EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
140K subscribers
33.4K photos
376 videos
80 files
12.8K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ
************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለዐቅመ ደካሞች ዓመታዊውን የማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር በቤተ መንግሥት አከናውነዋል።
በቤተ መንግሥት የተከናወነው ዓመታዊ የማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር በምስል፡-
ፍቅር እስከ መቃብር!

ዛሬ ቀን 8 ሰዓት በኢቢሲ ብቻ

“ፍቅር እስከ መቃብር” ተከታታይ ፊልም በአዲሱ ዓመት በኢቢሲ ለተመልካች መቅረብ ጀምሯል።

በኢቢሲ ዜና ቻናል ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት እና በመዝናኛ ቻናል ደግሞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ ይተላለፋል። እንዲሁም በድጋሚ ምሽት ከዜና በኋላ በሁለቱም ቻናሎች ይተላለፋል።

የኢቢሲ ዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ በማድረግ ሙሉ ተከታታይ ፊልሙን መመልከት ይችላሉ።
https://youtu.be/ct3xlFWEgcI?si=I1-MxA5t05X1RRDB
https://www.youtube.com/watch?v=Ivfgc8Y-sG8
በረራ የሚከለከልበት፣ የዞዲያክ ምልክት የሚሰጥበት እስከ ሰባቱ ምሳሌዎች የአዲስ ዓመት አከባበር
******************

የዘመን መለወጫ በዓል በበርካታ ሀገሮች የሚከበርባቸው ባህሎች የተለያዩ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሀገር የራሱ የሆነ ባህል እና ሕዝባዊ መስተጋብር አለው፡፡ በዚህም መሰረት ነው ሀገራት አዲስ ዓመታቸውን የሚያከብሩት፡፡

አዲስ ዓመት አብዛኛውን ጊዜ የአካባቢውን ባህል እና እምነት በሚያንጸባርቅ መልኩ ይከበራል። አዲስ ዓመት በተለያዩ ሀገራት ባህል የተለየዩ አከባበሮች ቢኖሩትም ሁሉንም አንድ የሚያደርገው ግን አሮጌ ዘመን አልፎ አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ እንደሚቀበሉ ማመናቸው ነው፡፡

የጎርጎሮሳውያንን ዘመን ቀመር ከሚከተሉ ሀገራት የተለየ የአዲስ ዓመት አከባበር ካላቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች፡፡ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቀመር የፀሐይ እና የጨረቃ ዑደቶችን በመጠቀም የሚሠራ ነው፡፡ የወቅቶች ለውጥን ተከትሎ የሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በጨለማ የሚመሰለው ክረምት መውጫ ላይ መከበሩ ልዩ ያደርገዋል፡፡

ሙሉ ፅሁፉን ለማግኘት ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=7773
21ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተመረቀ
*********

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አካባቢ የተገነባው 21ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ሥራ ጀመሯል፡፡

ከንቲባዋ ማዕከሉን በመረቁበት ወቅት፤ የምገባ ማዕከሉ እርስ በእርስ የመረዳዳት እና የመተጋገዝ ማሳያ ነው ብለዋል።

አረጋውያን፣ አቅመ ደካማና የተቸገሩ ዜጎችን ማስታወስ ይገባል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ 21ኛው የተስፋ ብርሃን የምግባ ማዕከል ለገነቡት በረከት ወርቁ ምስጋና አቅርበዋል።

ማዕከሉን ያስገነቡት ባለሀብቷ በረከት ወርቁ በበኩላቸው፤ በአስተዳዳሩም እንደ ሀገርም የሚሰሩ የሰው ተኮር ስራዎችን ለማገዝ ወደ ማዕከል ግንባታ መግባታቸውን ገልፀዋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02ouQjqsfc1KQBDkDFAQCm1i9vnsxXxbuN4Bg8AotErqg9GQMDF4U9HikyLmEFszsbl