Dagmawi Babi
4.47K subscribers
12.3K photos
1.51K videos
225 files
1.58K links
Believer of Christ | Creative Developer.

Files Channel: https://t.me/+OZ9Ul_rSBAQ0MjNk

Community: @DagmawiBabiChat
Download Telegram
የብርሃን አምላክ ቃልን በብርሃን ነው የጀመረው፤ "ብርሃን ይሁን" (ዘፍ 1፥3) ብሎ። ይህ ቃል የእግዚአብሔር የሥራው መጀመሪያ ነው። በብርሃናት የተከበበው አምላክ ያንኑ ብርሃን ለፍጥረት አካፈለ፤ ብርሃኑን በመፍጠር ሰጠ። "የብርሃናት አባት" ስለሆነ፣ ለሥራው ብርሃን አያስፈልገውም። ፍጥረቱ ግን በብርሃን አቅም ይኖራል። "ቅርጽ የለሽና ባዶ" የነበረችውም ምድር ብርሃን ሲበራባት መልክ መያዝ ጀመረች፣ እየሞላችና እየተዋበች መጣች። 'ብርሃን ፈጣን ተጓዥ ነው' ይባላል፤ ቃሉ ግን ይቀድመዋል፣ ከቃሉ የተነሣ ብርሃን ሆኗልና። ቃሉን ተከትሎ የመጣው ብርሃንም ጨለማውን አሸነፈ። ዛሬም ቃሉን የሚሰሙ ልባቸውን በብርሃኑ ይሞላሉ። ብሩህ ልቦና ደግሞ ብሩህ ቀንን ያስከትላል።

Genesis 1:3
"And God said, 'Let there be light,' and there was light."

@Devotion #DailyInjera #Scripture
@Dagmawi_Babi
የእግዚአብሔር ሕግ (ቃል) ብርሃን ስለሆነ ይታያል፤ ያሳያልም። እውነት ሆን ተብሎና ባለማወቅ በተሰወረበት ዓለም ቃሉን የያዙ መንገዳቸውን በብርሃን ይገፋሉ፤ ይወጣሉም። ዘማሪው፣ "ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው" (119፥105) አለ። የጻድቅ መንገድ በእግዚአብሔር ብርሃን የተሞላ ነው፤ ጻድቃን ለጌታ ሕግ ከበሬታ ይሰጣሉና። ቃሉን የሚያነቡና የሚያጠኑ ብርሃናቸውን የያዙ፣ በዙሪያ ያለውን ጨለማም የረቱ ናቸው። የጻድቃን መንገድም በቃሉ ብርሃን ግልጽ የሆነ ብቻ ሳይሆን የደመቀም ነው።

Psalms 119:105
"Your word is a lamp for my feet, a light on my path."

#DailyInjera #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
"አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ ይላል አምላካችሁ።" (ትንቢተ ኢሳይያስ 40:1) እግዚአብሔር ሕዝቡን ተናግሮ ብቻ የሚተው አምላክ አይደለም፤ የሚያጽናናም አምላክ ነው። ተናግሮ ለትካዜ የሚዳርግ አምላክ አይደለም፤ ስለዚህ ለሕዝቡ መጽናናት እንዲሆን "አጽናኑ" አለ። መጽናናትም ሐዘንን መርሳት መጀመር፣ ከሐዘን እየወጡ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሸጋገር፣ ከትናንት ትዝታ በላይ በነገ ተስፋ መኖር ነው። አምላክ ያለው ሕዝብ እየተደፋ የሚሄድ ሳይሆን፣ እየተጽናና የሚያጽናና፣ እየበረታም የሚያበረታ ነው።

Isaiah 40:1
"Comfort, comfort my people,
says your God."

#Scripture #Devotion #DailyInjera
@Dagmawi_Babi
ጳውሎስ በሁለተኛው የቆሮንቶስ መልእክቱ የተለመደውን "ጸጋ...ከእናንተ ጋር ይሁን" የሚለውን ሰላምታ ካቀረበ በኋላ፣ "የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ" (1፥3) ይላል። ርኀራኄ አባት አለው፤ መጽናናትም አምላክ አለው፤ ያም እግዚአብሔር ነው። እርሱ ሙሉና የማይለዋወጥ ስለሆነ ሁልጊዜ የሚራራ፣ የሚያጽናናም ነው። ሰዎች ያጽናናሉ፣ ሁልጊዜ ግን አጠገብ ሊሆኑ አይችሉም፤ የራሳቸው ኑሮና ሸክም አለባቸውና። ዛሬ የሚያጽናኑም ነገ መጽናናት የሚፈልጉ ናቸው። ጌታችን ግን ሳይነካ—በስሜት ሳይጎዳ—የሚነካ ነው። የጸጋ አምላክ ለልጆቹ ማጽናናቱን ያበዛል፤ ሳይለይም ያበረታል። አዛኝ አጽናኝ እንጂ 'ተሰባሪ' አጽናኝ የለንም!

1 Corinthians 1:3
"Grace and peace to you from God our Father and the Lord Jesus Christ."

#DailyInjera #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
የታምራት ብዛት ወደ እግዚአብሔር አያቀርብም፤ አድናቂ ግን ሊያደርግ ይችላል። እስራኤል በታላቅ ክንድ (ተአምር) ከግብጽ ቢወጣም፣ ከመጀመሪያው የተጓዠ ቡድን ተስፋውን የወረሱት ሁለት ብቻ ነበሩ። ብዙዎቹ ወይም ሁሉም ማለት ይቻላል አምላክን አስቆጡ። በቀጥታ በርሱ ምሪት፣ በርሱ መንገድና በርሱ እረኝነት ሥር ሆነው እርሱኑ አስከፉ። አሳፍ እንደ ዘመረው፣ ግሩም መረዳት ውስጥ ገብተው ነበር፤ "እግዚአብሔር ዐለታቸው፣ ልዑል አምላክ ቤዛቸው እንደ ሆነ ዐሰቡ" (78፥25)። ይሁንና ግን በዝማሬያቸው አልጸኑም። መልሰው የራሳቸውን ዜማ አቀነቀኑ፤ በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረሙ። ጌታ አምላክ ግን የማይታማ ዐለት፣ የማያሳፍርም ቤዛ ነው። ምስጋናው በምስጋና፣ በውዳሴም ይደረባል እንጂ ስሞታ የሚቀርብበት አይደለም።

Psalms 78-35
"They remembered that God was their Rock, that God Most High was their Redeemer."

#DailyInjera #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
መከራ የብቻነት ጕዞ አይደለም። እግዚአብሔር የሁልጊዜ አጋር፣ የሙሉ ጊዜ ወዳጅና የማይለይ ከለላ ነው። ለዚህ ነው ዘማሪው በመከራው መካከል አምላኩ ያልጠፋበት፤ "በመከራ መካከል ብሄድም፣ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ" (መዝ 138፥7)። እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ ተገን፣ ከለላም ነው። ሕዝቡን እየጠበቀ፣ የሕዝቡን ጠላቶች ይመታል። "በቀኝ" እጁ እያዳነ 'በግራው' ጠላትን ያርቃል። ችግርና መከራ እግዚአብሔርን ከእኛ ካልለየ፣ እኛን ከእግዚአብሔር ሊለይ አይችልም።

Psalms 138:7
"Though I walk in the midst of trouble, you preserve my life. You stretch out your hand against the anger of my foes; with your right hand you save me."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
የእግዚአብሔርን ቃል ያገኙና ያስቀሩ፣ የሚጠብቁም ጥበብን የሰወሩ ናቸው። የጥበብ ጥሪ ቃሉን የማስተዋል፣ በጥንቃቄ የማድመጥ፣ የማቅረብና የመጠበቅ ነው። እግዚአብሔር የገለጠውና መመሪያ እንዲሆን የሰጠው ቃል ሁሉ ጥበብን የተሞላ ቃል ነው። በጥበብ መጽሐፍ (ምሳሌ) እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ "ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ። ከእይታህ አታርቀው፤ በልብህም ጠብቀው፤ ለሚያገኘው ሕይወት፣ ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና" (4፥20-22)። ቃሉን የሁልጊዜ ተግባር የሚያደርጉ ሕይወትን ያገኙ፣ የዚያኑ ሕይወት ትሩፋትም የሚያጣጥሙ ናቸው። ነፍስን የሚያረካው የጥበብ ቃልም ለሰውነት ፈውስና ብርታት ይሆናል።

Proverbs 4:20-22
"My son, pay attention to what I say; turn your ear to my words. Do not let them out of your sight, keep them within your heart; for they are life to those who find them and health to one’s whole body."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
የእግዚአብሔርን ቃል የሚያሰላስሉ በቃሉ እውነትና ብርሃን አምላካቸውን ያወቁ ናቸው። እነርሱም ያወቁትን አምላክ ለማነጋገር (ወደ እርሱ ለመጸለይ) የበራላቸው ብቻ ሳይሆን ድፍረትን ያገኙ ናቸው። ዘማሪው "ቃልህን አሰላስል ዘንድ፣ ዐይኔ ሌሊቱን ሙሉ ሳይከደን ያድራል" ካለ በኋላ፣ "እንደ ቸርነትህ መጠን ድምፄን ስማ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ሕግህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ" አለ (119፥148-149)። እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ቃሉ ነው። ራሱን ገልጦ የሚሸሸግ ወይም በዘመን ብዛት ኅይሉ ደክሞ መስማትም ሆነ መታደግ የማይችል አምላክ አይደለም። በቃሉ (መንገድ) የሚመጡትን በተስፋው ይገናኛቸዋል።

Psalms 119:149
"Hear my voice in accordance with your love; preserve my life, Lord, according to your laws."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
በጭንቅና በውጥረት ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ ውጭ ምን የተሻለ መፍትሄ ይኖራል? መጽሐፍ—በተለይ ደግሞ መዝሙር—የጭንቅ ጊዜ ጸሎቶችን እስከ ዘማሪዎቹ አስቸጋሪ የነፍስ  ሁኔታ አስቀምጦልናል። መዝሙር 142ም አንዱ ነው፤ "እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ 'አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ' እላለሁ" (ቍ. 5)። ይህ 'አስተማሪ የጽሞና መዝሙር' ተስፋን ከመከራ በላይ የሚያጎላ፣ ሰቆቃን ከመታመን ሥር የሚያደርግ፣ እግዚአብሔርንም ከጥያቄ በላይ የሚያገን ነው። ወደ እግዚአብሔር የሚጮኹ ሊታመኑበት፣ መጠጊያቸውና ዕድል ፈንታቸው እንደ ሆነም ለራሳቸው ሊያውጁ ይገባቸዋል። የርሱ የሆኑትን የትኛውም ችግርና መከራ ብቻቸውን አያገኛቸውም። የምናሰማው ጩኸት እንግዲህ፣ ከሩቅ ሳይሆን ከውስጥ የምንጮኸው ነው፤ በመጠጊያው ሆነው የሚጮኹ ቅርብ ናቸውና።

Psalms 142:5
"I cry to you, Lord ; I say, 'You are my refuge, my portion in the land of the living." '

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሕግ በድንጋይ ላይ ጽፎ በሙሴ አማካኝነት ለሕዝቡ ሰጠ። የዚያም ሕግ ፅንሰ ሐሳብ—አስፈላጊነት—ዛሬም ድረስ ይሠራል። ሕጉን የሚያነቡና ሊፈጽሙ የሚወድዱ ግን ልባቸው የድንጋይ እንጂ የሥጋ አልነበረም። በአዲሱ ኪዳን ግን ሕያው የሆነው አምላክ ሕጉን በክርስቶስ ባመኑት ልብ ላይ በመንፈስ ጻፈው። ከሕያው አምላክ ሕይወትን የተካፈሉ ሁሉ፣ ከቃሉ ከመንፈስ የሆነውን ሕግ በመንፈስ ተቀብለው ሕያው ምስክር ይሆናሉ፤ "እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ" (2ቆሮ 3፥3)። "በመንፈስ ላይ የተመሠረው የአዲሱ ኪዳን" ተካፋዮችም ሕያው በሆነው ቃሉ እየተሠሩና እርሱን እየመሰሉ የአምላካቸውን ማንነት በሕይወታቸው እንደ ደብዳቤ—መልእክት—ይገልጣሉ። እነርሱም በተማሩት—ምሕረት ባገኙትና ትምህርት በወሰዱት—በቀላሉ ይነበባሉ።

2 Corinthians 3:3
"You show that you are a letter from Christ, the result of our ministry, written not with ink but with the Spirit of the living God, not on tablets of stone but on tablets of human hearts."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi