Debtera Media
4.76K subscribers
10.1K photos
544 videos
88 files
738 links
ደብተራ ሚዲያ የእውነት ድምጽ!
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!👇

በዩቲዩብ 👉 https://bit.ly/3bMfT8D

በፌስቡክ 👉 fb.me/DebteraMedia

በቴሌግራም 👉 t.me/DebteraMedia

ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ሆነ መረጃ በ t.me/DebteraMedia_Bot ማድረስ ትችላላችሁ።
Download Telegram
🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ከጌትነቱም ክብር ፈጽሞ አልተለየም ]

🕊                    💖                       🕊

❝ አምላክ ሲሆን ሰው ሆነ ፤ ከጌትነቱም ክብር ፈጽሞ አልተለየም። ምንም ሰው ቢሆን እርሱ ከፍጡራን ሁሉ በላይ ነው።

በመለኮቱ ሕግን የሠራ ሲሆን እነሆ ሕግን በመፈጸም ተገኘ ፤ ሕግን ሲሰጥ በነበረበት ባሕርዩ ጸንቶ ኖረ። [ ገላ.፬፥፬ ]

በመለኮቱ ገዢ ሊሆን የተገዥ ባሕርይን ገንዘብ አደረገ። ግን የጌትነት ክብር ከእርሱ አልተለየም። አንድ ሲሆን ለብዙዎች ምእመናን በኵር ሆነ። [ በትንሣኤ ፤ በዕርገት ] ። በአንድነቱም ጸንቶ ኖረ። [ ሮሜ.፰፥፱ ። ፊልጵ.፪፥፭፰ ]

ሰው እንደ መሆኑ በሥጋ ቢሞት የሚያስደንቅ አይደለም። እነሆ በመለኮቱ የማይሞት ነው። ሐዋርያው ጳውሎስም በዚህ አንድ ጌትነት አብን በመምሰል ያለ ቃል እርሱ ለሞት እስከ መድረስ ደርሶ መከራውን እንደ ታገሠ ሞቱም በመስቀል እንደሆነ ተናገረ። [ ፊልጵ.፪፥፰-፱]

ዳግመኛም በሌላ መልእክቱ ከፍጡራን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ፤ እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው ፤ በባሕርይ የሚተካከለው እንደሆነ ተናገረ ፤ በሰማይም በምድርም ያለውን የሚታየውን ፥ የማይታየውን ሁሉ በርሱ ቃልነት ፈጥሮአልና ። ❞

[    🕊   ቅዱስ ቄርሎስ   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                     🕊                      💖
🔔

[ የፊደል እርማት ! ]

" ሊሆን " የሚለው " ሲሆን " በሚል ይታረም !

በመለኮቱ ገዢ ሊሆን የተገዥ ባሕርይን ገንዘብ አደረገ። የሚለው

በመለኮቱ ገዢ ሲሆን የተገዥ ባሕርይን ገንዘብ አደረገ። በሚል ይታረም።

🔔
                       †                           

†    🕊  መንፈሳዊው መሰላል  🕊   †


[ ወጣንያንን ስለሚገጥማቸው ሕልሞች በተመለከተ ]

            [   ክፍል  ሠላሳ አንድ  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ የሁለቱም የነፍስ ምኞትንና የሰውነት ብልቶችን መግደል ጅማሬው የበዛ ከባድ ሥራ ነው፡፡ መካከለኛው አንዳንዴ አድካሚ አንዳንዴም የማያደክም ነው፡፡ ፍጻሜው ግን ለድካምና ለመከራ አለመሰቀቅና አለመታወክ ነው፡፡ ይህ ሕያው ሆኖ የሚኖር የተባረከ ሬሳ ራሱን የገዛ ፈቃዱን ብቻ ሲያደርግ ሲመለከተው ኀዘን የሚሰማውና በልቡም የሚታመም ይሆናል፤ በገዛ ውሳኔ የመመራት ኃላፊነትንም ይፈራል፡፡

ለዚህ መንፈሳዊ ኑዛዜ [ ሙያ ] የውድድር [ ሩጫ ] መድረክ ብለህ መራቆትን የወሰንክ አንተ ፣ የክርስቶስን ቀንበር በአንገትህ ለመሸከም የምትመኝ አንተ ፣ በዚህም የገዛ ሸክምህን በሌሎች ትከሻ ላይ ለማኖር የምትሞክር አንተ ፣ በፈቃድህ ራስህን ለባርነት ለማስገዛት የቃል ኪዳን ውል ለመፈረም የምትፋጠን አንተ ፣ በምላሹም ከዕዳ ነጻ መሆንህን የሚገልጸውን ጽሑፍ የምትሻ ፣ ይህን ታላቅ ባሕር በዋና የምታቋርጥ እንደ መሆንህ መጠን በሌሎች እጆች የምትታገዝ አንተ ይኸውም በራስ ፈቃድ መመራት ተብሎ በሚጠራ አጭር ሆኖ ሳለ ነገር ግን አስቸጋሪ በሆነ አንድ አሳሳች መንገድ ብቻ ለመጓዝ እንደ ወሰንህ እወቅ፡፡

ዳሩ ግን መልካምና መንፈሳዊ እንዲሁም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ መስለው በሚታዩ ነገሮች ውስጥ እንኳ ይህን (በራስ መመራትን) ጨርሶ የተወ ፣ ጉዞውን ከመጀመሩ በፊት ወደ ፍጻሜው ደርሶአል፡፡ መታዘዝ አንድ ሰው መልካም ቢሆን እንኳ ፣ እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ድረስ በነገር ሁሉ በራስ አለመታመን ነውና፡፡ ❞

[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]


🕊                      💖                     🕊
💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷  " ሕ ዋ ሳ ት ን መ ቆ ጣ ጠ ር  "

💖 አቡነ አትናቴዎስ ዘእስክንድር 💖  ] 

[                        🕊                        ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ ፤ ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ❞ [ ሮሜ . ፮ ፥ ፲፪  ]


❝ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና ፥ ያውም እናንተ ናችሁ።❞ [ ፩ቆሮ.፫፥፲፯ ]



🕊                       💖                   🕊
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊

        [   የአርያም ንግሥት  !     ]       


† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል [ ደብረ ምጥማቅ ] በሰላም አደረሳችሁ †

🕊  †   ደብረ ምጥማቅ  †   🕊

የአርያም ንግሥት : የሰማይና የምድር እመቤት : የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት ፳፩ [ 21 ] ቀን በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::

🕊


[ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለዐምስት ቀናት ያኽል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያኽል ደስ ታሰኚ ኖሯል ! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው ]

[ አባ ጽጌ ድንግል ]

†                       †                         †
💖                    🕊                     
🕊

[ † እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል [ደብረ ምጥማቅ] በሰላም አደረሳችሁ † ]

🕊  †   ደብረ ምጥማቅ  †   🕊

የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::

ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ ፦

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር::

ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት ፳ [21] ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::

በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ፭ [5] ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት :- እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል::

እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::

የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር::

እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: ፭ [5] ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች::


🕊   †  አባ መርትያኖስ   †   🕊

አባ መርትያኖስ በበርሃ ከ ፷፰ [68] ዓመታት በላይ በቅድስና የኖሩ አባት ናቸው:: ሰይጣን እርሳቸውን ፊት ለፊት ተዋግቶ መጣል ቢያቅተው በዝሙት በተለከፉ ሴቶች ያስቸግራቸው ነበር::

አንድ ቀን አንዷ ሽቶ አርከፍክፋ በዝሙት ልትጥላቸው ብትል እግራቸውን እሳት ውስጥ ጨምረው እግራቸው እየተቃጠለ በሚወጣው ጠረን አጋንንትን አርቀዋል:: እሷንም በንስሃ መልሰው ለቅድስና አብቅተዋታል:: ጻድቁ ከፈተና ለመራቅ በ ፻፰ [108] ሃገራት ፻፰ [108] በዓቶች የነበሯቸው ብቸኛ አባት ናቸው::

† ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: †

🕊

[ † ግንቦት ፳፩ [ 21 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅድስት ደብረ ምጥማቅ [የእመቤታችን መገለጥ]
፪. አባ መርትያኖስ ጻድቅ [በዝሙት ላለመሰናከል እግራቸውን በእሳት ያቃጠሉ አባት]
፫. ቅዱስ አሮን ሶርያዊ
፬. ቅዱስ አሞጽ ነቢይ

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. አበው ጎርጎርዮሳት
፪. አቡነ ምዕመነ ድንግል
፫. አቡነ አምደ ሥላሴ

" የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: " [መዝ.፵፬፥፲፪-፲፯] (44:12-17)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖