ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት Dire Dawa Customs Branch Office
1.23K subscribers
4.39K photos
14 videos
39 files
34 links
Download Telegram
Forwarded from Ethiopian Customs Commission (Yonas Damtew)
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ738 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ
****

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሀምሌ 2 ቀን 2018 ዓ.ም )

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) የኮሚሽኑን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ለሚዲያ ባለሙያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።


ኮሚሽነር ደበሌ በመግለጫቸው ፤ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ሥራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል።


ለኮሚሽኑ ከተሰጡት ተግባራት መካከል ቀረጥና ታክስ መሰብሰብ አንዱ መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ በበጀት ዓመቱ 725.25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 738.144 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል::


የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ322.4 ቢሊዮን ብር ወይም 77.56 በመቶ ብልጫ ማሳየቱንም አስረድተዋል።


ኮሚሽነር ደበሌ (ዶ/ር) አክለውም፤ ከደንበኞች ጋር ተከታታይ ውይይቶች መደረጋቸው፣ ጠንካራ የድጋፍ እና ክትትል ሥርዓት መዘርጋቱ፣ ፈጣን ቀልጣፋ እና ፍትሐዊ አገልግሎት መሰጠቱ እንዲሁም የስጋት ሥራ አመራር ሥርዓት በተጠናከረ ደረጃ መተግበሩ ለገቢ አሰባሰቡ ዕድገት አስተዋጽዖ ማበርከቱን አስገንዝበዋል።


የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የጉምሩክ ህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ሥራም ተጨባጭ ስኬቶች መመዝገባቸውንም ኮሚሽነር ደበሌ (ዶ/ር) በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት አንስተዋል።


በዚህም 27 ቢሊዮን ብር የገቢ እና 1.9 ቢሊዮን ብር የወጪ በአጠቃላይ 28.9 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 1 ሺህ 835 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ተናግረዋል።


በአጠቃላይ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ሀገር ልታጣ የነበረውን 380.1 ቢሊዮን ብር ማዳን ተችሏልም ብለዋል።


የወጪና ገቢ ንግድን ለማሳለጥ ፣ ኮንትሮባንድ እና የንግድ ማጭበርበርን ለመከላከል እና አገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ ኮሚሽኑ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማልማት ገቢራዊ ማድረጉንም ኮሚሽነር ደበሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።


ጊዜውን የዋጀ ፣ ከዓለም ዓቀፍ የንግድ አሰራር ጋር የተጣጣሙ የህግ ማዕቀፎችን የመቅረጽ እና የማሻሻል ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቁመዋል።


የጉምሩክ ኮሚሽን በ2019 የበጀት ዓመት ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙንም በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ተመላክቷል።


ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission