ኮሚሽነር አለሙ መግራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ!
18ኛው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መደበኛና የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል። በጉባኤውም አቶ ኢሳያስ ጅራ ለሶስተኛ ጊዜ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሆኖ በድጋሚ ተመርጠዋል።
የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆነው ኮሚሽነር አለሙ መግራ በሚቀጥሉት አራት አመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ በዛሬው ዕለት ተረጋግጧል።
⚽ ለኮሚሽነር አለሙ መግራ እና ለተመረጡት የስራ አስፈፃሚ አባላት መልካም የስራ ዘመን እንመኛለን!

❤18👍5🔥4🙏3🥰2
የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የታዳጊዎች እግር ኳስ ልማት ስትራቴጂን ይፋ አደርገ።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የወጣቶች ልማት ስትራቴጂ የማብሰርያ መርሐ ግብር እና ከ17 ዓመት በታች ሃገር አቀፍ የሊግ ውድድር መዋቅር ምስረታ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
በዚህም የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር አንድ ላይ በመሆን ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ፕሮጀክትን በድሬዳዋ ለማስጀመር የሦስትዮች ፊርማ ተፈራረሙ

❤12👍7
የቱ ጋር ይሆን መሻሻሉ?
የኳስ ቁጥጥር ከሴኔጋል ጋር 39%_ ከሱዳን ጋር 39%፣
ሙከራ ሴኔጋል ጋር 11 _ ሱዳን ጋር 13፣
ኦን ታርጌት ሙከራ ሴኔጋል ጋር 1 _ ሱዳን ጋር 5፣
ትልቅ የግብ እድል ሴኔጋል ጋር 2 ሱዳን ጋር 4፣
በተቃራኒ ፍጹም ቅጣት ምት ቦክስ ውስጥ የተነካ ኳስ ብዛት ከሴኔጋል ጋር 14 _ ከሱዳን ጋር 14፣
ኳስ የማቀበል ጥራት ከሴኔጋል ጋር 74% _ ከሱዳን ጋር 76%
በሃገሯ የውስጥ ሊግ የሌላትን ሱዳን ገጥመንና በአልቲቲውድ የተነሳ ጨዋታውን በማዝገም እየተራመዱ ከተጫወቱት ሴኔጋሎች ጋር ተጋጥመን በሁለቱም ተሸንፈናል።
የዮሃንስ ሳህሌው ቡድን ከሁለት ሁለት አጥቶ ጉዞውን ጀምሯል።

❤4🙏1😭1
የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 2ኛ ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀን ታወቀ
የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2019 ዓ.ም. የ2ኛ ሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀንን ይፋ አደረገ።
በዚህም መሠረት የ2ኛ ሊግ ውድድሩ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም. በደማቅ ሁኔታ እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
ውድድሩ በድሬዳዋ ከተማ የእግር ኳስ እንቅስቃሴን ለማሳደግና በሊጉ የሚሳተፉ ክለቦች ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳየት ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ይጠበቃል።
የውድድሩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት፣ የሚሳተፉ ቡድኖች እና የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በፌዴሬሽኑ እንደሚገለጽ ይጠበቃል።

🔥12❤5👍3🙏3😍2
BUY SPORT
የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲሱ ሎጎ
ስለ ሎጎው በጥቂቱ
⚽ ኳሶቹ — ድሬዳዋ እግር ኳስ መፍለቂያ ከተማ በመሆኗ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑን በቀጥታ ይወክላሉ።
🚂 ባቡሩ — የድሬዳዋን ታሪካዊ የባቡር ቅርስ ይወክላል፤ ይህም ሎጎውን ከሌሎች የእግር ኳስ ሎጎዎች የተለየ ያደርገዋል።
🏛️ የድሬዳዋ ባቡር ጣቢያ — የከተማዋን ከባቡር ጋር ያላትን ታሪክ ያሳያል።
🇪🇹 የኢትዮጵያ አርማ/ባንዲራ — ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አካል መሆኑን ያመለክታል።
☀️ የፀሐይ ጨረሮች — እድገት፣ ተስፋ እና የወደፊት ስኬትን ይወክላሉ በተጨማሪም የምስራቅ የጸሃይ መውጫ መሆኗን ጭምር ይገልጻል።
🔵🔴🟡 ሰማያዊ፣ ቀይና ወርቃማ ቀለሞች — ሎጎውን እንደ ስፖርት ፌዴሬሽን አርማ ጠንካራና ሙያዊ ያደርጉታል።
በአጠቃላይ፦
“የድሬዳዋ ታሪክ + የከተማዋ ማንነት + እግር ኳስ” በአንድ አርማ ውስጥ ይገልጻል።

❤13👍2🙏1
የድሬዳዋ ሊግ 2 የእግርኳስ ዉድድር ጥቅምት 22 ይጀምራል።
የድሬዳዋ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንትና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕረዚዳንት የሆኑት ኮሚሽነር አለሙ መግራ የ2019ን የድሬዳዋ ሊግ ሁለትን እንድሁም ከ17 አመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ላይ በዚህ የዉድድር አመት የድሬዳዋ እግርኳስ ፌደሬሽን በርካታ ለዉጦችን ይዞ ብቅ እንዳለ ጠቁመዋል ለአብነትም በፊት በከተማዋ ሲከሀዱ የነበሩት የድሬዳዋ አንደኛ ድቭዝዮንና ሁለተኛ ድቭዝዮን የስም ቅያሬ ተደርጎባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህ መሠረት በአድሱ የዉድድር አመት የድሬዳዋ ታላቁ የእግርኳስ ዉድድር ከድሬዳዋ ዳዋ ከፍተኛ ድቭዝዮን ወደ ድሬዳዋ ሊግ አንድ ስያሜ ሲሸጋገር የቀድሞዉ የድሬዳዋ ዝቅተኛ ድቭዝዮን ደግሞ የድሬዳዋ ሊግ ሁለት የእግርኳስ ዉድድር የሚል ስያሜ እንደተሰጠዉ ተናግረዋል።
ለድሬዳዋ ሁለተኛ ሊግ ዉድድር ከፍተኛ የሆነ ዝግጅት ተደርጓል የሚሉት ኮሚሽነሩ እስካሁን 15 ቡድኖች ተመዝግበዋል ዉድድሩ ከኛ በተጨማሪ ያማረና የደመቀ ለማድረግ ክለቦቹ ብርቱ ፉክክር ማድረግ አለባቸዉ ምክናየቱም ነገና ከነገ ወድያ በትልቅ ዉድድር መፎካከር የሚችል ተጨዋች የምናገኘዉ እርስ በዕርስ ስንፎካከር ነዉ ብለዋል።
#ይቀጥላል.....

👍3❤1🙏1
BUY SPORT
የድሬዳዋ ሊግ 2 የእግርኳስ ዉድድር ጥቅምት 22 ይጀምራል። የድሬዳዋ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንትና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ምክትል ፕረዚዳንት የሆኑት ኮሚሽነር አለሙ መግራ የ2019ን የድሬዳዋ ሊግ ሁለትን እንድሁም ከ17 አመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ላይ በዚህ የዉድድር አመት የድሬዳዋ እግርኳስ ፌደሬሽን በርካታ ለዉጦችን…
#የቀጠለ....
ከ17 አመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጋርም በተያያዘ ኮሚሽነሩ ሀሳባቸዉን አጋርተዋል በዚህ ዉድድር በከተማዋ 10 ቡድኖች ይሳተፋሉ በደማቅ ሁኔታ ለማዘጋጀት እንሞክራለን ከ10ሩ ዉስጥ ምርጥ ዉጤት ያስመዘገበዉ ቡድን የምስራቁን የሀገራችንን ክፍል ለመወከል ከሌሎች የምስራቁ ክፍል ክለቦች ጋር ይገናኛል ያን ካለፈ ምስራቁን ክፍል በመወከል በኢትዮጵያ ደረጃ ከሌሎች ቀጠናዊ ክፍሎች ጋር ይጫወታል በዚህ ረገድ ከዳኞች ጋር በተገናኘ በትምህርት ቤቶች በመዉረድ ለተማሪዎች የዳኝነት ስልጠና ሊሰጥ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
ከሴቶች እግርኳስ ጋር በተገናኘም ኮሚሽነሩ ሀሳባቸዉን አስቀምጠዋል በሀገራችን አሁናዊ የሴቶች እግርኳስ እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነዉ ነገር ግን አሁንም ዝቅ ብለን መስራት አለብን ሁሉም የወንዶች ቡድን የሴቶች ቡድን ሊኖረዉ ይገባል ይህንንም በከተማችን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነዉ በዚህ ጥረታችን ዉስጥ ደግሞ አስተዳደሩ ድጋፍ ቢያደርግልን መልካም ነዉ ብለዋል።
ስለ ድሬዳዋ የእግርኳስ ለዉጦች ተጠይቀዉ የሰጡት ምላሽ ደግሞ እንደሚከተለዉ ነዉ ይሄ ፌደሬሽን የራሱ ቢሮ አልነበረዉም ነበር አሁን ግን የራሳችንን ቢሮ መገንባት ችለናል ለአንድ ሀገር የእግርኳስ ዉድቀት አንዱ የተቋም ዉድቀት ነዉ ተቋም ከሌለ የእግር ኳስ ለዉጥ የለም ያሉት ኮሚሽነሩ እኛ ያንን መቅረፍ ችለናል ተቋም መመስረት ብቻ ሳይሆን የፌደሬሽኑን ሎጎ ቀይረናል ይሄ ሎጎ የድሬዳዋን ባህልና እሴት የሚገልፅ እንደሆነ ተናግረዋል።
ኮሚሽነሩ በመጨረሻም የድሬዳዋ አንደኛ ሊግም ታህሳስ ወር ላይ ጅማሮ እንደሚያደርግ በመጠቆም ለአንድ ሀገር እግርኳስ እድገት ሚድያ ትልቅ አስተዋጽኦ አለዉ በዚህ መሠረት ሚድያዎች ከፌደሬሽኑ ጎን እንድቆሙ በመጠየቅ ጋዜጣዊ መግለጫቸውን አጠናቀዋል።

❤10🔥3👍2