የፀጥታ አካላት አመራር የ2017 ዓ.ም የገና በዓል የፀጥታ ማስከበር ተግባራትን አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሠላም አዳራሽ ለአመራሩ የሥራ መመሪያ ተሰጥቷል።

በመድረኩ የሕግ ማስከበሩን ሥራ በውጤት ለማከናወን የሚያስችል ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ውይይቱን የመሩትና መመሪያ የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ናቸው።

ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በዓላት ሲከበሩ አሉታዊ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች እንደመልካም አጋጣሚ እንዳይጠቀሙበት ከሚከናወነው መደበኛ የወንጀል መከላከል ስራ ጎን ለጎን የህብረተሰቡን አቅም መጠቀም ፈፅሞ መዘንጋት የሌለበት ሥራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ቅንጅታዊ የሥምሪት አቅጣጫን በመከተል ጠንካራ የወንጀል መከላከል ተግባር ማከናወን እንደሚገባም አመላክተዋል።

አያይዘውም፥ የፀጥታ አካላቱ ዋና ግብ በሕግ የበላይነት ሠላምና ፀጥታን ማረጋገጥ በመሆኑ፤ ሁሉም አመራርና አባል ይህን ተገንዝቦ በዓሉ በሠላም እንዲከበር እንደ ከዚህ ቀደሙ ኃላፊነቱን በብቃት ሊወጣ እንደሚገባ መመሪያ ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው፥ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ ተቀናጅቶ በመስራቱ ስኬታማ መሆን እንደተቻለ ተናግረዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02SrwatTZEgYpu4FBnrVnmgtcd4kX4VHZ2iakw9wzTxa8siWMmcNkYidQp4wpVbB6yl
👍17