#ዜና /በድሬዳዋ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት 25 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለማስከፈትና ለማፅዳት ስራ ተጀመረ
#DGC ጥቅምት 20/2019
የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ውስጥ የተዘጉ መንገዶችን ለማስከፈት፣ የተደፈኑ የውሃ ማፋሰሻ ቦዮችን ለማፅዳትና በየአካባቢው የተከማቹ ተረፈ ምርቶችን ለማስወገድ የ25 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራ መጀመሩ ተገለፀ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም፣ በአስተዳደሩ የተለያዩ ወረዳዎች ለመንገድ ጠረጋና ማስከፈቻ የሚያገለግሉ ማሽነሪዎችን ዛሬ በድሬዳዋ መንገዶች ባለሥልጣን ግቢ ተገኝተው ለሚመለከታቸው አካላት አስረክበዋል።
ከንቲባው እንደገለፁት፣ ከመንግሥት ምሥረታ ማግስት ጀምሮ ከከተማና ከገጠር ነዋሪዎች ጋር በተደረጉ ውይይቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች አለመከፈትና ተያያዥ የመሠረተ ልማት ችግሮች ከፍተኛ የህዝብ ጥያቄ ሆነው ቀርበዋል።
የችግሩን አጣዳፊነት በመገንዘብ፣ ከአስተዳደሩ ከተማ ሥራ አስኪያጅና ከመንገዶች ባለሥልጣን ጋር በተደረገ ውይይት በቀጣዮቹ ሶስት ወራት የ25 ኪሎ ሜትር የከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በማስተር ፕላኑ መሠረት የማስከፈት፣ የተደፈኑ የውሃ ማፋሰሻ ቦዮችን የማፅዳትና በተለያዩ አካባቢዎች የተከማቹ ተረፈ ምርቶችን የማስወገድ አቅጣጫ መቀመጡን አስታውቀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ወራት በገጠር አካባቢዎች ከህብረተሰቡ የተነሱ የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄዎችን፣ በኮንትራክተሮች የተጀመሩ የመንገድ ግንባታ ሥራዎችንና ሌሎች ተያያዥ የልማት ጥያቄዎችን በ2019 ዓ.ም ለማጠናቀቅ በትጋት እንደሚሠሩ ከንቲባው ገልፀዋል።
የተጀመረው እንቅስቃሴ የከተማዋን የመንገድ ተደራሽነት ለማሻሻል፣ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍና የአካባቢዎችን ፅዳት ለማስጠበቅ የሚያግዝ እርምጃ መሆኑ ይጠበቃል።
በዳግማዊ ፍቃዱ
ፎቶ፦በአገኘሉ ሸዋረጋ
ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DGCOMU
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@Direcommunication
ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB
ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!