Dagmawi Babi
3.97K subscribers
11.8K photos
1.42K videos
215 files
1.47K links
Believer of Christ | Creative Developer.

Files Channel: https://t.me/+OZ9Ul_rSBAQ0MjNk

Community: @DagmawiBabiChat
Download Telegram
መከራ የብቻነት ጕዞ አይደለም። እግዚአብሔር የሁልጊዜ አጋር፣ የሙሉ ጊዜ ወዳጅና የማይለይ ከለላ ነው። ለዚህ ነው ዘማሪው በመከራው መካከል አምላኩ ያልጠፋበት፤ "በመከራ መካከል ብሄድም፣ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ" (መዝ 138፥7)። እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ ተገን፣ ከለላም ነው። ሕዝቡን እየጠበቀ፣ የሕዝቡን ጠላቶች ይመታል። "በቀኝ" እጁ እያዳነ 'በግራው' ጠላትን ያርቃል። ችግርና መከራ እግዚአብሔርን ከእኛ ካልለየ፣ እኛን ከእግዚአብሔር ሊለይ አይችልም።

Psalms 138:7
"Though I walk in the midst of trouble, you preserve my life. You stretch out your hand against the anger of my foes; with your right hand you save me."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
የእግዚአብሔርን ቃል ያገኙና ያስቀሩ፣ የሚጠብቁም ጥበብን የሰወሩ ናቸው። የጥበብ ጥሪ ቃሉን የማስተዋል፣ በጥንቃቄ የማድመጥ፣ የማቅረብና የመጠበቅ ነው። እግዚአብሔር የገለጠውና መመሪያ እንዲሆን የሰጠው ቃል ሁሉ ጥበብን የተሞላ ቃል ነው። በጥበብ መጽሐፍ (ምሳሌ) እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ "ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ። ከእይታህ አታርቀው፤ በልብህም ጠብቀው፤ ለሚያገኘው ሕይወት፣ ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና" (4፥20-22)። ቃሉን የሁልጊዜ ተግባር የሚያደርጉ ሕይወትን ያገኙ፣ የዚያኑ ሕይወት ትሩፋትም የሚያጣጥሙ ናቸው። ነፍስን የሚያረካው የጥበብ ቃልም ለሰውነት ፈውስና ብርታት ይሆናል።

Proverbs 4:20-22
"My son, pay attention to what I say; turn your ear to my words. Do not let them out of your sight, keep them within your heart; for they are life to those who find them and health to one’s whole body."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
የእግዚአብሔርን ቃል የሚያሰላስሉ በቃሉ እውነትና ብርሃን አምላካቸውን ያወቁ ናቸው። እነርሱም ያወቁትን አምላክ ለማነጋገር (ወደ እርሱ ለመጸለይ) የበራላቸው ብቻ ሳይሆን ድፍረትን ያገኙ ናቸው። ዘማሪው "ቃልህን አሰላስል ዘንድ፣ ዐይኔ ሌሊቱን ሙሉ ሳይከደን ያድራል" ካለ በኋላ፣ "እንደ ቸርነትህ መጠን ድምፄን ስማ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ሕግህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ" አለ (119፥148-149)። እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ቃሉ ነው። ራሱን ገልጦ የሚሸሸግ ወይም በዘመን ብዛት ኅይሉ ደክሞ መስማትም ሆነ መታደግ የማይችል አምላክ አይደለም። በቃሉ (መንገድ) የሚመጡትን በተስፋው ይገናኛቸዋል።

Psalms 119:149
"Hear my voice in accordance with your love; preserve my life, Lord, according to your laws."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
በጭንቅና በውጥረት ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ከመቅረብ ውጭ ምን የተሻለ መፍትሄ ይኖራል? መጽሐፍ—በተለይ ደግሞ መዝሙር—የጭንቅ ጊዜ ጸሎቶችን እስከ ዘማሪዎቹ አስቸጋሪ የነፍስ  ሁኔታ አስቀምጦልናል። መዝሙር 142ም አንዱ ነው፤ "እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ 'አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ' እላለሁ" (ቍ. 5)። ይህ 'አስተማሪ የጽሞና መዝሙር' ተስፋን ከመከራ በላይ የሚያጎላ፣ ሰቆቃን ከመታመን ሥር የሚያደርግ፣ እግዚአብሔርንም ከጥያቄ በላይ የሚያገን ነው። ወደ እግዚአብሔር የሚጮኹ ሊታመኑበት፣ መጠጊያቸውና ዕድል ፈንታቸው እንደ ሆነም ለራሳቸው ሊያውጁ ይገባቸዋል። የርሱ የሆኑትን የትኛውም ችግርና መከራ ብቻቸውን አያገኛቸውም። የምናሰማው ጩኸት እንግዲህ፣ ከሩቅ ሳይሆን ከውስጥ የምንጮኸው ነው፤ በመጠጊያው ሆነው የሚጮኹ ቅርብ ናቸውና።

Psalms 142:5
"I cry to you, Lord ; I say, 'You are my refuge, my portion in the land of the living." '

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi
እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ሕግ በድንጋይ ላይ ጽፎ በሙሴ አማካኝነት ለሕዝቡ ሰጠ። የዚያም ሕግ ፅንሰ ሐሳብ—አስፈላጊነት—ዛሬም ድረስ ይሠራል። ሕጉን የሚያነቡና ሊፈጽሙ የሚወድዱ ግን ልባቸው የድንጋይ እንጂ የሥጋ አልነበረም። በአዲሱ ኪዳን ግን ሕያው የሆነው አምላክ ሕጉን በክርስቶስ ባመኑት ልብ ላይ በመንፈስ ጻፈው። ከሕያው አምላክ ሕይወትን የተካፈሉ ሁሉ፣ ከቃሉ ከመንፈስ የሆነውን ሕግ በመንፈስ ተቀብለው ሕያው ምስክር ይሆናሉ፤ "እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ" (2ቆሮ 3፥3)። "በመንፈስ ላይ የተመሠረው የአዲሱ ኪዳን" ተካፋዮችም ሕያው በሆነው ቃሉ እየተሠሩና እርሱን እየመሰሉ የአምላካቸውን ማንነት በሕይወታቸው እንደ ደብዳቤ—መልእክት—ይገልጣሉ። እነርሱም በተማሩት—ምሕረት ባገኙትና ትምህርት በወሰዱት—በቀላሉ ይነበባሉ።

2 Corinthians 3:3
"You show that you are a letter from Christ, the result of our ministry, written not with ink but with the Spirit of the living God, not on tablets of stone but on tablets of human hearts."

#DailyInjera #EthioBiblica
#Spiritual #Scripture #Devotion
@Dagmawi_Babi