Dagmawi Babi
4.6K subscribers
12.5K photos
1.54K videos
227 files
1.61K links
Believer of Christ | Creative Developer.

Files Channel: https://t.me/+OZ9Ul_rSBAQ0MjNk

Community: @DagmawiBabiChat
Download Telegram
Good night

"እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡"
-- መዝ 26፡10

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Good night

“ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ? በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ። ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ? በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ? የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?"
— ኢዮብ 38:4-6

“አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ።”
— ኢዮብ 42፥2

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Good night

ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
¹⁴-¹⁵ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Good night

“ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነውን ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናድርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው?”
— 1 ዜና 29፥14

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥1

#Scripture #Spiritual #Lessons
@Dagmawi_Babi
Happy New Years Everyone 🥰

“አትሸበሩ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር ዛሬ የሚያደርግላችሁን መታደግ ታያላችሁ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ዳግም አታዩአቸውም። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተ ያለባችሁ መታገሥ ብቻ ነው።"
-- ዘጸአት 14:13-14

#Scripture #HNY #Holidays #2017
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Good night and happy new year! 🎊

"እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።የምትሉትን ቃል ይዛችሁ፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እንዲህም በሉት፤ “ኀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን፤ የከንፈራችንንም ፍሬ እንድናቀርብ፣ በምሕረትህ ተቀበለን። አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”

እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤ እንዲሁ እወዳቸዋለሁ፤ ቊጣዬ ከእነርሱ ተመልሶአልና። እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ ውብ አበባ ያብባል፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም፣ ሥር ይሰዳል፤ ቅርንጫፉ ያድጋል፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባ ይሆናል። ሰዎች እንደ ገና ከጥላው በታች ያርፋሉ፤ እርሱም እንደ እህል ይለመልማል፤ እንደ ወይን ተክል ያብባል፤ ዝናውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይወጣል።

ኤፍሬም ሆይ፤ ከእንግዲህ ከጣዖት ጋር ምን ጒዳይ አለኝ? የምሰማህና የምጠነቀቅልህ እኔ ነኝ፤ እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ ነኝ፤ ፍሬያማነትህም ከእኔ የተነሣ ነው።

ጥበበኛ የሆነ እነዚህን ነገሮች ያስተውላል፤ አስተዋይም እነዚህን ነገሮች ይረዳል። የእግዚአብሔር መንገድ ቅን ነውና፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ዐመፀኞች ግን ይሰናከሉበታል።"

-- ሆሴዕ 14:1-9

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Good night

“ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤ በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤ እንደ አደይም ያብባል።”
— ኢሳይያስ 35፥1

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Good night

“እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ይመራሃል፤ ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ ዐጥንትህን ያበረታል፤ በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣ እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ።”
— ኢሳይያስ 58፥11

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Good night

“በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?””
— ኢያሱ 1፥9

#Scripture
@Dagmawi_Babi
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM