የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ 85% ደረሰ
ሚያዝያ 28 ቀን 2018ዓ.ም
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአዲስ አበባ መካኒሳ ቆሬ አካባቢ የሚገነባው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት አፈጻጸም 85 በመቶ መድረሱን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዮሃንስ ኃይሉ ገለጹ ።
የተከናወኑ ዋና ዋና የግንባታዎች መካከል:-
• የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃዎች 99ተጠናቀዋል
• የመመገቢያ ህንፃ 95% የግንባታ ደረጃ ላይ ይገኛል
• የቢሮ አስተዳደር ህንፃ 87% ደርሷል
• የመማሪያ ህንፃ 59% አፈጻጸም ላይ ይገኛል።
ከተከናወኑ የሕንፃ ግንባታ ክፍሎች መካከል የመሰረት ቁፋሮ፣ የመዋቅር፣ የግንብ፣ የጣራ እና የብረት ሥራዎች 100% ተጠናቀዋል።
የህንፃዎቹ የመዋቅር ሥራ በጥራት በመከናወኑ የኮንክሬት ስላብ ሶፊት (ሶሌታ) ልስን እንዲቀር ተደርጓል ። በዚህም 5,685,138.37 ብር ወጪ ማዳን የተቻለ ሲሆን፣ ይህም በኢንተርፕራይዙ የመጀመሪያው ተሞክሮ ነው ።
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መመሪያ ባለቤት የሆነውና በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት አማካሪነት የሚከናወነው ይህ ፕሮጀክት፤ የዲዛይን ለውጥና የዋጋ ንረትን ጨምሮ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በልምድ ተቋቁሞ ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ እየደረሰ ይገኛል ። ቀሪ 15% ሥራዎችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ።

❤6
Forwarded from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

የዘመኑን የቴክኖሎጂ ሽግግር መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አሰራሩን ዘመናዊና ውጤታማ ለማድረግ የጀመረው የዲጂታላይዜሽን ጉዞ አካል የሆነው የተግባር ስልጠና ዛሬ ተሰጥቷል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ ተቋሙ ካለበት ሰፊ ኃላፊነት አንጻር አሰራሮችን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አሰራራችንን ከወረቀት ንክኪ ወደ ዲጂታል ማሸጋገር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው በማለት፣ አመራሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት እንዲከተል ስልጠናው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በአፅንኦት ሰጥተዋል።
በአመራር ደረጃ የተጀመረው ስልጠና በተዋረድ እስከ ታችኛው የሥራ ክፍል ድረስ እንደሚቀጥልና ተቋሙ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል የሥራ አካባቢ ለመቀየር የያዘውን ግብ ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በኢንተርፕራይዙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት መምሪያ የተሰጠው ይህ ስልጠና፤ የሥራ መሪዎች የኢሜል ልውውጥንና የሥራ መርሃ-ግብር ምደባን በአውትሉክ (Outlook) መተግበሪያ፣ እንዲሁም የሥራ ሪፖርት አቀራረብን በሰርኩኒ (Serkuni) መተግበሪያ በኩል በዘመናዊ መንገድ እንዲመሩ ለማስቻል የታለመ ነው። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሚሳኤል የማነ እንደገለጹት፤ ስልጠናው አመራሩ መረጃዎችን በፍጥነት እንዲለዋወጥና ሥራዎችን በቅልጥፍና እንዲያከናውን ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ ጥላሁን ደስታ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤5🔥1
ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!
ሙስናን ለመከላከል እና አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ በአስተማማኝ ሕጋዊ መሰረት ላይ የተመረኮዙ እንዲሆኑ የህግ ማዕቀፎች ወሳኝ መሳሪያዎች ናቸው።
👉 ስለ ፀረ-ሙስና ህጎች ምን ያህል ያውቃሉ?
የሀገራችንን የፀረ-ሙስና ትግል የሚመሩ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ የህግ ማዕቀፎች የሚከተሉት ናቸው፦
🌐 ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፡-
• የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ኮንቬሽን (አዋጅ ቁጥር 544/1999 ዓ.ም)፦ በሙስና የተገኘን ሀብት ማስመለስና ዓለም አቀፍ ትብብር ላይ ያተኩራል።
• የአፍሪካ ህብረት የሙስና መዋጊያና መታገያ ኮንቬሽን (አዋጅ ቁጥር 545/1999 ዓ.ም)፦ በአፍሪካ አህጉር (በተለይም በመንግስት ባለስልጣናት) የሚፈጸሙ ሙስናዎችን ለመዋጋት የወጣ ስምምነት ነው።
🇪🇹 ዋና ዋና የሀገር ውስጥ ህጎች፡-
• የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 ዓ.ም፦ የተለያዩ የሙስና ወንጀሎችንና ቅጣቶችን በ25 አንቀጾች (ከአንቀጽ 9 እስከ 33) ደንግጎ የያዘ ተቀዳሚ ህግ ነው።
• የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 ዓ.ም፦ ተመራጮች፣ ተሿሚዎችና የመንግስት ሰራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ በማስገደድ የመንግስት ሀብት እንዳይመዘበር ይከላከላል።
• የተሻሻለው የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1236/2013 ዓ.ም፦ በትውልድ ሥነ-ምግባር ግንባታ እና በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ላይ ይሰራል፡
የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ (1183/2012)
የምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ (699/2003)፣ የመንግስት ግዥ አዋጅ (1333/2016) እና የንብረት ማስመለስ አዋጅ (1364/2017) ይጠቀሳሉ።
"ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር እንገንባ!"

❤4👍1
Forwarded from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
ኢንተርፕራይዙ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፕሮጀክት ተመረቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል ግንባታን ከተሰጠው የውል ጊዜ ቀድሞ ያጠናቀቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ምስጋና ተችሮታል።
በድሬዳዋ ከተማ የተገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በዛሬው እለት በተመረቀበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን በልዩ ሁኔታ አመስግነዋል።
ኢንተርፕራይዙ ለፕሮጀክቱ ከተሰጠው የውል ማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በጥራት አጠናቆ ማስረከቡን በከፍተኛ አድናቆት የገለፁት ኮሚሽነር ጄኔራሉ የማዕከሉ ግንባታ ሳይጓተት የተጠናቀቀው፣ ያጋጠሙ የተለያዩ ማነቆዎችን በተግባር በመቅረፍ መሆኑን አብራርተዋል።
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ለግንባታው የወጣው ወጪ ካለው አጠቃላይ የገበያና የኮንስትራክሽን ሁኔታ አንጻር እጅግ ወጪ ቆጣቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማዕከሉን ልክ እንደ ራሱ ተቋም በመቁጠር በጥራትና በከፍተኛ ቁርጠኝነት የገነባ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢንተርፕራይዙ በተመሳሳይ መልኩ በሐረር ከተማ የሚገኘውንና በቀጠናው ዘመናዊ የሆነውን የፖሊስ ሆስፒታል ግንባታ ወደ ማጠናቀቂያው ማድረሱንም ጠቁመዋል።
ማዕከሉ ድሬዳዋ ላይ መመስረቱ ለአካባቢውና ለአጎራባች የሐረሪና የሶማሌ ክልሎች ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፣ ግንባታው በጥራትና በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቁ ለቀጠናው ትልቅ ኩራት መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካሪነት ግንባታው የተከናወነውና ዛሬ በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ማዕከል የአስተዳደር ቢሮ ህንጻ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የሴቶችና የወንዶች ዶርሚተሪዎች፣ ክሊኒክ፣ የእንግዳ ማረፊያ እንዲሁም ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ያካተተ ነው።
ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል ግንባታን ከተሰጠው የውል ጊዜ ቀድሞ ያጠናቀቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ምስጋና ተችሮታል።
በድሬዳዋ ከተማ የተገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በዛሬው እለት በተመረቀበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን በልዩ ሁኔታ አመስግነዋል።
ኢንተርፕራይዙ ለፕሮጀክቱ ከተሰጠው የውል ማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በጥራት አጠናቆ ማስረከቡን በከፍተኛ አድናቆት የገለፁት ኮሚሽነር ጄኔራሉ የማዕከሉ ግንባታ ሳይጓተት የተጠናቀቀው፣ ያጋጠሙ የተለያዩ ማነቆዎችን በተግባር በመቅረፍ መሆኑን አብራርተዋል።
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ለግንባታው የወጣው ወጪ ካለው አጠቃላይ የገበያና የኮንስትራክሽን ሁኔታ አንጻር እጅግ ወጪ ቆጣቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማዕከሉን ልክ እንደ ራሱ ተቋም በመቁጠር በጥራትና በከፍተኛ ቁርጠኝነት የገነባ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢንተርፕራይዙ በተመሳሳይ መልኩ በሐረር ከተማ የሚገኘውንና በቀጠናው ዘመናዊ የሆነውን የፖሊስ ሆስፒታል ግንባታ ወደ ማጠናቀቂያው ማድረሱንም ጠቁመዋል።
ማዕከሉ ድሬዳዋ ላይ መመስረቱ ለአካባቢውና ለአጎራባች የሐረሪና የሶማሌ ክልሎች ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፣ ግንባታው በጥራትና በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቁ ለቀጠናው ትልቅ ኩራት መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካሪነት ግንባታው የተከናወነውና ዛሬ በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ማዕከል የአስተዳደር ቢሮ ህንጻ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የሴቶችና የወንዶች ዶርሚተሪዎች፣ ክሊኒክ፣ የእንግዳ ማረፊያ እንዲሁም ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ያካተተ ነው።
ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Telegram
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤6👏4👍3👎3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ
(አረፋ) በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ
(አረፋ) በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!
ዒድ ሙባረክ!
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
👍5❤1👏1
Forwarded from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እያካሄደ የሚገኘው የለውጥ ጉዞ ትግበራ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጀመረውን ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረውንና አሠራሩን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ የሚያደርገውን የኢአርፒ ERP (Enterprise Resource Planning) ሲስተም ትግበራ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ አድርሷል፡፡
ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ተቋሙ ያለውን አቅም በማቀናጀት ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተወዳዳሪ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ጠንካራ መሠረት የጣለ ሲሆን፤ ቴክኖሎጂውን ከሰው ኃይል አቅም ጋር ለማዋሃድ ታስቦ የተዘጋጀው የማጠቃለያ የተግባርና የለውጥ አስተዳደር ሥልጠና በኢንተርፕራይዙ ተሰጥቷል፡፡
ለዲጂታል ሽግግሩ ግንባር ቀደም መሪ የሆኑት የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄነራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፣ ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የመምሪያ ኃላፊዎችና የቡድን መሪዎች በሥልጠናው ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ከኤክሲድ (Exceed) ኩባንያ የመጡት የለውጥ አስተዳደር፣ ማርኬቲንግ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት የሥራ ክፍል ኃላፊ አቶ መኮነን ትኩ ሥልጠናውን የሰጡ ሲሆን፤ አመራሮቹ አዲሱን ሲስተም ከዕለት ተዕለት የሥራ ሂደት ጋር እንዴት ማዋሃድ እንደሚችሉ፣ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶችን በዲጂታል መንገድ መምራትን እና አዳዲስ አሠራሮች ሲተገበሩ የሚገጥሙ የሰዎችን የሥነ-ልቦና ተግዳሮቶች በብልሃት እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል በጋራ ውይይትና ልምምድ አድርገዋል፡፡
አሰልጣኙ ማሽኖችንና ሲስተሞችን መቀየር ብቻውን ለውጥ እንደማያመጣ ጠቁመው፣ ዋናው ስኬት የሚገኘው የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች የጋራ ግንዛቤና ዝግጁነት ሲኖራቸው መሆኑን በሥልጠናው ላይ አስገንዝበዋል፡፡
ሥልጠናው በየደረጃው በሚገኙ መሪዎች መካከል ጠንካራ የሥራ ቅንጅት የፈጠረ ሲሆን፤ ከፍተኛ አመራሩን በስትራቴጂካዊ ዕይታ፣ መካከለኛውን አመራር በክትትልና ትግበራ፣ እንዲሁም በታችኛው እርከን ላይ የሚገኘውን ፈጻሚ የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ እንዲያከናውን አዲስ አቅምና መነሳሳትን የፈጠረ ነው።

❤3👍1