EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
133K subscribers
43K photos
483 videos
80 files
13.6K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
በአነፍናፊ ውሾች የታገዘ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ዝውውርን መከላከል የሚያስችል ልዩ የቁጥጥር ማዕከል ሥራ ጀመረ
*************

በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በአነፍናፊ ውሾች የታገዘ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶች ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችልና የቁጥጥር ስራዎችን ለማከናወን የሚያግዝ ልዩ የቁጥጥር ማዕከል ሥራ መጀመሩ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እና በአፍሪካን ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን የቴክኒክ ድጋፍ የተቋቋመው ልዩ የቁጥጥር ማዕከሉን የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊመርቀው ሥራ አስጀምረዋል።https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02LdX3KxmvMiifNHXbjr66LSgvPL4qtLT1ZK7XHJ6hU3hZ7mMPFeuVEH1pP2xuZ535l
👍29👏93
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ጋር ተወያዩ
****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የቶኒ ብሌር ኢንስቲቲዩት ዋና ሊቀመንበር ከሆኑት ቶኒ ብሌር ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስሰር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ መጠነ ርዕይ ባላቸው አለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡

የቶኒ ብሌር ኢንስቲቲዩት በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተም መነጋገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
👍406👏4
ከገቢ ግብር የሚሰበሰበው የኢትዮጵያ ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፦ ገቢዎች ሚኒስቴር
****************

ባለፉት ዓመታት በተሰሩ የለውጥ ስራዎች ከገቢ ግብር የሚሰበሰበውን የኢትዮጵያ ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለው መምጣቱን የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይን ዓለም ንጉሴ በተለይ ለኢቲቪ እንደገለጹት፤ግብርን በታማኝነት መክፈል የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚረዳ መሰረት ነው፡፡

በ2010 በጀት ዓመት ከገቢ ግብር የተሰበሰበው 170 ቢሊዮን ብር እንደነበር ያስታወሱት ሚኒስትሯ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቶ በ2016 ዓ.ም 512 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ የህሕግ ማዕቀፎች፣የአሰራር ሥርዓቶች እንዲሁም የቴክኖሎጂ አማራጮችን ማሻሻል መቻሉ ለተገኘው እድገት አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02YVm5mB7cwbKZed3EmFLQ32LLUA4Ri6WW9bEuLWeFf2pohF5EBUysCHRr4DBGcjSTl
👍21👎42
ከጃፓኑ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የተረፉት ግለሰቦች ያቋቋሙት ማህበር የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸነፈ
**************

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 6 ቀን 1945 አሜሪካ በሂሮሺማ ከተማ ላይ የአቶሚክ ቦምብ በመጣሏ ወደ 140,000 የሚጠጉ ሰዎች ተገደሉ።

ከሶስት ቀናት በኋላ ሁለተኛው የአቶሚክ ቦምብ በናጋሳኪ ከተማ ላይ ተጣለ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ጃፓን እጅ ሰጠች፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነትም አበቃ።

ታዲያ ከዚህ የሂሮሺማ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የተረፉት ቶሺዩኪ ሚማኪ እና ከጥቃቱ የተረፉት ሌሎች ጃፓናውያን ያቋቋሙት "ሂባኩሻ" ማህበር የ2024 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፏል።

ሂባኩሻ የተባለው ይህ ማህበር እ.ኤ.አ. በ1945 በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ከደረሰው የቦምብ ጥቃት የተረፉ ሰዎችን ያቀፈ ማህበር ሲሆን፤ በቶሺዩኪ ሚማኪ ኒዮን ሊቀመንበርነት ይመራ ነበር፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0T4Fhk8Dz9sKkDVLyVx62qcaYT3hGudQchH6qQY1UGDnsVdoPJWLMbgcBDnie3gQGl
👍26👏84
የግብርናውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ምርታማነት ለማሸጋገር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል - ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)
***************************

የግብርናውን ዘርፍ ወደ ተሻለ ምርታማነት ለማሸጋገር ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ሩሲላን ናሲቦቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዘርባጃን የንግድ ልዑካን ቡድን የግብርና ኢንቨስትመንት እድሎችን እና አማራጮችን ለመመልከት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ተገልጿል፡፡

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን የግብርና ኤክስፖርት ትብብር ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንዳለውም ተጠቁሟል።

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የአየር ንብረት ለውጥ በግብርናው ዘርፍ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እና ለማስተካከል እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02HtHoCUNWo4E6UhWx33P2U9xCSfUNL5VkNePj4J8K8HV8HR5Yeo1qFpNR4dL6V8v4l?cft[0]=AZU-3Nvsz-qt0x65_27hicjDmpN1WvWeiKkOgPHXRwyN50NRWmsbOnID4_aODtAnOAz-mpiAjgCvbcqqetwD7dHrs6ZW60XDuxWcbybdqLkQyrYGkjjdFkPraPwguvJ989NkhYSHnCzG57rPxLvsORnIRYFmWM_gIOB_pC0yMkK-W8DjqUAzKARSlo-Ra-6pMzw&tn=%2CO%2CP-R
👍211
ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች
*****************************

ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት ሚኒስትሩ፤ ዩናይትድ ኪንግደም ማሻሻያዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በዘላቂነት እንድትደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች በማድነቅ ለውጡ በኢትዮጵያ የንግድ ምቹነትን እንደሚያሻሻል ተናግረዋል፡፡

ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ የልማት ሥራዎች የምታደርጋቸውን ድጋፎች አጠናክራ እንደምትቀጥልም መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።
👍47👎74
አዲሱ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ የወጪ ገቢ ንግድን ለማቀላጠፍ እያገዘ ነው - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
**********************

አዲሱ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ የወጪ ገቢ ንግድን ለማቀላጠፍ እያገዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል፡፡

ባንኩ ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአራት ዙር 282 ሚሊዮን 459 ሺህ 436 ዶላር ለበርካታ ደንበኞች መደልደል መቻሉን ገልጿል፡፡

በአራት ዙር ከፈቀደው የውጪ ምንዛሬ ውስጥም ደንበኞቹ የተጠቀሙት በአማካይ 28 በመቶ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0aUKhnzjNEMvsP1LRMxAA8upPDs8D4Mcofg2GggKbFsn2s38PfBnBe82UgAQmJw4Tl?cft[0]=AZUcWbO-osog0toO3bvAAKbbmp1Zg5rwk-_sMoBTrJ_JOxAm65MhMxLrt-NxezIun8QoEIVcYtMME9uSNJYGRiviUXO4VJn4RnEBL78cQ3Icf-6xgAECsATE0TeCby6Whx1_zqLegTITfUc8ZqwntVOGHQ_980-xjkRFoUR7xuZB_Q&tn=%2CO%2CP-R
👍49👏41
"የሐረሪ ክልል የወጠነው አዲስ ፈጥኖ ደራሽ የማሽላ ምርት ትልቅ ተስፋ አሳይቷል። ከዚህ ቀደም ጾም ያደረ መሬትን በማልማት በሄክታር በአማካይ 43 ኩንታል ምርት ይጠበቃል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍26👏1