EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
133K subscribers
43.1K photos
483 videos
80 files
13.6K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ከጃፓኑ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የተረፉት ግለሰቦች ያቋቋሙት ማህበር የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸነፈ
**************

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 አሜሪካ በሂሮሺማ ከተማ ላይ የአቶሚክ ቦምብ በመጣሏ ወደ 140,000 የሚጠጉ ሰዎች ተገደሉ።

ከሶስት ቀናት በኋላ ሁለተኛው የአቶሚክ ቦምብ በናጋሳኪ ከተማ ላይ ተጣለ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ጃፓን እጅ ሰጠች፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነትም አበቃ።

ታዲያ ከዚህ የሂሮሺማ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የተረፉት ቶሺዩኪ ሚማኪ እና ከጥቃቱ የተረፉት ሌሎች ጃፓናውያን ያቋቋሙት "ሂባኩሻ" ማህበር የ2024 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፏል።

ሂባኩሻ የተባለው ይህ ማህበር እ.ኤ.አ. በ1945 በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ከደረሰው የቦምብ ጥቃት የተረፉ ሰዎችን ያቀፈ ማህበር ሲሆን፤ በቶሺዩኪ ሚማኪ ኒዮን ሊቀመንበርነት ይመራ ነበር፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0T4Fhk8Dz9sKkDVLyVx62qcaYT3hGudQchH6qQY1UGDnsVdoPJWLMbgcBDnie3gQGl
👍26👏84
የግብርናውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ምርታማነት ለማሸጋገር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)
***************************

የግብርናውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ምርታማነት ለማሸጋገር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ሩሲላን ናሲቦቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዘርባጃን የንግድ ልዑካን ቡድን የግብርና ኢንቨስትመንት እድሎችን እና አማራጮችን ለመመልከት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ተገልጿል፡፡

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን የግብርና ኤክስፖርት ትብብር ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንዳለውም ተጠቁሟል።

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የአየር ንብረት ለውጥ በግብርናው ዘርፍ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እና ለማስተካከል እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02HtHoCUNWo4E6UhWx33P2U9xCSfUNL5VkNePj4J8K8HV8HR5Yeo1qFpNR4dL6V8v4l?cft[0]=AZU-3Nvsz-qt0x65_27hicjDmpN1WvWeiKkOgPHXRwyN50NRWmsbOnID4_aODtAnOAz-mpiAjgCvbcqqetwD7dHrs6ZW60XDuxWcbybdqLkQyrYGkjjdFkPraPwguvJ989NkhYSHnCzG57rPxLvsORnIRYFmWM_gIOB_pC0yMkK-W8DjqUAzKARSlo-Ra-6pMzw&tn=%2CO%2CP-R
👍211
ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች
*****************************

ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት ሚኒስትሩ፤ ዩናይትድ ኪንግደም ማሻሻያዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በዘላቂነት እንድትደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች በማድነቅ ለውጡ በኢትዮጵያ የንግድ ምቹነትን እንደሚያሻሻል ተናግረዋል፡፡

ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች የምታደርጋቸውን ድጋፎች አጠናክራ እንደምትቀጥልም መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።
👍47👎74
አዲሱ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ የወጪ ገቢ ንግድን ለማቀላጠፍ እያገዘ ነው - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
**********************

አዲሱ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ የወጪ ገቢ ንግድን ለማቀላጠፍ እያገዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል፡፡

ባንኩ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአራት ዙር 282 ሚሊዮን 459 ሺህ 436 ዶላር ለበርካታ ደንበኞች መደልደል መቻሉን ገልጿል፡፡

በአራት ዙር ከፈቀደው የውጪ ምንዛሬ ውስጥም ደንበኞቹ የተጠቀሙት በአማካይ 28 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0aUKhnzjNEMvsP1LRMxAA8upPDs8D4Mcofg2GggKbFsn2s38PfBnBe82UgAQmJw4Tl?cft[0]=AZUcWbO-osog0toO3bvAAKbbmp1Zg5rwk-_sMoBTrJ_JOxAm65MhMxLrt-NxezIun8QoEIVcYtMME9uSNJYGRiviUXO4VJn4RnEBL78cQ3Icf-6xgAECsATE0TeCby6Whx1_zqLegTITfUc8ZqwntVOGHQ_980-xjkRFoUR7xuZB_Q&tn=%2CO%2CP-R
👍49👏41
"የሐረሪ ክልል የወጠነው አዲስ ፈጥኖ ደራሽ የማሽላ ምርት ትልቅ ተስፋ አሳይቷል። ከዚህ ቀደም ጾም ያደረ መሬትን በማልማት በሄክታር በአማካይ 43 ኩንታል ምርት ይጠበቃል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍26👏1
"በባህር ዳር የተገነቡ የልማት ስራዎች እጅግ ውብ እና ማራኪ ናቸው"፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
**********

"በውቢቷ ባህር ዳር የተገነቡ መናፈሻዎችን እንዲሁም ግዙፉንና አስደማሚውን የአባይ ድልድይ ጎብኝተናል" ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "እነዚህ የልማት ስራዎች እጅግ ውብ እና ማራኪ ናቸው" ሲሉ ገልፀዋል።

የልማት ስራዎቹ ለህዝባችን እንዲሁም ከሩቅም፣ ከቅርብም ለሚመጡ ቱሪስቶች ማረፊያነትና መዝናኛነት ምቹ የሆኑ ከተሞችን ለመገንባት እየሰራን ስለመሆኑ ማረጋገጫ አሻራዎች ናቸው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉብኝቱ በኋላ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ።
👍31👏42👎2