በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ በተደረገው አዲሱ መዋቅራዊ አደረጃጀት ትግበራ ዙሪያ የማጠቃለያ ስልጠና ተሰጠ።
መጋቢት 22/2018ዓ.ም ሰ/ት/ቤቶች አንድነት
በሀገረ ስብከታችን ከቀን 18 እስከ 20/07/2018ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት አምና ተግባራዊ በሆነው በአዲሱ የሰ/ት/ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ዙሪያ ለአጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ሥራ አመራር ጉባኤ አባላት በዓለም አቀፍ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ዶ/ር ስንታየው ምስጋናው የሙከራ ትግበራ ጊዜ የማጠቃለያ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናውም የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ አባ ዕዝራ እና የሰ/ት/ቤቶች አንድነት የስራ አመራር አባላት በተገኙበት ከደረጃ 2 - 4 ያሉ ሰ/ት/ቤቶች በተለያየ የስልጠና መርሐ ግብር የተሳተፉ ሲሆን በመወቅራዊ አደረጃጀቱ የሙከራ ትግበራ ወቅት ለታዩ ክፍተቶችና ጥያቄዎች ለጉባኤው ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ይህን የስልጠና መርሐ ግብር ለማከናወን በሀገረ ስብከታችን ለተገኙ ለዓለም ዓቀፉ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ የሀገረ ስብከታችን ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ሀብታሙ ሽፈራው ምስጋና በማቅረብ ስልጠናውን የም/ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ መ/ሐዲስ አባ ዕዝራ በፀሎት ዘግተዋል።
መረጃው የአንድነቱ መ/መዛግብት ክፍል ነው።
( የድሬደዋ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት)
👉
https://www.facebook.com/profile.php?id=61557918219413
👉
https://t.me/DireAndinet
👉https://www.tiktok.com/@andinet.media?_t=ZM-8uNUxtCJBO2&_r=1

👍1