ዳማከሴ - Damakese
13 subscribers
6 photos
21 links
" እንኳን ደህና መጣችሁ "
ይህ የ ዳማከሴ Medical Tube የ ቴሌግራም ቻናል ነው !
Download Telegram
🌻 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ !
🌻 እንቋዕ አብፀሓኩም - ርዑስ በዓል !
🌻 Baga Bara Haraatiin isiin
gahee !
🌻 Happy Ethiopian new year !

የ Youtube ቻናላችንን Subscribe , Share , Like እና Comment ያድርጉ ያተርፉበታል !
https://www.youtube.com/@DamakeseMedicalTube-sj6wm
Channel photo updated
✍️ #የጨጓራ #ባክቴሪያ

#የጨጓራ ባክቴሪያ ወይም ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ(Helicobacter pylori (H. pylori)) ወደ ሰውነታችን በመግባት የምግብ ትቦ ላይ እና  ጨጓራ ውስጥ መኖር የሚችል ነው፡፡ ይህ ባክቴሪያ ሳይታከም ከቆየ አልሰር/  ቁስለት በጨጓራ ላይ እና በትንሹ አንጀት የላይኛው ክፍል ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ አለፈፍ ሲልም ካንሰርንም ሊያስከትል ይችላል፡፡

🔹 በጨጓራ ባክቴሪያ መያዝ በብዙዎች ላይ የሚያጋጥም የተለመደ በሽታ ቢሆንም ባክቴሪያው አንዳንድ ሰዎች ላይ ምንም ምልክት የማያሳይ፣ የቁስለት ሁኔታም የማይፈጥር ቢሆንም ብዙዎችን ግን ለከፍተኛ ለሕመም ይዳርጋል፡፡

#ባክቴሪው #እንዴት #ህመም #ይፈጥራል?

🔹 የጨጓራ ባክቴሪያ ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ በጨጓራ ውስጣዊ አካል ላይ ጥቃት በመፈፀም ጨጓራችንን ተጋላጭ ያደርገዋል፤ ምክንያቱም ጨጓራችን ምግብ ለመፍጨት አሲድ ይጠቀማል፡፡ ይህ አሲድ በጨጓራ አካል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚያደርገው የጨጓራ  ውስጣዊ አካል ነው፡፡ ይህ አካል ከተሸረሸረ ጨጓራችን ለአሲዱ የተጋለጠ ስለሚሆን ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ጉዳቱ የደም መፍሰስ ጨምሮ አካሉ እንዲቆስል፣ እንዲሁም የበላነው ምግብ እንዳይፈጭና እንዳይረጋ ሊያደርግ ይችላል፡፡

#ይህ #ባክቴሪያ #ከየት #ሊያገኘን #ይችላል?

🔹 የጨጓራ ባክቴሪያ ከምንበላው ምግብ፣ ከምንጠጣው ውኃና ከምንጠቀማቸው በባክቴሪው ከተበከሉ ቁሶች ሊያገኘን ይችላል፡፡ በሽታው አብዛኛውን ጊዜ ፅዳት በሚጎድልባቸው አካባቢዎች የሚከሰት ሲሆን ባክቴሪያው በምራቅ ንክኪና ባክቴሪያው ካለበት ሰው ጋር በሚኖር የፈሳሽ ንክኪ ሊተላለፍብን ይችላል፡፡

#የጨጓራ #ባክቴሪያ #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው?

🔹 የሆድ መነፋት፤
🔹 ግሳት፤
🔹 የረሃብ ስሜት አለመሰማት፤
🔹 ማቅለሽለሽ፤
🔹 ማስመለስ፤
🔹 ቁስለት ከተፈጠረብን በሆዳችን የላይኛው ክፍል የማቃጠልና የመደንዘዝ ስሜት፤
🔹 ያለምክንያት ክብደት መቀነስ ሊታዩ ይችላሉ፡፡

#መቼ #ወደ #ህክምና #መሄድ #ይኖርብናል?

🔹 የሰገራ መጥቆርና ደም መቀላቀል ካለ፣
🔹 ለመተንፈስ መቸገር ካጋጠመን፣
🔹 ያለስራ የመልፈስፈስና የድካም ስሜት ከተጫነን፣
🔹 የቆዳ መገርጣትና ራስን የመሳት ሁኔታ ከታየብን፣
🔹 የተፈጨ ቡና የመሰለ ነገር የሚያስመልሰን ከሆነ፣
🔹 ከባድ የሆድ ህመም ካለን የጨጓራ ባክቴሪያ ሊሆን ስለሚችል መታየት አለብን፡፡

#ምርመራ

🔹 የኋላ ታሪክን በመጠየቅ
🔹 የትንፋሽ ምርመራ
🔹 የኢንዶስኮፒ ምርመራ

#ሕክምና

🔹 ጸረ - በክቴሪያ መድኃኒቶች፧
🔹 በጨጓራ ውስጥ አሲድ የሚረጩትን ጥቃቅን ቧንቧዎች በመዝጋት አሲድ የሚቀንሱ መድኃኒቶችን
🔹 የአመጋገብ ስርአት ማስተካከለል ይካተቱበታል፡፡
© Doctor Alle
👍1
የጡት ህመም | Breast Pain

🔬🦠የጡት ህመም የሚያስከትሉ 09 ምክንያቶች

1. ሆርሞኖች
       
የወር አበባ ከመጀመሩ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት ቀደም ብሎ ህመም ይሰማዎታል፧ ከጀመሩ በኋላ  ያቆማል።
       
ይህ የሆነበት ምክንያት የወር አበባዎ ከመጀመሩ በፊት የኢስትሮጅንና ፕሮጄስትሮን መጨመር ነው።
        
ነፍሰ ጡር ከሆናችሁ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ የሆርሞን ምርት እየጨመረ በመምጣቱ ጡቶዎን ይታመማሉ።
          
ህመሙን ለመቀነስ መውሰድ ያለቦት እርምጃዎች፦
             - ካፌይን ያስወግዱ
             - የጨው መጠን ይቀንሱ
             - ስጋራ ማጨስን መተው
             - የህመም ማስታገሻ ይውሰዱ
             - የወሊድ መከላከያ ክኒኖችን ወይም
                የሆርሞን ምትክ ሕክምናን መቀየር
                ሊረዳህ እንደሚችል ሐኪሞን ይጠየቁ።

2. የጡት ጉዳት
        
ይህ በአደጋ ምክንያት, ስፖርት በሚጫወቱበት ጊዜ ወይም በጡት ቀዶ ጥገና ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
         
ህመሙ ካልተሻሻለ ወይም ከእነዚህ ምልክቶች አንዱን ካዩ ሐኪምዎን ይምክሩ፦
         - ከባድ እብጠት
         - በጡት ውስጥ እብጠት ካለ
         - መቅላት እና ሙቀት
         - የማይጠፋ ቁስል ካለ

3. በማይደገፍ ብራ ምክንያት
        
ተገቢው ድጋፍ ከሌለ ጡቶችን ከደረት ግድግዳ ጋር የሚያገናኙት ጅማቶች ከመጠን በላይ ይወጠሩ እና ህመም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ሰለዚ ብራዎ ትክክለኛ ሳይዝ መሆኑን ያረጋግጡ።

4. የጡት ህመም ከደረት ግድግዳዎ የመጣ ሊሆን ይችላል

5. ጡት ማጥባት
          
ጡት ማጥባት አንዳንድ ጊዜ የጡት ህመም ምንጭ ሊሆን ይችላል።
       
- በመነካከስ ወይም በደረቁ፣ በተሰነጠቀ ቆዳ ወይም በበሽታ ምክንያት የጡት ጫፍ ህመም ይፈጠራል 
       
- ተገቢ ባልሆነ መልኩ ጡት ማስያዝ በጡት ማጥባት ግዜ የጡት ህመም የሚያስከትሉ ናቸው።

6. የጡት ኢንፌክሽን
       
ጡት የሚያጠቡ ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ በጡት ኢንፌክሽን ይያዛሉ። የጡት ኢንፌክሽን ካለብዎ ትኩሳት ሊኖርብዎት ይችላል። በተጨማሪም የጡት   መቅላት ፤ እብጠትና ህመም ይኖራል። የጡት ኢንፌክሽን ካለቦት  ዶክተር ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው።

7. የጡት ህመም የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳት ሊሆን ይችላል።

8. የጡት እጢ/ሲይስት ሲይስትን ለመመርመር ሐኪምዎ ማሞግራም/ አልትራሳውንድ ሊያዝሎዎ ይችላል።

9. የጡት ህመም አንዳንድ ጊዜ የጡት ካንሰር ምልክት ሊሆን ይችላል።
         
በጡት ላይ ያለው ቆዳም ሊወፍር ወይም ወደ ውስጥ ሰርጎድ ሊል ይችላል። ስለ የጡት ካንሰር ካሳሰበዎት ወዲያውኑ ዶክተርዎን ያነጋግሩ።

ዶ/ር አንዱአለም ዘገዬ : Obstetrician and Gynecologist
© Hakim
Breast pain Breast Pain

🔬🦠 09 causes of breast pain

1. Hormones

Do you feel pain three to five days before your period? It stops after starting.

This is due to the increase in estrogen and progesterone before your period.

If you are pregnant, your breasts will be sore during the first trimester due to increased hormone production.

Steps to take to reduce the pain:
- Avoid caffeine
- Reduce the amount of salt
- Quitting smoking
- Take pain reliever
- Birth control pills or
Changing hormone replacement therapy
Ask your doctor if he can help you.

2. Breast injury

This can happen as a result of an accident, while playing sports, or as a result of breast surgery.

Consult your doctor if the pain does not improve or if you notice any of these symptoms:
- Severe swelling
- If there is swelling in the breast
- Redness and heat
- If there is a permanent wound

3. Due to unsupported bra

Without proper support, the ligaments that connect the breasts to the chest wall can become overstretched and cause pain. So make sure your brows are the right size.

4. Breast pain may be coming from your chest wall

5. Breastfeeding

Breastfeeding can sometimes be the source of breast pain.

- Nipple pain occurs due to irritation or dry, cracked skin or infection

- Improper breastfeeding causes breast pain during breastfeeding.

6. Breast infection

Breastfeeding women are more likely to get breast infections. If you have a breast infection, you may have a fever. Also, breast redness; There will be swelling and pain. It is very important to consult a doctor if you have a breast infection.

7. Breast pain can be a side effect of medication.

8. Breast Lump/Cyst Your doctor may order a mammogram/ultrasound to check for cysts.

9. Breast pain can sometimes be a symptom of breast cancer.

The skin on the breast may also thicken or become wrinkled. If you are concerned about breast cancer, contact your doctor immediately.

Dr. Andualem Zegye : Obstetrician and Gynecologist
© Hakim
ከ ' ዳማከሴ Medical Tube ' የቀረበ ግብዣ
   📌 [ የ SUBSCRIBER ቻሌንጅ ]
  📌  [ 5000 ብር የገንዘብ ሽልማት ]
        💵💵💵💵💵💵💵💵💵

🗣 በቅድሚያ እርስዎ ቻናሉን Subscribe አድርገው የ ደውል 🛎  ምልክቱን ይጫናሉ ፤ ሌሎች ከ 5 በላይ ሰዎችን Subscribe ያስደርጉ ፤ በመቀጠል የእርስዎን ጨምሮ Screen Shot በዚህ  { @damakese21} የ Telegram አድራሻችን ይላኩልን ።

📌 " ዳማከሴ Medical Tube " ስለ ጤና ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሆኖ ግንዛቤ የሚሰጥ ቻናል ነው ፤ ቻናሉ ወደፊት ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል በገንዘብ እጥረት ( እጦት ) ህክምና ሳያገኙ የሚቀመጡ ወገኖችን ህክምና እንዲያገኙ ፣ እንዲታገዙና ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያግዝ ( የሚያስተባብር )ሆኖ በዋነኝነት ይሰራል ።

💉 በቅንነት Subscribe ስላደረጉንና ቤተሰባችን ስለሆኑ እናመሰግናለን ።

የ YOUTUBE ቻናላችን 👇
https://www.youtube.com/@Damakese

የ Telegram ቻናላችን 👇
https://t.me/DamakeseTube

የ Tik Tok አድራሻችን 👇
https://www.tiktok.com/@damakesemedicaltube4?_t=8g8splNEQiM&_r=1

የ Instagram አድራሻችን 👇
https://instagram.com/damakesemedicaltube?igshid=YTQwZjQ0NmI0OA==
An invitation from 'Damakese Medical Tube'
📌 [ SUBSCRIBER CHALLENGE ]
📌 [5000 Birr cash prize]
💵💵💵💵💵💵💵💵💵

🗣 First of all, you subscribe to the channel and press the bell icon 🛎; Subscribe more than 5 people; Next, send us a Screen Shot including yours on this { @damakese21 } Telegram address.

📌 "Damaske Medical Tube" is a channel that provides awareness about health with health professionals; One of the future activities of the channel is to help (coordinate) people who are left without treatment due to lack of money to get treatment, help and receive proper care.

💉 Thank you for sincerely subscribing and being our family.

Our YOUTUBE channel 👇
https://www.youtube.com/@Damakese

Our Telegram channel 👇
https://t.me/DamakeseTube

Our Tik Tok address 👇
https://www.tiktok.com/@damakesemedicaltube4?_t=8g8splNEQiM&_r=1

Our Instagram address 👇
https://instagram.com/damakesemedicaltube?igshid=YTQwZjQ0NmI0OA==
📍የማድያት ምንነት!


🖌ለመሆኑ ማድያት ምንድነው?

ማድያት (melasma) ማለት በፀሐይ የጠየመ ወይም የጠቆረ የቆዳ ቀለም ቅየራ ማለት ነው። ማድያት ለፀሐይ በተጋለጡ የሰውነት ክፍሎች ላይ በብዛት ፊት ላይ ይከሰታል። በዋናነትም ሴቶችን በተለይ ጥቁር/ጠይም የቆዳ ቀለም ያላቸውንና ለፀሐይ ጨረር(UV radiation) የተጋለጡትን ያጠቃል።

#መንስኤዎቹ ፦

በብዛት መንስኤው አይታወቅም

--  እርግዝና
–  በአፍ የሚዋጡ የእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶች
– ለፀሐይ መጋለጥ
– በቤተሰብ ማድያት ካለ
– የመዋቢያ ቅባቶች
– የሚጥል በሽታ መድኃኒቶች
– የእንቅርት በሽታ
– የኩላሊት ዕጢ በሽታ(addisons disease)

🖌ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?

ጠቆር ያለ፡ ቅርፅ አልባና ከጤነኛው ቆዳ በደንብ መለየት የሚችል ከትንሽ እስከ ትልቅ መጠን ያለው የቆዳ መዝጎርጎር። በዋናነት ሦሥት አይነት የማድያት ስርጭት አለ

1. Centrofacial፦ ጉንጭን፣ ግንባርን፣ የላይኛውን ከንፈር፣ አፍንጫና አገጭን ያጠቃለለ ሲሆን
2. Malar፦ ጉንጭንና አፍንጫን ሲያጠቃልል
3. Mandibular፦ የታችኛውን ግንጭል ያጠቃለለ ከሆነ

🖌ለማድያት ምን ምርመራ ይታዘዛል?

– አካላዊ ምርመራ
– የጨረር ምርመራ(wood’s lamp)

ህክምናው ምንድን ነው?

ማድያትን ለመታከም ወደህክምና ተቋማት ሲሄዱ ሊደረግሎ ከሚችሉ ነገሮች መካከል በጥቂቱ:-

 ማድያት በረጅም ጊዜ የሚመጣና በዘላቂነት የመቆየት ባህሪ ስላለው በቶሎ ለማከም አስቸጋሪ ነው። በዋናነት ግን ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የሚቀቡ መድኃኒቶችን እና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ(ከተገኘ ለዚህ ተብለው የተሰሩ፣ አለበለዚያ ማንኛውንም ጨርቅ እና ባርኔጣ/ኮፍያ መጠቀም ይቻላል) መጠቀም አስፈላጊ ነው።
ምናልባት ግን ማድያቱ በእርግዝና የመጣ ከሆነ ልጅ ከተወለደ እስከ አንድ አመት ባለው ጊዜ ሊጠፋ ይችላል።

የሚያነጡ መድኃኒቶች ሊሰጥዎ ይችላል(hydroquinone, azelaic acid, tretinoin…)

ቆዳን የሚልጡ ኬሚካሎች(chemical peels)፦ ይኸ በቆዳ ስፔሻሊስት ሐኪም ምክር ብቻ የሚከናወን ነው

 የጨረር ህክምና(laser theraphy)

 የፊት ሜካፕ(cosmotic camouflage) በመጠቀም ማድያቱ እንዳይታይ ማድረግም ይቻላል::


ውድ ተከታታዮቻችን ይህ አስተማሪ ትምህርት ብዙ ሰዎች ጋር ተደራሽ እንዲሆን በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከታተሉን !
  እ  .  ና  . መ  . ሰ  .ግ  . ና  . ለ  . ን

የ Youtube ቻናላችን
👉 https://www.youtube.com/@DamakeseMedicalTube-sj6wm

የ Instagram አካውንታችን
👉https://instagram.com/damakesemedicaltube?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg%3D%3D

የ Tik Tok አካውንታችን
👉 http://tiktok.com/@damakesetube

የ Telegram ቻናላችን
👉 https://t.me/DamakeseTube

የ Twitter አካውንታችን
👉 https://twitter.com/jossyjo13256874?t=fxhZbxDPfUQWOrkqaqpwSQ&s=35

የ Threads አካውንታችን
👉 https://www.threads.net/@damakesemedicaltube

Pinterest
👉 https://pin.it/3gi3s8U
መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል

#ረቡኒ_Tube
#ዳማከሴ_Medical_tube
#ሆሴዕ_ቤተውበት
Channel photo updated
Channel name was changed to «ዳማከሴ - Damakese»