Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ
4.24K subscribers
1.3K photos
33 videos
1.43K links
Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ
Subscribe YouTube Channel
https://bit.ly/368pQrX
Join on Telegram
https://t.me/DJEthiopian
Visit Our Website
https://ethiopiandj.com/am/
Like & Follow us on FACEBOOK
https://www.facebook.com/Ethiopian.DJ/
የእናንተው ድምፅ | ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማሳሰቢያ!

የኦሮሙማው መንግስት ሃይሎች በተቀናጀ መልኩ ለአንድ ወር ማለትም እስከ ሰኔ 12 የሚቆይ ፋኖን የማፅዳት ዘመቻ የሚል እቅድ አውጥቷል።

ለዚህም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመሩ 5 ቀናት አልፏቸዋል። በዚህ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ውስጥ

=> የመከላከያ ሠራዊት በበላይነት የሚመራው
=> የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት መረጃ ወደ መከላከያ መረጃ ቋት እንዲሆን እና ሌሎች የመረጃ ተቋማትም በመከላከያ መረጃ ስር ተጠርንፈው እንዲመሩ አድርገዋል።

=> ሚሊሻ፣ ፖሊስ እና በየ አካባቢ የተደራጀ አዲስ ካድሬ አካባቢወችን በመለየት ጦሩን አቅጣጫ እንዲጠቁሙ ስምሪት ወስደዋል። በየቤተሰቡ ፋኖ ያለበትን የመለየት ስራ የሚሠሩ ናቸው።
=> የትግራይ ሃይሎች በመከላከያ ዩኒፎርም በተመረጡ በተለይም ፋኖ ጠንካራ እንቅስቃሴ በሚያደርግባቸው የጎጃም፣ የሸዋ፣ የወሎ እና የጎንደር ከፈተኛ እና በርሃማ ቦታወች ላይ ስምሪት ወስደው ጅምላ የብቀላ ጭፍጨፋ እንዲፈፅሙ ሥምሪት ወስደዋል።

=> የፌደራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሌሎች ክልሎች የፖሊስ ሃይል የተወጣጣ ሃይል እንዲያዘጋጅ አድርገዋል ይሄም ቤት ለቤት የትጥቅ ነጠቃ፣ አሰሳ ጨምሮ ወጣቱን ወደ ማጎሪያ የመሠብሰብ ተግባር የሚፈፅሙ ይሆናሉ።


=> የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ፣ አድማ ብተና እና ጋቸና ሲርና (የስርዓቱ ዘብ)የተባሉት ከየቀበሌው የተወጣጡ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።


=>የአማራ ክልል የፖለቲካ አመራሩ በየ ትውልድ ቦታው በየደረጃው ያለው ስምሪት ተሠጦት በመከላከያ ስር ሆኖ እንዲጠረነፍ ታዟል።


ይሄ ሁሉ ዘመቻም በተለይም የአማራ ህዝብ ላይ ያለውን የፖለቲካ ጥያቄ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመጨፍለቅ ፣ አንገት ለማስደፋና ከተቻለም ዘር ማጥፋት ለመፈፀም በድርብርብ ጠላት ሃይሎች ቅንጅት ጭምር የታቀደ ነው።
******************************************************************
በመሆኑም የወገን ሃይል አጠቃላይ የጠላትን እንቅስቃሴ በመለየት በተለመደው የደፈጣ፣ የቆረጣ እና አመቺ ሁኔታወች ላይ ደግሞ የከበባ ውጊያወች በማድረግ የገባውን ሃይል አስምጦ የማስቀረት እንቅስቃሴወች የሚጠናከሩ ይሆናል።
=> ህዝቡ፣ ወጣቱ ይሄ እየተዝረከረከ የሚመጣውን በየቦታው እየማረከ፣ እየቆረጠ እና ሌሎች መንገዶችን በመጠቀም ትጥቁን እንዲረከብ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
=> በፋኖ አደረጃጀት ውስጥ እንደራደራለን የሚሉ አስቀድመው ፍላጎታቸውን የገለፁ ጥቂት ቡድኖች የጠላት (የመንግስት) ኦፕሬሽን እንዲሳካ እና ትግሉን የሚያስቀጥሉትን ጠንካራ አመራሮች እንዲደመሰሱ የማድረግ ተግባር ሊያከናውኑ ስለሚችሉ የፋኖ አደረጃጀቶች የውስጥ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

=> በክልሉ ያሉ የተለያዩ የፋኖ አደረጃጀቶች ያለቸውን ጥቃቅን የውስጥ ልዩነት ትተው በጋራ የተቀናጀ መግለጫ በመስጠት ህዝቡም በአንድነት መንፈስ እንዲከላከል፣ ትግሉም ይሄን ወቅት ተሻግሮ ትግሉ ፍሬ እንዲያፈራ ማድረግ ግዴታ የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

=> በብልፅግና ፍላጎት መሠረት በዚህ የዘመቻ ሃደት ውስጥ የፋኖ አመራሮች እንደሚገደሉ እና ሃይሉም እንደሚበተን በማሰብ የእቅድ ግብ ስላስቀመጠ በቀጣይም ለፖለቲካ ፍጆታ የሚሆን አስቀድሞ ካዘጋጃቸው ጋር ድርድር ለማድርግ እና ድርድር አናደርግም ብሎ የሚቀረውን በአሸባሪነት ለመፈረጅ ተዘጋጅተዋል።
ሁሉም የወገን ሃይል ይህን መረጃ ያዛምት የፋኖ አደረጃጀቶች ለሚያቀርቡት የአስተዋፅኦ ጥያቄ ሁሉም የአቅሙን የምድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ በፍጥነት ይነቀሰቀስ፡፡
ድል ለአማራ ህዝብ!!!!!
Look what happen in our country Ethiopia 💔
~ የሚገባህ ከሆነ የጎንዮሽ ልፊያህን ትተህ እንዲህ ለሚታረደው ወገናችን እዘንለት እያልኩህ ነው።

አራጁን ትተህ ከወንድምህ ጋር አትተናነቅ!

አንድ ሁን!
#Update

የአማራ ፋኖ በጎጃም በሰከላ ዙሪያ አምቢሲ አካባቢ በ3ኛ እና 5ኛ ክፍለ ጦር ስር ያሉ ብርጌዶች ባደረጉት የተቀናጀ ዘመቻ "ሰምበቶ እንዳጣፎ" የተባለ የ73ኛ ክፍለ ጦር አመራርን (ሻምበል አዛዥ) ጨምሮ በርካታ የሻለቃ እና የሻምበል አመራሮችን ከነ መገናኛ ሬዲዮናቸው ማርኳል!

ይቀጥላል...

ዝርዝር መረጃው በምሽቱ የቃል አቀባዮች መረጃ ይቀርባል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጎንደር አፈና በቃን ባሉ ነዋሪዎች ላይ ስርአቱ ተኩስ በመክፈት የ5 ሰዎችን ህይዎት ቀጠፈ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአማራ ፋኖ እዝ በጎንደር መግለጫ ሰጠ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጷግሜ ፀበልተኞች😂
የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ የስርአቱ አገልጋይ ወታደሮችን ማረከ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምርኮኞቹን መቀለብ አልቻልንም። ቀይ መስቀል እና አለም አቀፍ ተቋማት ሊረዱን ይደገባል።

ይደመጥ
ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ለዕዛችን እና ለመላው የአማራ ፋኖ አባላት፣ለዞናችን እና ለመላው የአማራ ህዝብ እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን "እንኳን ከ2016 ወደ 2017 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ማለት ይወዳል።

አዲሱ ዓመት የሰላም ፣የአንድነት ፣የነፃነት የእኩልነት የፍቅር ዘመን እንዲሆን እየተመኘን በዓሉን ስናከብር በፍፁም አማራዊ ለጋስነት ፣ኢትዮጵያዊ መተሳሰብ የተቸገሩትን በመርዳት፣የታመሙትን በመጠየቅ ፣አቅመ ደካሞችን በማገዝ እንድናሳልፍ እዛችን ጥብቅ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

አዲስ አመት :-ያንን ሁሉ ድቅድቅ ጨለማ የክረምት ጊዜ አሳልፈን በአደይ አበባ ፍካት ቀዬው ሁሉ ድምቅ ብሎ አዳዳዲስ ተስፋዎችና እቅዶች የሚሰነቁበት ወቅት ነው።የአማራ ህዝብም ከተጫነበት ዓብይ መራሽ የባርነት ቀንበር ተላቆ በአብራኩ ልጆች ብርቱ ክንድ የባርነት ቀንበሩ ሊንኮታኮት ዋዜማው ላይ ደርሷል ለዚህም የአማራ ፋኖ በደማቅ ብዕር የሚፃፍ አይረሴ አሻራውን አስቀምጧል።

በእርግጥ እንቅፋት ሲመታ ወደፊት እንደሚያንደረድር ሁሉ የአማራ ህዝብም የደረሰበት ሞትና ስደት፣ግፍና መከራ፣ሰቆቃና ሲቃይ፣ርሀብና ጥም አንድ ሆኖ እንዲደራጅና በተናጥል ከመታረድም አልፎ ለማንም የማታዳላ ኢትዮጵያን ለመገንባት ከጥንት አባቶቹ ከነ እምዬ ምኒሊክ የመሪነት ጥበብን በመውረስ ታላቋን ሀገር "ኢትዮጵያን"ለመረከብ ጥቂት ጊዜያት ብቻ ቀርተውታል።

የተከበርከው የአማራ ህዝብና የዕዛችን ደጋፊዎች ሆይ ትናንት ስንደራጅ ጀምሮ ሲርበን እያጎረስክ ፣ሲጠማን እያጠጣህ፣ስናጠፋ እየገሰጥክ፣ስንደሰት ተደስተህ ስንከፋ ተክዘህ እዚህ አድርሰኸናል ።እኛም የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አመራሮችና አባላት የህዝብ ልጆች እንደመሆናችን መጠን ለወጣንለት አላማ ፀንተን የአማራ ህዝብ ነፃነት በነጋሪት እስኪታወጅ ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ልንከፍል ቃል እንገባልሀለን።በአዲሱ ዓመት አዲስ አሰራር፣አዲስ የምስራች ይዘንም ብቅ እንላለን።

መልካም አዲስ ዓመት!
ክብር ለተሰው ፋኖዎች
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም
update
ሰበር ዜና ዳባት ተቆርጧል!
አሁን ከቀኑ 7:40 ዳባት ከተማ ከፍተኛ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው ፣ውጊያው ጧት 11:00 ደባርቅ የጀመረው ከፍተኛ ውጊያ እስከሰሁኑ የቀጠለ ሲሆን ዳባትን በመቁረጥ የፋኖ ሃይል እየተዋጋ ይገኛል።

ደባርቅ ፣ወቅን ያለው የጠላት ሃይል ማፈግፈጊያ መሸሸጊያ በማሳጣት በሙሉ ሀይል የጎንደር ፋኖ እየተዋጋ ሲሆን በሚገርም ሁኔታ ሰሜናዊ ጎንደር ቀጠና ከጠላት ነፃ የሚሆንበት ሰአታት እየተቃረበ ነው።

ደባርቅ ወቅን የተከማቸ የጠላት ሃይል እጅ ከመስጠት ወይም መሞት ብቻ ነው ምርጫው።ዳባት ተቆረጠ!!
መስከረም 6-2017 ዓ.ም
Forwarded from ማያ ሚዲያ (ነፂ)
በመንግስታዊ አገልግሎት ሽፋን የጠላትን ተልዕኮ ማስፈጸም አይቻልም::
_______
መስከረም 06/2017 ዓ/ም
___
ጠላት በመደበኛ ሁኔታ የሚያደርገውን ወታደራዊ ስምሪት ውጤታማ ለማድረግ የተጠቀማቸው የመረጃ እና የስለላ ስራዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከሽፈዋል::

ይሁን እንጅ የሁሉም እቅዶቹ መነሻ ሕዝብን ማታለል የሆነው የብልጽግና ቡድን ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በተለያዩ የማኅበራዊ አገልግሎት ተቋማት በዘመናዊ የስለላ እና የመረጃ መሳሪያዎች የሚጠቀሙ የእናት ጡት ነካሽ የሆኑ ባንዳዎችን አሰልጥኖ ለስምሪት ማዘጋጀቱን ደርሰንበታል::

በግብርና መረጃ ሰብሳቢነት እና በሌሎችም መንግስታዊ አገልግሎቶች ስም ስምሪት ወስደው የሚንቀሳቀሱ የጠላት የመረጃ ሰወች ላይ ለምንወስደው እርምጃ ሕዝቡ እውቅና እንዲኖረው እና ጥቆማ በመስጠትም ትብብር እንዲያደርግ እናሳስባለን::

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ![ ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!]
የዘመቻ 100ተራሮች ጅማሮዎች
6ኛ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር
ስናን አባጅሜ ብርጌድ
ደንበጫ ኢንጂነር ክበር ተመስገን ብርጌድ
በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር በሁለቱ ወረዳዎች የተሰሩ ጀብዶች
፩ ስናን ረቡዕ ገብያ
1: ስናን ረቡዕ ገቢያ የመሸገን የጁላ ሰራዊት ከ80%በላይ መደምሰስ ተችሏል።
2: ከስናን ባንዳዎችን አንቆ ማውጣት ተችሏል።
4: ከ 10 በላይ መሳሪያና ተተኳሽ መማረክ ተችሏል።
፪ ደንበጫ
1: ሙሉ በሙሉ ከተማውን መቆጣጠር ተችሏል ።
2: ከከተማ ባንዳዎችን አንቆ መያዝ ተችሏል።
3: ዋና መሪ የሚባሉ ሚኒሻዎችን ከነ አጃቢዎቻቸው መሸኘት ተችሏል።
-ልጃም መንገሻ--- የሚኒሻ ፅ/ቤት ሃላፊ መሃል አስፖልት ላይ ተሸኝቷል
-መኮነን ይበይን - ዋና የአገዛዙ አሽከር ሚኒሻ
አዛገ ምትኩ - ታማኝ የብልፅግና ሚኒሻ ወደሲኦል ተሸኝተዋል።
4: ከ40 በላይ መሳሪያ እና ብዙ የመትረየስ ተተኳሽ መማረክ ተችሏል።
ዘመቻውን አጠናክረን እንቀጥላለን።
አዲስ ትውልድ ፣
አዲስ አስተሳሰብ ፣
አዲስ ተስፋ።
#ዘመቻ 100 ተራሮች
እስቲበል አለሙ ዘሪሁን
ሰበር ዜና
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ መሽጎ በሚገኘው የአገዛዙ ወታደር ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፀመ።

የምንጃር ሸንኮራ ወረዳን ህዝብ በማሰቃየት አማራን የማጥፋት ዘመቻውን እየፈፀመ የሚገኘው የብልፅግናው ወንበዴ ቡድን የአብይ አህመድ ሰራዊት በክንደ ነበልባሎቹ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌድ በተፈፀመበት መብረቃዊ የተጠና ጥቃት በርካቶች የአብይ አህመድ ሰራዊት እስከወዲያኛው ሲሸኙ ለቁጥር የሚያስቸግሩት ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል እየተጣጣሩ ሞጆ ወደሚገኘው ሆስፒታል ተግዘዋል።

አምባገነኑ የብርሀኑ ጁላ ጦር ከምንጃር ሸንኮራ መዲና አረርቲ ከተማ ቅርብ እርቀት ላይ ወደምትገኘው የሸንኮራ ከተማ በማቅናት ንፁሀንን ሲያሰቃይ፣የግለሰቦችን ሀብትና ንብረት ሲዘርፍ ሲያዩት እልህ እና ቁጭት የተሰማቸው የነበልባል ብርጌድ የፋኖ አባላት መስከረም 25/2017 ዓ.ም በምሽት አረርቲ ከተማ ስር በተለምዶ እንዶድ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ስፍራ የጠላትን ምሽግ ደምስሶ በመግባት በፈፀመው መብረቃዊ ጥቃት ጠላት የያዘውን ምሽግ በመልቀቅ ወደ አረርቲ ከተማ ቢፈረጥጥም የአማራ ህዝብ አለኝታዎች የምንጃር ሸንኮራ እንቁዎች የነበልባል ብርጌድ አናብስቶች አረርቲ ከተማ ድረስ በመግባት ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል።

ያለምንም መስዋዕትነት ጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰው በከሰም ክፍለጦር ስር የሚገኘው የነበልባል ብርጌድ ፋኖዎች አምባገነኑ የአብይ አህመድ ጉጅሌ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የጀመረውን የጥፋት ሴራ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ለመፈፀም ቢፍጨረጨርም በአይበገሬዎቹ ፋኖ ቁርጠኛ አቋም ጠላት ያሰበው ሳይሳካ በየጫካው እየወደቀ ይገኛል ብለዋል።

ንፁሀንን ማሰቃየት የምንጊዜም ተግባሩ የሆነው በአረጋ ከበደ መልካም ፈቃድ የአማራን ህዝብ የሚያሰቃየው የጁላ ወታደር የፋኖን በትር መቋቋም ሲያቅተው ንፁሀንን መደብደብ ፣የግለሰቦችን ሀብት መዝረፉን ቢቀጥልበትም በዚህ አፀያፊ ተግባሩ ወደ ኋላ የሚጓዝ አንድም የአማራ ትግል እንደማይኖር ቆራጦቹ የነበልባል ብርጌድ ከፍተኛ አመራሮች በልበሙሉነት ገልፀዋል።


ድል ለአማራ ፋኖ
ክብር ለተሰው ፋኖዎች

መስከረም 26/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ ከስም ክፍለ ጦር ነበልባል ብርጌድ ከመሸ የምንጃር ሸንኮራ ንዑስ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን #ባልጪ ከተማን ከጠላት እጅ ነፃ አውጥቶ ሙሉ ለሙሉ ፋኖ ተቆጣጥሯል::

ምንጃር አረርቲ ከተማም የትላንትናው ውጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነው::

የአማራ ፋኖ በሸዋ እዝ ህዝብ ግንኙነቶች
*የድል ዜና

በሸዋ ምድር ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ መሽጎ የሚገኘው የአብይ አህመድ ፀረ አማራ ቡድን በጀግናው የነበልባል ብርጌድ የፋኖ አባላት በአራት አቅጣጫ እየተገረፈ ይገኛል።

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የነበልባል ብርጌድ መስከረም 27/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአራት አቅጣጫ ማለትም በጨሌ መስመር፣አዳማና ድሬ ፣ሸንኮራ እና ቦሎ አካባቢ አሰፍስፎ የመጣን የብርሀኑ ጁላ ፍዝ ምንጋ ሠራዊት እየገረፉ በርካቶች ተገድለው ፣በርካቶች ቆስለው እድለኛ የሆኑት ደግሞ የያዙትን መሳሪያ በየጫካው እየጣሉ ፈርጥጠዋል።

ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከምሽቱ 2:30 ድረስ በቆየው የ12 ሰዓታት እልህ አስጨራሽ ውጊያ ጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የነበልባል ብርጌድ ፋኖዎች ዙ-23 እና ዲሽቃ እስካፍንጫው የታጠቀ የአብይ አህመድን ግሪሳ ቡድን እየገረፉ ታላቋን የባልጪ ከተማን ተቆጣጥረው ያደሩ ሲሆን ፀረ አማራው የአብይ አህመድ ቡድን በየቤተክርስቲያኑ ተበታትኖ ነፍሴ አውጪኝ እያለ የድኩላ ፀሎት ሲያደርስ አድሮ ለማንሳት ያልቻለውን አስከሬን በየጫካው እየጣለ ሔዶ በአካባቢው ማህበሰሰብ ወግና ባህል ስርዓተ ቀብራቸው በክብር ተፈፅሞላቸዋል።

ታላቅ አማራዊ ስነልቦና በተሞላበት ወኔው አማራን አጠፋለሁ ብሎ ተማምሎ የመጣን ወንበዴ ቡድን ከህዝባቸው ጋር በመሆን አይቀጡ ቅጣት እየቀጡ እንደሆነና አሁንም በፀና ወታደራዊ አቋማቸው ተገደን የጀመርነውን የህልውና ትግል በቅርቡ ቋጭተን የአማራን ህዝብ ከተደቀነበት የሞት ድግስ እንደሚያላቅቁት በልበ ሙሉነት ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና የሸዋን ምድር በስህተት የረገጠው የአብይ አህመድ መንበር አስጠባቂ ቡድን በተስፋ ብርጌድ የፋኖ አባላት እንደ ጌሾ እየተወቀጠ ይገኛል።ከመስከረም 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት እለት ማለትም 28/01/2017 ዓም ድረስ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚፈራገጠውን የአገዛዙ አሽከር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ የፋኖ አባላት የበረታ ክንድ በተሬ፣በወሲል እና በዋኒሴ አካባቢዎች እየተገረፈ የአሞራ ቀለብ ሆኖ ይገኛል።

አምባገነኑና ፀረ አማራው የብልፅግና ቡድን በረኸት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማ ላይ ያሰራቸውን ንፁሀን ዜጎች ወደ ሌላ ቦታ ለማንቀሳቀስ ለበርካታ ጊዜ ሙከራ ቢያደርግም ከላይ ድሮን ከታች ዙ እና ዲሽቃ የማይበግራቸው የተስፋ ልጆች እስካሉ ድረስ አንድም የወረዳችንን ህዝብ ወደ ሌላ ቦታ ሊጭን እንደማይችል በአቋምም በአቅማቸውም አገዛዙን ልክ ማስገባት ችለዋል።

ድል ለተካደው የአማራ ህዝብ
መስከረም 28/2017 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
በእግረኛ ውጊያ የተሸነፈው የብልጽግና ቡድን ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል።በትላንትናው እለት በሰሜን ዳጊ ቀበሌ ትምህርት ቤትና ጤና ጣቢያዎችን የደበደበ ሲሆን በዛሬው እለትም ማለትም መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ሰሜን ሜጫ ወረዳ ቆለላ ቀበሌ በሚገኝ ትምህርት ቤት ላይ የቦምብ ናዳ ያወረደው የአብይ አህመድ አየር ኃይል ንጹሐን ላይ ጉዳት አድርሷል።

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!