EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
133K subscribers
43.1K photos
483 videos
80 files
13.6K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ሙስናን መቀነስና የግብር አሰባሰብ ሥርዓትን ማዘመን ግልፅ፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አሰራር ለመፍጠር ወሳኝ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************

በግብር አሰባሰብ ላይ እየታዩ ያሉ አዎንታዊ ለውጦችን ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ሙስናን መቀነስ እና የግብር አሰባሰብ ሥርዓታችንን ማዘመን ለሁሉም የተመቸ፣ ግልፅ፣ ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ አሰራር ለመፍጠር ወሳኝ ነውም ብለዋል።

የ6ኛው የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና የሽልማት መርሐ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ተካሂዷል።

ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ተሸላሚዎችን "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።

የዜግነት ግዴታችሁን ለመወጣት ያደረጋችሁት ቁርጠኝነት ምስጋና የሚገባው ነውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ታማኝነት ከግለሰብ ይጀምራል፤ ግብር መክፈል ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የዚያ እምነት መገለጫም ነው፤ ለበለጠ ጥቅም ሁላችንም የምንካፈለው ግዴታችንም ነው ብለዋል።

መንግሥት በታማኝነት የከፈላችሁት ግብር ለጋራ እድገታችን ወሳኝ በሆኑ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል ብለዋል።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02BpxhHFkSPXNbfY7NRTSDpYozYq5ehuSy6hnEpjN75PGiHfPkzbaBR8MpXpGmcF9El
👍252👏2
2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ወደ ትግበራ የገባው ከህብረተሰቡ ጋር በቂ ውይይት ተደርጎ ነው - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
**************

2ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት ከልማት ተነሺ ነዋሪዎች ጋር ውይይት መደረጉን የአዲስ አበባ ከንቲባ ዋና አማካሪ ሞላ ንጉስ ገለፁ።

በልማቱ አንዱ የትኩረት ማዕከል ህብረተሰቡን ማወያየት እንደነበር የጠቀሱት ዋና አማካሪው፤ በዚህም የልማቱ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የሆኑት የከተማዋ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባ፣ የክፍለ ከተሞች ስራ አስፈፃሚዎች እና ሌሎች አመራሮች ከነዋሪዎች ጋር መወያየታቸውን ገልፀዋል።

በውይይቱ ህብረተሰቡ በልማቱ ላይ ጥያቄ እንዳላነሳ ገልፀው፤ ይህም በቀዳሚው የኮሪደር ልማት አመርቂ ውጤት በመገኘቱ መሆኑን ተናግረዋል።

በውይይቱ በነዋሪዎች የተነሱ ጥያቄዎች የእኛ መብት ምንድን ነው? የምትክ ቤት ጉዳይ እንዴት ይሆናል? የሚሉት መሆናቸውን ገልፀዋል።

ተነሺዎቹ በዕጣ ፍትሃዊ የሆነ እና ማህበራዊ አንድነትን የማያሳሳ ድልድል እንዲያገኙ መደረጉንም ተናግረዋል።

ከምትክ ቤት አሰጣጥ እና መሰል ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ ይህንኑ የሚያስተናግድና ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ አሰራር በወረዳዎች ስለመኖሩ ገልፀዋል።

የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ውበታቸውን እንደጠበቁ እንዲቆዩ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ጋር በጋራ እየተሰራ ስለመሆኑም አንስተዋል።

በመጀመሪያው ዙር የተሰራው የኮሪደር ልማት ውጤታማነት ህብረተሰቡ ከልማቱ ጎን እንዲቆም እና መሰረተ ልማቱንም በባለቤትነት እንዲጠብቅ ማስቻሉንም የአዲስ አበባ ከንቲባ ዋና አማካሪ ሞላ ንጉስ ተናግረዋል።

በአፎምያ ክበበው
👍417👏6👎4
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዕለቱ የምንዛሬ ዋጋ
👍163👏1
በ2017 ተቋማዊ ነፃነትን የጠበቀ የፍትህ ስርዓትን ለማጠናከር ይሰራል - የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
*****************

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም መደበኛ የዳኝነት የስራ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በመከናወን ላይ ይገኛል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረቱ በ2016 በርካታ ሪፎርሞች መደረጋቸውን አስታውሰው፤ በተለይም በቴክኖሎጂ የተደራጀ አሰራር በሰፊው መተግበሩን አንስተዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በተስተዋሉ ግድፈቶች ላይ እርምት መወሰዱን ያነሱ ሲሆን ከተለያዩ ተቋማት በጋራ ተሰርቷል ብለዋል።

በ2017 ዓ.ም ተቋማዊ ነፃነትን የጠበቀ የፍትህ ስርዓትን ማጠናከር፣ ለዳኞች ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር፣ የተጠያቂነት ስርዓትን በአግባቡ መተግበር፣ የሽግግር ፍትህ ልዩ ችሎትን ማቋቋምና ሌሎችም የማሻሻያና አዳዲስ አሰራሮች በፍ/ቤቶች ይከወናሉም ነው ያሉት።

ይህን ለማሳካትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትጋት እና በስነ-ምግባር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በሰለሞን ከበደ
👍235
የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ይከበራል - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
*************

የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡

የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሃሳብ ለ17ኛ ጊዜ በመላው ሀገሪቱ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

በፌደራል፣ በክልሎችና በሁለቱም የከተማ አስተዳደር ከተሞች ከሰንደቅ ዓላማ መርሆዎች ጋር ተገናዝቦ በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪነት በመላው ሀገሪቱ እንደሚከበርም ምክር ቤቱ ጠቅሷል፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02UCyojVq27aobhzBoLg1DNu2AgLo2fnR2a5vqEzv7ZEfrmtHu2v4gtsHuSZZMzGCfl
👍225
"ኢትዮጵያን ማበልፀግ የትውልዶች ሁሉ ህልም ወይም ምኞት ሆኖ የቆዬ ነበር።
ብልፅግና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት እና በማፅናት የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚቻል መንገዱን በተግባር እያሳዬ ያለ ፓርቲ ነው።"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
👍347👎3
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ
*******************

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አዲስ ለተሰየሙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመልእክታቸው፤ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕረዚዳንት ሆነው በመመረጦ እንኳን ደስ አልዎት ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል።

የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመልካም ወዳጅነት እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በአዲሱ ፕሬዝዳንት መሪነት የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር እንደሚጎለብት እና ቀጣናዊ መረጋጋትም እንደሚጠናከር ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መመኘታቸውንም በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል፡፡
59👍32👏8👎3
በኢትዮጵያ ከ8 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረዋል፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
***************

በ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8 ሺህ 854 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረዋል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ።

5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር "የቁልፍ መሰረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሃሳብ በሳይንስ ሙዚዬም እየተከበረ ይገኛል።

የተቋማትና የግለሰቦች በሳይበር ጥቃት ላይ ያላቸው የግንዛቤ ውስንነት ለጥቃቱ በመንስኤነት ከሚጠቀሱት ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ በመድረኩ ገልፀዋል።https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0XHyaBf6hJmPuwS6JotsqXjL5k5xKPyyW7xCVa8hfLN8awRXd8HZ1AYJ8v9bFcLC9l
👍13
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
***************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ሎርድ ኮሊንስን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን አስመልከቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ዛሬ የእንግሊዙን የአፍሪካ ሚኒስትር የሀይበሪውን ሎርድ ኮሊንስን አግኝቼ በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
👍407👎3