Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት
1.03K subscribers
118 photos
61 videos
48 files
247 links
አጠቃላይ የአጫጭር ማስታወሻ በቪዲዮ የተዘጋጀ ለብዙ ትምህርታዊ ነክ የሆኑትን ማዘጋጀት ጀምረናል።

• 1-12ኛ ክፍል
• ጥያቄ እና መልስ መስራት

ዩቱብ ላይ ተከታተሉ:

https://youtube.com/@Mstv_Kinemaster_Show
https://youtube.com/@DigitalLibraryofEducations

• ዩኒቨርሲቲ የተጠቃለለ ኮርሶች እና መፅሐፎች
• ዩኒቨርሲቲ ጥያቄ እና መልስ መስራት።
Download Telegram
#University
#Placement

የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ 👇
ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም
 
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ የሚያደርጉበት ሊንክ 👇
https://student.ethernet.edu.et/
 
የሕክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከስድስት ወር በታች ህጻን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «#University #Placement የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!   በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡   የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ…»
ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገቡና ለፈተና ለተመረጡ ተማሪዎች ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፈተና መስጠቱ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ለፈተና ተመርጣችሁ በተለያየ ምክንያት ፈተና ያልተፈተናችሁ ተማሪዎች፣ ሰኞ ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፈተና መስጫ ማዕከል በመገኘት መፈተን የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በድጋሜ መፈተን የማይቻል መሆኑ ተገልጿል።
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 የትምህርት ዘመን በፌዴራል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገቡና ለፈተና ለተመረጡ ተማሪዎች ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ፈተና መስጠቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ለፈተና ተመርጣችሁ በተለያየ ምክንያት ፈተና ያልተፈተናችሁ ተማሪዎች፣ ሰኞ ጳጉሜን 02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፈተና መስጫ ማዕከል በመገኘት መፈተን የምትችሉ መሆኑን ትምህርት…»
ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2019ኛው የዘመን መለወጫ አዲስ አመት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

Happy New Year!!
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2019ኛው የዘመን መለወጫ አዲስ አመት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። Happy New Year!!»
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር፣ የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ጊዜ መራዘሙን አሳውቋል።

በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ወስደው በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ማጠናቀቂያ ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫቸውን እስካሁን ያላስገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ መስከረም 5 ቀን ማጠናቀቅ ይችላሉ ተብሏል።

ተማሪዎች ምርጫቸውን ለማስገባት
student.ethernet.edu.et የተሰኘውን ድረ-ገጽ በመጠቀም የራሳቸውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በማስገባት ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ መልዕክት ተላልፏል።
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «#MoE ትምህርት ሚኒስቴር፣ የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ጊዜ መራዘሙን አሳውቋል። በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ወስደው በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ማጠናቀቂያ ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች…»
#Remedial

የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%)

2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%)

በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ

1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%)

4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «#Remedial የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል…»
#MoE
#Placement

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አድርጓል።

የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ይመልከቱ 👇
https://student.ethernet.edu.et/view-placement

በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ጀምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንድታቀርቡ ተብሏል።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇
https://student.ethernet.edu.et/complaints

በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመሔድ የሚቀርብ የምደባ ቅሬታን የማያስተናገድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቅሬታ በምታስገቡበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «#MoE #Placement ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አድርጓል። የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ይመልከቱ 👇 https://student.ethernet.edu.et/view-placement በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ጀምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ…»
#Remedial
 
ትምህርት ሚኒስቴር፣ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ።
 
ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫቸውን እስከ መስከረም 11/2019 ዓ.ም ድረስ እንዲያደርጉ ነው ያሳወቀው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇
https://student.ethernet.edu.et/preferences
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «#Remedial   ትምህርት ሚኒስቴር፣ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ።   ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫቸውን እስከ መስከረም 11/2019 ዓ.ም ድረስ እንዲያደርጉ ነው ያሳወቀው። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇 https://student.ethernet.edu.et/preferences»
#Remedial

ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉
https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡
https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
👉
https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ
https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «#Remedial ምደባ ይፋ ሆነ።   በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።   በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ…»
#Placement

"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡

ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡

ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም።

ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል።

የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር ሊፈፀም የሚችል ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል፡፡
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «#Placement "ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ…»
ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ-መስቀሉ (ደመራ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
Digital Library of Educations | ትምህርታዊ ዲጂታል መፅሀፍት pinned «ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ-መስቀሉ (ደመራ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።»